Skip to main content

Posts

Showing posts from November, 2013

ፍቅር በአርጩሜ!

ያኔ ትምህርት ቤት ቀለሙን ስንቀልም፣ ስሌት ስናሰላ ሰይንስ ስንጠበብ፣ አይናችን ሲገለጥ ሁሉን ስንካን፣ ፍቅርን ዝም አሉን የኛ መምህር፡፡ ትዝ ይለኛል ያኔ.... የክፍሌ ተማሪ ፍቅር ብታሲዘኝ፣ አይናፋርነጸቷ ዝምታዋ ቢያመኝ፣ ፍቅረሯ አያማለለ መማሩ ቢሳነኝ፣ ትዝ ይለኛል ያኔ.... ቃላት አውጣጥቼ ደብዳቤ መፃፌ፣ ባማሩ ቃላቶች ወደድኩሽ ማለቴ፤ ግና ምን ይሆናል.... ወድጃለሁ ብዬ ሃሳቤን በገለፅኩ፣ እሰልፉ መሃል ላይ ባርጩሜ ተገረፍኩ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... እንደወንጀለኛ ፍርድ እንዳጎደለ፣ ማፍቀሬ ተወራ ጉድ እየተባለ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... የአርጩሜው መዘዝ ስር አየሰደደ፣ ፍቅር በአርጩሜ ከኔ ተዋሀደ፡፡ ይመስገነው ዛሬ ሴትን አልጠይቅም፣ የማፍቀሩን ፀጋ ነፃነት አላውቅም፣ ሰጠየቅ እሺ እንጂ እኔ አልጠይቅም፡፡ እኔ!?.... ምን በወጣኝ! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... በስመአብ!! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... እማማ ትሙት - እኔ አልጠይቅም፡፡ 1981 ዓ.ም. — ናዝሬት በመስፍን ገብሬ ወንዳፍራሽ (ቅንጣት 2005 ዓ.ም.)

Model School 'Literature day' launched yesterday

On a recital of Artist Wogayehu Nigatu, the well known actor who made the Haddis Alemayehu 'Fikir Eskemekabir' live in the minds of all Ethiopian nationalists; mind it was on the date he was buried, Hidar 05, 19___; Mesfin Gebre has started a new literature stage where many young Ethiopian would learn to care for their art work. Mesfin Gebre, on his way to publicize his Poetry; 'Kintat', an Amharic poem book meaning a drop or fine,  has held an open day of the literature day in Adama/ Nazareth town. School of sadan has provided a regular stage to be hold every Thursday, 10:30-1:00 am, Ethiopian time.

'My nationality'

™û|Âá¿­Œ{...............( ፪ ) አደባባይ ቆሜ አላፊ አግዳሚ ሳይ ወሬ ጠኔ ይዞኝ ሟች ባገኝ ወይ ገዳይ፣ ወገን ባህር ማዶ ሲሰቃይ ‘ሰማለሁ እዚህ ለሆድ ቁርጠት፣ሲባትል አያለሁ ጉሮሮዬን ትቼ እኔ አገር እጠርጋለሁ የት እንዳለሁ ማወቅ ማመን ፈልጌያለሁ “ እህህ “ እሚል ባገኝ “ ለምን “ ልል ዝያለሁ ኮምቡጦር ስር ሆኜ በ “ ኢ “ ፣ በ “ ት “ ፣ በ “ ዮ “ …እጎለጉላለሁ፤፤ ወገኔን ታዘብኩት ላሯሯጠው ሲሮጥ አቅሉን እንደሳተ ህሊናው ሲናወጥ ሁሉን ሆዱ እስኪፈጅ ሁሉንም ተውኩለት፤ ይልቅ ጨከንኩና… ወሬ መፍጠር ባይችል እኔ ልፈጥርለት እሱ የራቀውን ኮረንቲ ያዝኩለት ራሴን በራሴ በእሳት ለኮስኩለት ለካስ በርዶት ኖሮ ተሰብስቦ ሞቆኝ ወሬዬን ኮምኩሞ እሳቴን አዳፍኖ፣ከነመፈጠሬ-ከነሞቴም ረሳኝ “ ኢትዮጵያዊነቴ “ ፣ የዚያን ጊዜ ገባኝ ከዚያች ቀን ጀምሮ ዜግነትም የለኝ ማነው ምፀተኛ የኔ ሰው የሚለኝ በሞቴ ሞቼለት በቁም ያልገደለኝ፡፡ (ለሰማዕቱ መምህር የኔሰው ገብሬ እና በሳዑዲ ፖሊሶች ለተገደሉ ሃበሾች፡፡) ©ተስፋዬ ዋ.2006 ዓ/ም                     ethopianwoo.blogspot.com