Skip to main content

Posts

Showing posts from December 14, 2013

ሲሞት ያልገደለን…

ሲሞት ያልገደለን… ሞቱን የገደለ አንድ ሰው ተገኘ ጭቆናን ረግጦ በልዕልና የናኘ ሲታሰር ያስፈታ ሲለቀቅ የፈታ ሲሞት ያልገደለ ሲነሳ ይበረታ! ይልክልን ይሆን መንፈሱን መፅናኛ እምነቱን ፅናቱን ትዕግስቱን ስለእኛ አይጠረጠርም-ዛሬም ትላንትና መንፈሱ አብሮን አለ ሲያጀግን- ሲያፅናና የሮቢን ባህታዊ - እነሱ እነደሚሉን- የጥቁር ሰብዓዊ አካልን መንፈስን በአንድ አስተባብሮ ነፃነት ያወጀ በህገ-ተፈጥሮ ከኢየሱስ ቀጥሎ ሚስጥር የነገረን እውነትን በተግባር ቀምሶ ያስተማረን ማንዴላ ሕያው ነው በመኖሩ ያኖረን - ሲሞት ያልገደለን፡፡ - ተስፋዬ ዋቅቶላ - 27/03/2006 ዓ/ም - ናዝሬት-ኢትዮጵያ