Skip to main content

ፍቅር በአርጩሜ!


ያኔ ትምህርት ቤት ቀለሙን ስንቀልም፣
ስሌት ስናሰላ ሰይንስ ስንጠበብ፣
አይናችን ሲገለጥ ሁሉን ስንካን፣
ፍቅርን ዝም አሉን የኛ መምህር፡፡
ትዝ ይለኛል ያኔ....
የክፍሌ ተማሪ ፍቅር ብታሲዘኝ፣
አይናፋርነጸቷ ዝምታዋ ቢያመኝ፣
ፍቅረሯ አያማለለ መማሩ ቢሳነኝ፣
ትዝ ይለኛል ያኔ....
ቃላት አውጣጥቼ ደብዳቤ መፃፌ፣
ባማሩ ቃላቶች ወደድኩሽ ማለቴ፤
ግና ምን ይሆናል....
ወድጃለሁ ብዬ ሃሳቤን በገለፅኩ፣
እሰልፉ መሃል ላይ ባርጩሜ ተገረፍኩ፡፡
መቼ በዚህ ብቻ....
እንደወንጀለኛ ፍርድ እንዳጎደለ፣
ማፍቀሬ ተወራ ጉድ እየተባለ፡፡
መቼ በዚህ ብቻ....
የአርጩሜው መዘዝ ስር አየሰደደ፣
ፍቅር በአርጩሜ ከኔ ተዋሀደ፡፡
ይመስገነው ዛሬ ሴትን አልጠይቅም፣
የማፍቀሩን ፀጋ ነፃነት አላውቅም፣
ሰጠየቅ እሺ እንጂ እኔ አልጠይቅም፡፡
እኔ!?....
ምን በወጣኝ! - እኔ አልጠይቅም፣
እኔ!?....
በስመአብ!! - እኔ አልጠይቅም፣
እኔ!?....
እማማ ትሙት - እኔ አልጠይቅም፡፡

1981 ዓ.ም. — ናዝሬት
በመስፍን ገብሬ ወንዳፍራሽ (ቅንጣት 2005ዓ.ም.)

Comments

Popular posts from this blog

Hino da Etiópia (voz) Ethiopia National Anthem (vocal) (source: http://s.ytimg.com)

The man who taught Mandela to be a soldier

       The man who taught Mandela to be a soldier By Penny Dale BBC Africa, Addis Ababa In July 1962, Col Fekadu Wakene taught South African political activist Nelson Mandela the tricks of guerrilla warfare - including how to plant explosives before slipping quietly away into the night. Mr Mandela was in Ethiopia, learning how to be the commander-in-chief of Umkhonto we Sizwe - the armed wing of the African National Congress (ANC). The group had announced its arrival at the end of 1961 by blowing-up electricity pylons in various places in South Africa. Then on 11 January 1962, Mr Mandela had secretly, and illegally, slipped out of South Africa. His mission was to meet as many African political leaders as possible and garner assistance for the ANC, including money and training for its military wing. And to be moulded into a soldier himself. During this trip, he visited Ethiopia twice and left a deep impression on those who met ...

When one loves nature and all its value, art takes the position to tell the story!

ፍቅር በአርጩሜ! ያኔ ትምህርት ቤት ቀለሙን ስንቀልም፣ ስሌት ስናሰላ ሰይንስ ስንጠበብ፣ አይናችን ሲገለጥ ሁሉን ስንካን፣ ፍቅርን ዝም አሉን የኛ መምህር፡፡ ትዝ ይለኛል ያኔ.... የክፍሌ ተማሪ ፍቅር ብታሲዘኝ፣ አይናፋርነጸቷ ዝምታዋ ቢያመኝ፣ ፍቅረሯ አያማለለ መማሩ ቢሳነኝ፣ ትዝ ይለኛል ያኔ.... ቃላት አውጣጥቼ ደብዳቤ መፃፌ፣ ባማሩ ቃላቶች ወደድኩሽ ማለቴ፤ ግና ምን ይሆናል.... ወድጃለሁ ብዬ ሃሳቤን በገለፅኩ፣ እሰልፉ መሃል ላይ ባርጩሜ ተገረፍኩ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... እንደወንጀለኛ ፍርድ እንዳጎደለ፣ ማፍቀሬ ተወራ ጉድ እየተባለ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... የአርጩሜው መዘዝ ስር አየሰደደ፣ ፍቅር በአርጩሜ ከኔ ተዋሀደ፡፡ ይመስገነው ዛሬ ሴትን አልጠይቅም፣ የማፍቀሩን ፀጋ ነፃነት አላውቅም፣ ሰጠየቅ እሺ እንጂ እኔ አልጠይቅም፡፡ እኔ!?.... ምን በወጣኝ! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... በስመአብ!! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... እማማ ትሙት - እኔ አልጠይቅም፡፡ 1981 ዓ.ም. — ናዝሬት በመስፍን ገብሬ ወንዳፍራሽ (ቅንጣት 2005 ዓ.ም.)