Skip to main content

I am an Oromo too! ስለምን ይዘበትብናል…?



እኛ በሰው አምሳል መፈጠራችንንና ከናንተው እኩል የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ስለመሆናችን እንዴት ተዘነጋችሁ!
ቀደምት አባቶቻችን ስንቶቹን ደራሽ ያጡ የሀገራችንን ኢትዮጲያ ልጆች ጡት እያጠቡ ከአብራካቸው ከወጡ ልጆቻቸው እኩል እያስተማሩና ሀብት ንብረት እያወረሱ ለወግ ማዕረግ ያበቁ መሆናቸው ተረሳችሁ…?
ኢትዮጲያዊነትን ከኦሮሞ ሕዝብ፤ የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጲያዊነት በመነጣጠል የምታገኙት ልዩ ጥቅም እነደሚኖር ሳይታለም የተፈታ መሆኑ በየጓዳው የሚወራው ለዚህም አይደል ብላችሁ እነዴት አልጠረጠራችሁም…? ሕዝቡ ሁሉ ተጠርጣሪ (ሊያውም በሽብርተኝነት) ተብሎ በይፋ እስር ቤት  እንዲገባ የሚቻላችሁ መስሏችሁ ይሆን…? እንኪያስ የትኛውን ሕዝብ ልትመሩት ነው…?(ይቅርታ በአይንህን ጨፍን ላሞኝህ ልትነግዱበት ነው…?- ለማለት ፈልጌ ነው፡፡)
ለነገሩ ዞን 9ኞችን የመፍጠሩ ስትራቴጂ ሲነቃባችሁ ዞን 9 ነዋሪውን ትታችሁ ብሎገሮቹን ታስሩ ታንገላቱ ታሳድዱ ዘንድስ ማን አይዟችሁ እንዳላችሁ ምን ይታወቃል…? ይህች ፅሁፍ እንኳ ካቅሟ በመንግስታችሁ እውቅና አግኝታ ከመነበብና የፀሃፊውን መብት ከማስከበር ትታገድ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል…?
ዓለም ሁሉ በንግድ /ቢዝነስ/ ፅንሰ ሃሳብ በተወጠረችበት በዚህ ዘመን የኋሊዮሽ የተንቋሸሸሽንበት ያህል እንዲሰማን የተደረግንባቸውን የሀገራችንን ታሪክ እየባዘታችሁ ስለምን የትውልዱን ተስፋ በቁንፅል ሃሳብ በመወጠር ትቀጩብናላችሁ…? እናንተ የምትገነቡትን ሕንፃ፣ ለሎችን በመጨቆን ስንጥቅ የምታተርፉበትን ንግድ፣ በሀሰት ህዝብን እየሸነገላችሁ የምትቸበችቡትን መሬት፣ የምታቀያይሯቸውን መኪኖች፣ ህዝብ የሚያውቃቸውና የማያውቃቸው በአጭር ጊዜ የምትበለፅጉባቻው መንገዶች ሁሉ ከዓይንና ከህሊናችን የተሰወሩ ይመስላችሁ ይሆን…?
እንዲያው በንፅፅር ቢታይ ስንት ስንተኛው ወገናችሁ እና (በእናንተ አከፋፈል ህዝቡን ብንሸነሽነው ማለቴ ነው) ወገናችን አለፈለት…? ስንት ስንተኛውስ ከድጡ ወደማጡ ዘቀጠ…? እነዲያው ስነቱ ተገደለ…?  ስንቱ ታሰረ…?  ስለምን በምግባር ኮተኩቶ ማሳደግ እና በሀገሩ የሚኮራ ዜጋን ማፍራት የሚችለውን ያማረ ባህላችንን ጥራት ለሌለውና ሕይወትን ከመምራት ይልቅ በማልኮስኮስ ለአጉል ስልጣኔ መሳይ መጥፊያ በሚዳርግን ዘመናዊ ባርነት እኛ ወገኖቻችሁንእንዴት በሹማምንቶቻችሁ በኩል አሳልፋችሁ ሰጣችሁን…?
እንዲያው ለመሆኑ በርካቶችን እያስራቡ ዕጅግ ጥቂቶችን ማበልፀግ የትኛው ሀገር ወዳድነት ነውና…?  የሰው ልጅ ማህበራዊ ፋይዳ ገንዘብና ንብረት በማከማቸት ብቻ የሚታነፅ ነውን…? የለውጥ ዋንኛ መገለጫ የሀብት ብልፅግና ብቻ ነው ብላችሁ ትውልዱን እንድትጠመዝዙ ማን የቤት ስራ ሰጥቷችሁ ይሆን…?

Comments

Popular posts from this blog

የወሲብ ግፍና ዘመን

(This post had been on my other blog since April 04,2013. Please consider the original post date while reading.) ዘመነ ወሲብ ዛሬ ዛሬ መቼም ትዳር የሚባለው ጎጆ የጋብቻ   ምሰጢር ያለበት አልመስል ብሏል፡፡ በአፀያፊ መልኩ ዎንዶችና ሴቶች ገና ጨቅላ በሚባል የጉልምስና (በዘመንኛው ቃል የፍንዳታ እድሜ ይሉታል፡፡) እድሜያቸው ወሲብ መጀመራቸውና በአስራዎቹ አጋማሽ ላይ ሲደርሱ ዓለም ሰየጠንሁ  ያለበትን የወሲብ ክህሎት ጣራ ነክተው ከዚያ ሲዳክሩ ይከረሙና በወላጅ ይሁን በኑሮ ግፊት ትዳር ይመሰርታሉ፡፡ የዚህ አዲስ አይነት ጎጆ አባላት ደግሞ በአብዛኛው የሚያስቁ ጥነዶች የሆናሉ፡፡ እነዲህ ያለው ትዳር የተመሰረተው ለገንዘብ ወይም ለውጭ ሀገር ዕድል ከሆነ፤ ተጋቢዎቹም ሆነ ገገባው ሩቅ ሳይሄድ ህጋዊ ፍች እንደሚፈፀምበት ገና የሰርጉ እለት ያውቁታል፡፡ በቤተሰብ ግፊትና በአብሮ አበዶች ሆይሆይታ የሚቀለስም ተመሳሳይ ጎጆ አለ፡፡ ብቻ ይህኛውም መቼ  እነደሚሆን አይታወቅም እንጂ ላይዘልቅ እንደሚችል ተጋቢዎቹም ሆኑ እኛ ስለጋብቻው አሁን የሰማን ሰዎች ከልምዳችን በመነሳት እርግጠኞች መሆን ንችላለን፡፡ የሆኖሆኖ የዛሬ ትዳር ምነም እክሎችን የያዘ እነደሆነ ላሰታውሳችሁ፡፡ ውሽምና ድጋፍ ባያገኝም አስከዚህኛው ትውልድ በመዝለቁ፤ ወደሽርሙጥና  እና  የዳማ በሚል ስያሜ በቡድን ለሚፈፀም ሰው ሰራሽ አረመኔያዊ ወሲብነት አድጓ፡፡ ጥነዶች በአንድ ጣራ ስር ሆነው እንኳ በተመሳሳይ ሰዓት ከተለያዩ ሰዎች ጋር በስልክ ወሲብ ራሳቸውን ያረካሉ፡፡ የነውሩ ዘመን   በአባቶቻችንና ከዚያ ቀደም ባለው ትውልድ ወሲብ በይፋ በየመንገዱ እንደልብ የሚወሳ ሳይሆን እንደነውር ...

Hino da Etiópia (voz) Ethiopia National Anthem (vocal) (source: http://s.ytimg.com)

የሷ ሱስ

የወደዷትን ልጅ እያወዳደሱ እያሞጋገሱ እንዲህ እያስደነሱ፤ ልፍታ ልተው ቢሏት እንኳንስ ፍቅሯና አይለቅህም ሱሱ! tsenawoo