Skip to main content

ይብላኝ…

ችግር ወላፈኑ ጠብሶሽ
በላብሽ ፍሳሽ ልታብሽው
እንደዋዛ ካገር ወተሽ
ደፋ ብለሽ ለቀረሽው

በደሌን አሁን አወኩት
ምትክ በሌለው ብዕርሽ
ሰቆቃሽ ገፍቶ በፃፍሽው
በድንጋይ ላይ ትርክትሽ
በሞትሽ ቃል ገለፅሽው

እህቴ ልናዘዝ ስሚኝ
በባዕድ ሀገር ወርውሬ
የገደልኩሽ እኔነኝ

ስሚኝ…

የጅብ ከሄደ ጩኸቴን
የምፀት ቃል ምሬቴን
የፍርሀት ጠርዝ መልክቴን
የምላስ ተርፍ በረከቴን

ይብላኝ…

ያያትሽን ግብር ሳልፈፅም
በሞቴ ሂወት ሳልሰጥሽ
ከጠላትሽ ጋር አብሬ
እኔው በጅ አዙር ገደልኩሽ

ይብላኝ…

የሞትሽ ፀፀት ሳይበቃኝ
እንደገና ልገልሽ
በሰልፍ ወደሞት ስቴጂ
ዝም ብዬ ለማይሽ

ይብላኝ…

የሰው ትርፍ አርጌ
እንደ አይረባ ለጣልኩት
ውርደትሽን ክብር አርጌ
በደምሽ ወዝ ለራስኩት

የናቴ ልጅ…

እኔን ይድፋኝ ልበልሽ
ልደፋ ይድረሰኝ ፅዋሽ
ነፃ ማውጣቱ ቢያቅተኝ
ሞትሽን ባፌ ልጋራሽ

/ፀደቀ ድጋፌ/
ችግር ወላፈኑ ጠብሶሽ
በላብሽ ፍሳሽ ልታብሽው
እንደዋዛ ካገር ወተሽ
ደፋ ብለሽ ለቀረሽው

በደሌን አሁን አወኩት
ምትክ በሌለው ብዕርሽ
ሰቆቃሽ ገፍቶ በፃፍሽው
በድንጋይ ላይ ትርክትሽ
በሞትሽ ቃል ገለፅሽው

እህቴ ልናዘዝ ስሚኝ
በባዕድ ሀገር ወርውሬ
የገደልኩሽ እኔነኝ

ስሚኝ…

የጅብ ከሄደ ጩኸቴን
የምፀት ቃል ምሬቴን
የፍርሀት ጠርዝ መልክቴን
የምላስ ተርፍ በረከቴን

ይብላኝ…

ያያትሽን ግብር ሳልፈፅም
በሞቴ ሂወት ሳልሰጥሽ
ከጠላትሽ ጋር አብሬ
እኔው በጅ አዙር ገደልኩሽ

ይብላኝ…

የሞትሽ ፀፀት ሳይበቃኝ
እንደገና ልገልሽ
በሰልፍ ወደሞት ስቴጂ
ዝም ብዬ ለማይሽ

ይብላኝ…

የሰው ትርፍ አርጌ
እንደ አይረባ ለጣልኩት
ውርደትሽን ክብር አርጌ
በደምሽ ወዝ ለራስኩት

የናቴ ልጅ…

እኔን ይድፋኝ ልበልሽ
ልደፋ ይድረሰኝ ፅዋሽ
ነፃ ማውጣቱ ቢያቅተኝ
ሞትሽን ባፌ ልጋራሽ

/ፀደቀ ድጋፌ/

Comments

Popular posts from this blog

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የ...

ቀልድ ስላለማወቃችን

12/11/2006EC አንድ ሰሞን ወደሁለት ተከፍላ ብዙም ሳትቆይ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው ሱዳን የገጠማትን ምስቅልቅል ሁኔታ ለመከታተል አለም ሁሉ ጆሮውን አቁሞ ነበረ፡፡ ቀድሞም ጠግቦ ያላደረው ደሃ ሕዝብ ነፍሱን ስለማቆየት ሲል ወደጎረቤት ሀገራት ተሰዷል፡፡ በዛ አስቸጋሪ ወቅት ግን አቶ ሳልቫኪየር ከየሀገራቸው እድገትና ስልጣኔ ያልተመጣጠነ ምቾት ስላሰከራቸው አቻዎቻቸው ጉዳይ እንጂ ስለ ሕዝባቸው ፈፅሞ ግድ የሌላቸው እንደሆነ መሰከሩልን፡፡ “የፀጥታውን ስምምነት የፈረምኩት የኢትዮጲያው ጠቅላይ ሚኒሰተር አስርሃለሁ ስላሉኝ ነው”-ብለው አስደመሙን፡፡  ጋዜጠኞቹም ለጉዳዩ መልስ ሲጠባበቁ ቆዩና ሰሞኑን አቶ ኃይለማሪያምን ማብራሪያ ይጠይቋቸዋል፡፡ እርሳቸውም ሳልቫኪየር ቀልዴን ነው ብለዋል ሲሉ መለሱ፡፡ እንዲያውም እነዚህ ጋዜጠኞች ቀልድ አያውቁም ብለው መናገራቸውን ሊያብራሩ ሞክረው አለፉ፡፡ ይህም የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ደረቅ ቀልድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኢቴቪ 1 ፣ 2 ፣ 3 ፣ 4 ተብሎ ይቀለዳል፤ ስለመብራት ስርጭት ብዙ ቁም ነገር የሚመስሉ ቀልዶች እንሰማለን፤ እናያለን፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት ላይ በተጠናከረ መልክ እየሰሩ መሆኑን ይነግሩናል__የቀልዳቸውን፡፡ መንግስት ጸረ - ሰላም ሀይሎች የህዝብን ጥቅም የሚነኩ ኢ - ሰብዐዊ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው ብሎ የቀልዱን ይነግረንና አሴሩ የተባሉትን አሳራቸውን ያበላቸዋል፤ግን የቀልዱን ነው፡፡የሃገሪቷን ሰላም ለማደፍረስ ስለመነሳታቸው መረጃ የለማ ! ቀላል የከተማ ባቡር መጓጓዣን ስራ ለማሰጀመር ሩጫው እየተፋጠነ መሆኑ በተደጋጋሚ በቴሌ...

የሷ ሱስ

የወደዷትን ልጅ እያወዳደሱ እያሞጋገሱ እንዲህ እያስደነሱ፤ ልፍታ ልተው ቢሏት እንኳንስ ፍቅሯና አይለቅህም ሱሱ! tsenawoo