Skip to main content

Posts

Showing posts from 2022

ሰላም

ያቺ ጀግና እናቴ ስምንት ወንዶች ወልዳ፤ የሚጦራት አጣች፣ ረሃብ አንገላታት፣ ቁሩ ቀጭቶ አድምቶ፣ ማቅ አልባሷን ዘልቆ፣ እንዳልሆነ ሆነች፡፡   ያቺ ጀግና እናቴ ስምንት ወንዶች ወልዳ፤ ሁሉን ለጦር ማግዳ፤ በጉያዋ እሳት፣ እራሷን አንድዳ፣ በንዋየ ፍቅር፣ በስካረ ምንዳ፡፡   አይ እምይ እናቴ፤ ትረፊ ለሕይወቴ፤ ምንሽም መድሀኒት ነው፣ ይሽተተኝ በሞቴ፡፡   እንዳላገጡብን፣ እንደተላገዱ፤ እነርሱው ቆምረው፣ እነርሱው ሲሰጉ፤ ከጉጭን ወጥተው፣ ጎናችን ሲወጉ፤ ቀጠናውን አልፈው፣ አለምን ሲያሰጉ፤ ስንቀለብሰው፣ ጦርነቱን ባንዴ፤ መደቆሳቸውን፣ አምነው ዋጡት እንዴ ?   አይ እምይ እናቴ፤ በእኛ እና በእነሱ፤ በአበረ እና አበሩ፤ ሽምቅና ክተት፤ መፍረስና አንድነት፤ በአንድነት ልዩነት፤ በሕበረብሔር ዜማ፤ ምናምን እያልን፤ ስምንቱም ልጆችሽ እየተዋደድን፤ እየተቋሰልን፤ እየተዋደቅን፤ ስርዝ ድልዝ ታሪክ፣ ቅርስ እንገነባለን፡፡ ተረኛ እስኪያፈርሰው፣ ዛሬም እንሰራለን፡፡   አንቺ ጀግና እናቴ፣ ስምንት ጊዜ ያማጥሽው፤ ታምር ሚስጥራቱን በማህፀን አዝለሽ፣ በእንግዴ ልጅ ስበብ፣ ቀብረሽ የሸሸግሽው፤ እስኪ አፍሽን ክፈች፣ ተናገሪው ይውጣ፤ እህህ እና እዬዬሽ፣ በንግግር ይንቃ፤ በውይይት ይድቃ፤ ነጠላ መዘቅዘቅ፣ ፊት መንጨትሽ ይብቃ፡፡   እምዬ እናት አለም ማህፀነ ለምለም፤ ከአረንጓዴው በቀር፣ ትዝ የሚለን የለም፤ ብለን እናውጋቸው ለልጅ ልጅ ልጆችሽ፤ ከእርግማኑ ያምልጡ ተባርከው በእጆሽ፡፡   አንቺ ጀግና እናቴ፣ ስምንት የወለድሽው፤ ስምን...