™û|Âá¿Œ{...............(
፪ )
አደባባይ
ቆሜ አላፊ አግዳሚ ሳይ
ወሬ
ጠኔ ይዞኝ ሟች ባገኝ ወይ ገዳይ፣
ወገን
ባህር ማዶ ሲሰቃይ ‘ሰማለሁ
እዚህ
ለሆድ ቁርጠት፣ሲባትል አያለሁ
ጉሮሮዬን
ትቼ እኔ አገር እጠርጋለሁ
የት
እንዳለሁ ማወቅ ማመን ፈልጌያለሁ
“እህህ“ እሚል ባገኝ “ለምን“ ልል ዝያለሁ
ኮምቡጦር
ስር ሆኜ በ“ኢ“፣
በ“ት“፣
በ “ዮ“…እጎለጉላለሁ፤፤
ወገኔን
ታዘብኩት ላሯሯጠው ሲሮጥ
አቅሉን
እንደሳተ ህሊናው ሲናወጥ
ሁሉን
ሆዱ እስኪፈጅ ሁሉንም ተውኩለት፤
ይልቅ
ጨከንኩና…
ወሬ
መፍጠር ባይችል እኔ ልፈጥርለት
እሱ
የራቀውን ኮረንቲ ያዝኩለት
ራሴን
በራሴ በእሳት ለኮስኩለት
ለካስ
በርዶት ኖሮ ተሰብስቦ ሞቆኝ
ወሬዬን
ኮምኩሞ እሳቴን አዳፍኖ፣ከነመፈጠሬ-ከነሞቴም ረሳኝ
“ኢትዮጵያዊነቴ“፣ የዚያን ጊዜ ገባኝ
ከዚያች
ቀን ጀምሮ ዜግነትም የለኝ
ማነው
ምፀተኛ የኔ ሰው የሚለኝ
በሞቴ
ሞቼለት በቁም ያልገደለኝ፡፡
(ለሰማዕቱ መምህር የኔሰው ገብሬ እና በሳዑዲ
ፖሊሶች ለተገደሉ ሃበሾች፡፡)
©ተስፋዬ
ዋ.2006 ዓ/ም
ethopianwoo.blogspot.com
Comments
Post a Comment