Skip to main content

ሰላም

ያቺ ጀግና እናቴ ስምንት ወንዶች ወልዳ፤

የሚጦራት አጣች፣

ረሃብ አንገላታት፣

ቁሩ ቀጭቶ አድምቶ፣

ማቅ አልባሷን ዘልቆ፣

እንዳልሆነ ሆነች፡፡

 

ያቺ ጀግና እናቴ ስምንት ወንዶች ወልዳ፤

ሁሉን ለጦር ማግዳ፤

በጉያዋ እሳት፣

እራሷን አንድዳ፣

በንዋየ ፍቅር፣ በስካረ ምንዳ፡፡

 

አይ እምይ እናቴ፤

ትረፊ ለሕይወቴ፤

ምንሽም መድሀኒት ነው፣

ይሽተተኝ በሞቴ፡፡

 

እንዳላገጡብን፣ እንደተላገዱ፤

እነርሱው ቆምረው፣

እነርሱው ሲሰጉ፤

ከጉጭን ወጥተው፣ ጎናችን ሲወጉ፤

ቀጠናውን አልፈው፣ አለምን ሲያሰጉ፤

ስንቀለብሰው፣ ጦርነቱን ባንዴ፤

መደቆሳቸውን፣ አምነው ዋጡት እንዴ?

 

አይ እምይ እናቴ፤

በእኛ እና በእነሱ፤

በአበረ እና አበሩ፤

ሽምቅና ክተት፤

መፍረስና አንድነት፤

በአንድነት ልዩነት፤

በሕበረብሔር ዜማ፤

ምናምን እያልን፤

ስምንቱም ልጆችሽ እየተዋደድን፤

እየተቋሰልን፤

እየተዋደቅን፤

ስርዝ ድልዝ ታሪክ፣

ቅርስ እንገነባለን፡፡

ተረኛ እስኪያፈርሰው፣ ዛሬም እንሰራለን፡፡

 

አንቺ ጀግና እናቴ፣ ስምንት ጊዜ ያማጥሽው፤

ታምር ሚስጥራቱን በማህፀን አዝለሽ፣

በእንግዴ ልጅ ስበብ፣

ቀብረሽ የሸሸግሽው፤

እስኪ አፍሽን ክፈች፣

ተናገሪው ይውጣ፤

እህህ እና እዬዬሽ፣

በንግግር ይንቃ፤

በውይይት ይድቃ፤

ነጠላ መዘቅዘቅ፣

ፊት መንጨትሽ ይብቃ፡፡

 

እምዬ እናት አለም ማህፀነ ለምለም፤

ከአረንጓዴው በቀር፣

ትዝ የሚለን የለም፤

ብለን እናውጋቸው ለልጅ ልጅ ልጆችሽ፤

ከእርግማኑ ያምልጡ ተባርከው በእጆሽ፡፡

 

አንቺ ጀግና እናቴ፣

ስምንት የወለድሽው፤

ስምንት የቀበርሽው፤

ስምንት ሺህ ሰላም ይወለድ በቤትሽ፤

ይለምልም፣ ይባረክ፣ ያፍራ ማህፀንሽ፡፡

 

ፀና ነጋሽ ታህሳስ 30/2014 ዓም.

Comments

Popular posts from this blog

የወሲብ ግፍና ዘመን

(This post had been on my other blog since April 04,2013. Please consider the original post date while reading.) ዘመነ ወሲብ ዛሬ ዛሬ መቼም ትዳር የሚባለው ጎጆ የጋብቻ   ምሰጢር ያለበት አልመስል ብሏል፡፡ በአፀያፊ መልኩ ዎንዶችና ሴቶች ገና ጨቅላ በሚባል የጉልምስና (በዘመንኛው ቃል የፍንዳታ እድሜ ይሉታል፡፡) እድሜያቸው ወሲብ መጀመራቸውና በአስራዎቹ አጋማሽ ላይ ሲደርሱ ዓለም ሰየጠንሁ  ያለበትን የወሲብ ክህሎት ጣራ ነክተው ከዚያ ሲዳክሩ ይከረሙና በወላጅ ይሁን በኑሮ ግፊት ትዳር ይመሰርታሉ፡፡ የዚህ አዲስ አይነት ጎጆ አባላት ደግሞ በአብዛኛው የሚያስቁ ጥነዶች የሆናሉ፡፡ እነዲህ ያለው ትዳር የተመሰረተው ለገንዘብ ወይም ለውጭ ሀገር ዕድል ከሆነ፤ ተጋቢዎቹም ሆነ ገገባው ሩቅ ሳይሄድ ህጋዊ ፍች እንደሚፈፀምበት ገና የሰርጉ እለት ያውቁታል፡፡ በቤተሰብ ግፊትና በአብሮ አበዶች ሆይሆይታ የሚቀለስም ተመሳሳይ ጎጆ አለ፡፡ ብቻ ይህኛውም መቼ  እነደሚሆን አይታወቅም እንጂ ላይዘልቅ እንደሚችል ተጋቢዎቹም ሆኑ እኛ ስለጋብቻው አሁን የሰማን ሰዎች ከልምዳችን በመነሳት እርግጠኞች መሆን ንችላለን፡፡ የሆኖሆኖ የዛሬ ትዳር ምነም እክሎችን የያዘ እነደሆነ ላሰታውሳችሁ፡፡ ውሽምና ድጋፍ ባያገኝም አስከዚህኛው ትውልድ በመዝለቁ፤ ወደሽርሙጥና  እና  የዳማ በሚል ስያሜ በቡድን ለሚፈፀም ሰው ሰራሽ አረመኔያዊ ወሲብነት አድጓ፡፡ ጥነዶች በአንድ ጣራ ስር ሆነው እንኳ በተመሳሳይ ሰዓት ከተለያዩ ሰዎች ጋር በስልክ ወሲብ ራሳቸውን ያረካሉ፡፡ የነውሩ ዘመን   በአባቶቻችንና ከዚያ ቀደም ባለው ትውልድ ወሲብ በይፋ በየመንገዱ እንደልብ የሚወሳ ሳይሆን እንደነውር ...

Hino da Etiópia (voz) Ethiopia National Anthem (vocal) (source: http://s.ytimg.com)

የሷ ሱስ

የወደዷትን ልጅ እያወዳደሱ እያሞጋገሱ እንዲህ እያስደነሱ፤ ልፍታ ልተው ቢሏት እንኳንስ ፍቅሯና አይለቅህም ሱሱ! tsenawoo