Skip to main content

Posts

Showing posts from November 23, 2013

ፍቅር በአርጩሜ!

ያኔ ትምህርት ቤት ቀለሙን ስንቀልም፣ ስሌት ስናሰላ ሰይንስ ስንጠበብ፣ አይናችን ሲገለጥ ሁሉን ስንካን፣ ፍቅርን ዝም አሉን የኛ መምህር፡፡ ትዝ ይለኛል ያኔ.... የክፍሌ ተማሪ ፍቅር ብታሲዘኝ፣ አይናፋርነጸቷ ዝምታዋ ቢያመኝ፣ ፍቅረሯ አያማለለ መማሩ ቢሳነኝ፣ ትዝ ይለኛል ያኔ.... ቃላት አውጣጥቼ ደብዳቤ መፃፌ፣ ባማሩ ቃላቶች ወደድኩሽ ማለቴ፤ ግና ምን ይሆናል.... ወድጃለሁ ብዬ ሃሳቤን በገለፅኩ፣ እሰልፉ መሃል ላይ ባርጩሜ ተገረፍኩ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... እንደወንጀለኛ ፍርድ እንዳጎደለ፣ ማፍቀሬ ተወራ ጉድ እየተባለ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... የአርጩሜው መዘዝ ስር አየሰደደ፣ ፍቅር በአርጩሜ ከኔ ተዋሀደ፡፡ ይመስገነው ዛሬ ሴትን አልጠይቅም፣ የማፍቀሩን ፀጋ ነፃነት አላውቅም፣ ሰጠየቅ እሺ እንጂ እኔ አልጠይቅም፡፡ እኔ!?.... ምን በወጣኝ! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... በስመአብ!! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... እማማ ትሙት - እኔ አልጠይቅም፡፡ 1981 ዓ.ም. — ናዝሬት በመስፍን ገብሬ ወንዳፍራሽ (ቅንጣት 2005 ዓ.ም.)