Skip to main content

ናዝሬትዬ መሪዎችሽ ለምን ይፈሩሻል?

https://www.facebook.com/twaktola
ናዝሬትዬ መሪዎችሽ ለምን ይፈሩሻል?
ድሮም ጃንሆይ ናዛሬት/አዳማ መምጣት አይወዱም ነበር፣ይባላል፡፡በዚህም የተነሳ ለገላውዴዎስ ት/ቤት መሰረትና ምርቃት ከመምጣታቸው ውጪ ሌላ ጊዜ መች እንደመጡ ሲነገርም አልሰማሁም፡፡መንጌም ሲመጣ በጣም ተደብቆና በድንገት ሲሆን ፣የማስታውሰው ለናዝሬት ቴክኒክ ኮሌጅ (የዛሬው አዳማ ዩኒቨርሲቲ) መሰረትና ምርቃት መምጣቱን ነው፡፡ከዚያ በተረፈ ሁለቱም መሪዎች ወደ ሶደሬ ሲያልፉ ረዥም እድሜ ተመኙ ተብሎ ሕፃናት ወጥተን ቪቫ (VIVA JANHOY! …viva mengistu!..)ብለን እንገባ ነበር፡፡ያኔም ድንገት ካየናቸው ደስታችን ወሰን የለውም ነበር፡፡የልጅ ነገር!ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እጫወት ነበር …ያለው ማነው?
ታዲያ ፍርሃት የተጋባበት መሌም ናዝሬት መጣ ከተባለ ከተማው በፌደራል ይወረራል፡፡ከዚያ የት እንዳደረ ሳይታወቅ ወይ ምሽቱን ሄዷል ወይ …አድሯል፡፡ካደረ ጎብዟል፡፡ግን መሌ ሶደሬ ሄዶ ያውቃል?….ቢዚ ስለነበር ምስኪን፣….
ግን ግን-ሶስቱም መሪዎችሽ ለምንፈሩሽ- ---እውነት ግን አዳማ/ናዝሬትን ለምን ፈሯት…?
እስቲ እኔ ልገምት፡፡
ጊዜው በጣም ሩቅ ነው ይባላል፡፡ዓጼ ገላውዴዎስ ከግራኝ ጋር ጦርነት ገጥመዋል፡፡ጦርነቱ ተፋፍሞ ዓጼው ብዙ ከገፉ በኋላ ግራኝ ጦሩን አስተባብሮ እየገፋ ይመጣል፡፡ይሄኔ ላለመማረክ ሲዋጉ የነበሩት ንጉስ በስተመጨረሻ ይቆስላሉ በኋላም አሁን ካለው ከዓጼ ገላውዴዎስ ከፍ ብሎ ካለው ከአለሌ ወንዝ ማዶ ባለ ቦታ ተገድለው ተገኙ፡፡በኋላም ግራኝ አንገታቸውን ቆርጦ ወደ ሃረር ወስዶ በግንቡ ላ ሰቀለው የሚል ዲስኩር በገላውዴዎስ ት/ቤት ግቢ ውስጥ በ 50ኛ ዓመት የት/ቤቱ በዓል ላይ ከታወቁ የከተማው ያገር ሽማግሌ ሰምቻለኁ፡፡እንግዲህ የኔ ግምት ከዚህ ንግግር ጋር ይያዛል፡፡
ደም የለመደ አስፋልት ፣ደም የለመደ ሜዳ፣ደም የለመደ…እየተባለ ሲስፈራራ መቼም ሳትሰሙ አትቀሩም ፡፡ እንግዲህ የተራ ሰዎቹ ሳያሆን የታላላቅ መሪዎቻችን የአዳማ ሆነ የናዝሬት ፍርሃት ከዚህ የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡ካልሆነ ከምን ሊሆን ይችላል;…ነው ወይስ ከጥላቻ;….በእርግጥ ናዝሬቶች በጋራ በተከበበች ከተማችን የማይበጀንን መውጫ ማሳጣቱን እናውቅበታለን፡፡ካልሆነ እርም ብሎ ይወጣታል እንጂ በቀላሉ አንለቀውም፡፡ለዚህም ይሆናል በጥቂት አመታት ውስጥ ብቻ ከ14 በላ ይ ከንቲባ ሲመጣና ሲባረር የታየባት፡፡አይመቹንም እኛም አንመቻቸውም ፡፡ታዲያ እኮ ምናለ ቢተውን !...አሊያም የራሳችንነ ከንቲባ ራሳችን እንድንመርጥ ነፃነታችንን ቢመልሱልን፡፡
በመጨረሻ አንድ ቀልድ ቢጤ ልንገራችሁ፡፡
ሙስና የማይቀበል ከንቲባ መጣላት ተባለና 6 ወር ሙሉ ተወራ፡፡ያ ሰው የ6ወር ሪፖርት በግልፅ ሊያሰማና ከህዝቡ አስተያየት ሊሰበስብ በተንጣለለው የኦሊያድ አዳራሽ ኅዝቡን ያወያያል፡፡በከተማው ስላለው ጃንሆይ ስላሰሩት ሆስፒታል እየተወራ ነው፡፡እሱ የአዳማ ሆስፒታል እያለ ያትታል፡፡ ህዝቡ ደሞ የኀይለ ማርያም ማሞ ሆ/ል እያለ ችግሩን ይገልፃል፡፡በኋላ ሰብሳቢው አዲሱ ከንቲባ ግራ እንደተጋባ በሚገልጽ ሁኔታ ሆኖ ሲቆጣ ማዳመጥ ጀመረ፡፡ “አንዴ ቆይ እስቲ እኔ የማወራው እኮ ስለ አዳማ ሆ/ል ነው የትኛወ ነው ኀይለማርያም ማሞ ሆ/ል”?.. ብሎ ቁጭ!.....የተሰበሰበው ሕዝብ ሳቀበት፡፡በሆታም የቀድሞ ስሙ ኃይለ-ማሪያም ማሞ መሆኑን ሕዝቡ ነገረው፡፡
ይህ ሰው ማ መሰላችሁ?>>>፣በቅርቡ በታማኝነቱ በፈንጂ ወረዳ ላይ የተመደበው -መላኩ ፈንታን ቀይሮ በግራ ተመላላሽ መስመር ላይ በአጥቂነት የሚጫወተው በከር ሻሌ ነው፡፡አሪፍ ነበር ይላሉ ፣አንዳንድ የአዳማ ነዋሪዎች በቁጭት፡፡ሳንጠቀምብት ተነጠቅን !... አንዳንዶች ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት ሰውዬውን ለማስመለስ ሰልፍ ቢጤ የጠየቁ ሰዎች በመሃል አዳማ በየቀኑ በህቡዕ ፖሰታ ቤት አካባቢ ፈረንጆቹ ሲት ኢን(sit-in) የሚሉትን የሰላማዊ ተቃውሞ እያደረጉ መሆኑን ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ሰዎቹ ከንቲባችን ካልተመለሰ አንነሳም ድዳችንን ማስጣት ማንም አይከለክለንም-በገዛ ድድ ማስጫችን ማን ይከለክለናል ብለዋል፣ብለው ሲያወሩ ሰምቻለሁ ብሎ ነግሮኛል፡፡ካላመናችሁ ፖስታ ቤት አካባቢ ሂዱና እዩ…በዕርግጥ መፈክር አይዙም…በህቡዕ የሚደረግ ሰልፍ ነዋ…አችሉም እንዴ!
ናዝሬትዬ አትፍሩኝ በያቸው በናትሽ፣ግፋ ቢል ቀጨማ ነው!.....ግፋ ቢል አዱላላ ነው!.....ግፋ ቢል ሙክዬ ነው!...እነሆ አሁን ደግሞ መሪዎቿ በሚፈሯት ኣደማ/ናዘሬት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፅ/ቤትን ለመክፈት ተቸግረናል፡፡አንድነቶችጰዋጉሜ 3/2005ዓ/ም ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ አስፈሪነታቸውን አሳዩ መሰለኝ ይኸው ዳፋው ለኛ ደረስን፡፡እሺ ከፍርኃት ሚገላግል ምን ይምጣ….አሃ!...ለምን እኛም እዛ ድድ ማስጫላይ ሲት ኢን አናደርግም….በቃ አደባባዩ ላይ እንገናኝ፡፡አደባባይ ማከራየት ተጀምሮ ይሆንደሞ እንዴ… ተከራይተንም ቢሆን ድምፃችንን ማሰማታችን አይቀርም፡፡
ተገናኘን ፡፡እንበርታ አቦ!

Comments

Popular posts from this blog

Hino da Etiópia (voz) Ethiopia National Anthem (vocal) (source: http://s.ytimg.com)

The man who taught Mandela to be a soldier

       The man who taught Mandela to be a soldier By Penny Dale BBC Africa, Addis Ababa In July 1962, Col Fekadu Wakene taught South African political activist Nelson Mandela the tricks of guerrilla warfare - including how to plant explosives before slipping quietly away into the night. Mr Mandela was in Ethiopia, learning how to be the commander-in-chief of Umkhonto we Sizwe - the armed wing of the African National Congress (ANC). The group had announced its arrival at the end of 1961 by blowing-up electricity pylons in various places in South Africa. Then on 11 January 1962, Mr Mandela had secretly, and illegally, slipped out of South Africa. His mission was to meet as many African political leaders as possible and garner assistance for the ANC, including money and training for its military wing. And to be moulded into a soldier himself. During this trip, he visited Ethiopia twice and left a deep impression on those who met ...

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የ...