Watch this video
(This post had been on my other blog since April 04,2013. Please consider the original post date while reading.) ዘመነ ወሲብ ዛሬ ዛሬ መቼም ትዳር የሚባለው ጎጆ የጋብቻ ምሰጢር ያለበት አልመስል ብሏል፡፡ በአፀያፊ መልኩ ዎንዶችና ሴቶች ገና ጨቅላ በሚባል የጉልምስና (በዘመንኛው ቃል የፍንዳታ እድሜ ይሉታል፡፡) እድሜያቸው ወሲብ መጀመራቸውና በአስራዎቹ አጋማሽ ላይ ሲደርሱ ዓለም ሰየጠንሁ ያለበትን የወሲብ ክህሎት ጣራ ነክተው ከዚያ ሲዳክሩ ይከረሙና በወላጅ ይሁን በኑሮ ግፊት ትዳር ይመሰርታሉ፡፡ የዚህ አዲስ አይነት ጎጆ አባላት ደግሞ በአብዛኛው የሚያስቁ ጥነዶች የሆናሉ፡፡ እነዲህ ያለው ትዳር የተመሰረተው ለገንዘብ ወይም ለውጭ ሀገር ዕድል ከሆነ፤ ተጋቢዎቹም ሆነ ገገባው ሩቅ ሳይሄድ ህጋዊ ፍች እንደሚፈፀምበት ገና የሰርጉ እለት ያውቁታል፡፡ በቤተሰብ ግፊትና በአብሮ አበዶች ሆይሆይታ የሚቀለስም ተመሳሳይ ጎጆ አለ፡፡ ብቻ ይህኛውም መቼ እነደሚሆን አይታወቅም እንጂ ላይዘልቅ እንደሚችል ተጋቢዎቹም ሆኑ እኛ ስለጋብቻው አሁን የሰማን ሰዎች ከልምዳችን በመነሳት እርግጠኞች መሆን ንችላለን፡፡ የሆኖሆኖ የዛሬ ትዳር ምነም እክሎችን የያዘ እነደሆነ ላሰታውሳችሁ፡፡ ውሽምና ድጋፍ ባያገኝም አስከዚህኛው ትውልድ በመዝለቁ፤ ወደሽርሙጥና እና የዳማ በሚል ስያሜ በቡድን ለሚፈፀም ሰው ሰራሽ አረመኔያዊ ወሲብነት አድጓ፡፡ ጥነዶች በአንድ ጣራ ስር ሆነው እንኳ በተመሳሳይ ሰዓት ከተለያዩ ሰዎች ጋር በስልክ ወሲብ ራሳቸውን ያረካሉ፡፡ የነውሩ ዘመን በአባቶቻችንና ከዚያ ቀደም ባለው ትውልድ ወሲብ በይፋ በየመንገዱ እንደልብ የሚወሳ ሳይሆን እንደነውር ...
Comments
Post a Comment