የሷ ሱስ December 07, 2013 የወደዷትን ልጅ እያወዳደሱ እያሞጋገሱ እንዲህ እያስደነሱ፤ ልፍታ ልተው ቢሏት እንኳንስ ፍቅሯና አይለቅህም ሱሱ! tsenawoo Share Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Share Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ January 24, 2014 እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የ... Read more
When one loves nature and all its value, art takes the position to tell the story! December 12, 2013 ፍቅር በአርጩሜ! ያኔ ትምህርት ቤት ቀለሙን ስንቀልም፣ ስሌት ስናሰላ ሰይንስ ስንጠበብ፣ አይናችን ሲገለጥ ሁሉን ስንካን፣ ፍቅርን ዝም አሉን የኛ መምህር፡፡ ትዝ ይለኛል ያኔ.... የክፍሌ ተማሪ ፍቅር ብታሲዘኝ፣ አይናፋርነጸቷ ዝምታዋ ቢያመኝ፣ ፍቅረሯ አያማለለ መማሩ ቢሳነኝ፣ ትዝ ይለኛል ያኔ.... ቃላት አውጣጥቼ ደብዳቤ መፃፌ፣ ባማሩ ቃላቶች ወደድኩሽ ማለቴ፤ ግና ምን ይሆናል.... ወድጃለሁ ብዬ ሃሳቤን በገለፅኩ፣ እሰልፉ መሃል ላይ ባርጩሜ ተገረፍኩ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... እንደወንጀለኛ ፍርድ እንዳጎደለ፣ ማፍቀሬ ተወራ ጉድ እየተባለ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... የአርጩሜው መዘዝ ስር አየሰደደ፣ ፍቅር በአርጩሜ ከኔ ተዋሀደ፡፡ ይመስገነው ዛሬ ሴትን አልጠይቅም፣ የማፍቀሩን ፀጋ ነፃነት አላውቅም፣ ሰጠየቅ እሺ እንጂ እኔ አልጠይቅም፡፡ እኔ!?.... ምን በወጣኝ! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... በስመአብ!! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... እማማ ትሙት - እኔ አልጠይቅም፡፡ 1981 ዓ.ም. — ናዝሬት በመስፍን ገብሬ ወንዳፍራሽ (ቅንጣት 2005 ዓ.ም.) Read more
ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም.የግጥም መድብል .... December 15, 2013 አስገራሚ ገጠመኞች የተስተዋሉበት የግጥም መድብል ምርቃት ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም. በልዩ ሁኔታ በኢትዮጲያ ወመዘክር አዳራሽ ተፈፀመ፡፡ Read more
Comments
Post a Comment