Skip to main content

Posts

Showing posts from December 9, 2013

ይብላኝ…

ችግር ወላፈኑ ጠብሶሽ በላብሽ ፍሳሽ ልታብሽው እንደዋዛ ካገር ወተሽ ደፋ ብለሽ ለቀረሽው በደሌን አሁን አወኩት ምትክ በሌለው ብዕርሽ ሰቆቃሽ ገፍቶ በፃፍሽው በድንጋይ ላይ ትርክትሽ በሞትሽ ቃል ገለፅሽው እህቴ ልናዘዝ ስሚኝ በባዕድ ሀገር ወርውሬ የገደልኩሽ እኔነኝ ስሚኝ… የጅብ ከሄደ ጩኸቴን የምፀት ቃል ምሬቴን የፍርሀት ጠርዝ መልክቴን የምላስ ተርፍ በረከቴን ይብላኝ… ያያትሽን ግብር ሳልፈፅም በሞቴ ሂወት ሳልሰጥሽ ከጠላትሽ ጋር አብሬ እኔው በጅ አዙር ገደልኩሽ ይብላኝ… የሞትሽ ፀፀት ሳይበቃኝ እንደገና ልገልሽ በሰልፍ ወደሞት ስቴጂ ዝም ብዬ ለማይሽ ይብላኝ… የሰው ትርፍ አርጌ እንደ አይረባ ለጣልኩት ውርደትሽን ክብር አርጌ በደምሽ ወዝ ለራስኩት የናቴ ልጅ… እኔን ይድፋኝ ልበልሽ ልደፋ ይድረሰኝ ፅዋሽ ነፃ ማውጣቱ ቢያቅተኝ ሞትሽን ባፌ ልጋራሽ /ፀደቀ ድጋፌ/