Skip to main content

Posts

Showing posts from 2018

አሁንም መጠየቅና መጠየቅ አለብን!!!

የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዳይሻሻል እንሻለን?!   እኔ ሀገር እየኖራችሁ ስለትራንስፖርት ችግር ሳትሰሙ እና ሳታወሩ መዋል እና ማደር ከቶ እንደማይቻል የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ በሁለቱም ገዢዎቻችን   (በሙሰኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና በህጋዊ ማእቀፍ በህገወጥነት ከሚበለፅጉት ነጋዴዎች) ዘንድ የመፍትሄ ሀሳብ ሊቀርብበት የተደፈረ ጉዳይ እንኳ አልመስል ብሏል፡፡ የመኪና መንገዶች አብዛኛው አስፋልት መንገድ ከፈሰሰበት የሀብት መጠን አንጻር በበርካታ ምክኒያቶች ተገቢውን አገልግሎት ሳይሰጥ እንደሚቀር ከሁሉ አይን የተሰወረ ባይሆንም፣ መልካም አስተዳደር ጉድለት ግን ችግሩን አባብሶታል፡፡ እኔ ተዘዋውሬ በማውቅባቸው ቦታዎች ሁሉ ያስተዋልኩት አንዱ ነገር የመኪና ማቆም (ፓርኪንግ) ነው፡፡ የቀለበት መንገዶችን ጨምሮ (ለብዙ የሙዚቃ ቪዲዮ ክሊፖች እንዳልተመረጡ …. ጊዜ ጥሏቸው…) በርካታ የአስፋልት መንገዶች በህጋዊና በህገ-ወጥ መንገድ የፓርኪነግ አገልግሎት ለመስጠት ብቻ የተሰሩ ይመስላሉ፡፡ በርካታ ጎሚስታዎችና ጋራዦችም ስራቸውን በተቀላጠፈ መንገድ የሚያከናውኑት በእነዚህ በከፍተኛ ወጪ በተገነቡ   አስፋልት መንገዶች ላይ ነው፡፡ አንዳንዱ መንገድ ላይማ በግራም በቀኝም መኪኖች ተኮልኩለው ቆመው ታክሲዎችም ሆኑ የአደጋ ጊዜ አምቡላንሶች በስቃይ ጩኸት እየታገሉ የእንፉቅቅ ርጀም ጊዜ ፈጅቶባቸው እንደሚያልፉ አላየንም ብሎ ሊክድ የሚችል ነዋሪ አይገኝም፡፡ እነዚህን ቁጭቶች በገንዘብ ስሌት ቀይረን ብናያቸው ነገሩን የተሸለግልፅ የሚያደርገው ይመስለኛል፡፡ ….... ለምሳሌ አንዲት ኮብል ንጣፍ መንገድ ዳር የሚቆምን አነስተኛ ርዝማኔ ያለው ተሸከርካሪ ምን ያህል ገንዘብ ላይ ቆሞ እንደሚውል እናስላ፡፡ ...