Skip to main content

Posts

Showing posts from June 27, 2014

ፖለቲኳስ ቢሆን...!

                                                                                                                                      19/10/2006 ኳስ ክብ መሆኗ ብቻ ለአለም መነጋገሪያ አላደረጋትም፡፡ በእግር መለወሷም ከቶ አላስናቃትም፡፡ ብዙ ሚሊዮኖችን ታስፈነጥዛለች፤ ብዙ ሚሊዮኖችን ታስመነዝራለች፤ ለብዙ ሚሊዮኖች የስራ እድል ፈጥራ እንጀራ ታበላለች፡፡ ሊያውም “fair play” የሚል የሚዛንን አድልዎ የሚኮንን መፈክር አንግባ! ይልቁንም አለሙን ሁሉ በአንድ ቋንቋ ታዘምራለች፡፡ የግል ብቃትና ልዩ ክህሎት፣የቡድን ስራ እና ቁርጠኛ አመራር፣ የላቀ አፈፃፀም ያለውን ጠንካራ ቡድን ይመሰርታሉ፡፡ ምግብ፣ አልባስ፣ እና መጠለያ፤ የጤና ባለሙያ፣ የስነልቦና አማካሪ፣ ወኔ ወስቃሽ እና ሌሎች ሁሉ ስለ ቡድኑ ውጤት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እረገው በሚመዘገበው ድል ይረካሉ፣ ይቦርቃሉ፡፡ እንኳንና እነሱ ደጋፊዎች በሩቅ ሆነው እርሳቸውን እስኪስቱ   ይደሰታሉ፤ ስለ ድሉ ይዘምራሉ፤ በየቅፅበቱ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ሁሉ በጉጉት ይወራጫሉ፤ በቁጭት ይንገበገባሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን   ኳስ ገደብ ስላላት፣ እንዲሁም የተጫዋች ቅያሬ ልክ፤ የመለዮ ልብስ አግባብ፤ የግብ ሁኔታ፤ የመከላከልና የአፀፋ ምላሽ፤ ዝላይ፣ መንሸራተት፣ የእጅ ጣልቃ ገብነት፤ የማንቂያ ደውል(ፊሽካ፤) … ብቻ ሁሉም ገደብ አለው፡፡ እነዚህ ገደቦቸች ቢጣሱ የሚያስከትሉት ቅጣት አለ፡፡ ገደቦቹም ሆነ ቅጣቶቹ ለሕዝብ በማያሻማ መልኩ ይቀመጣሉ፡፡ በየደረጃውም በሰፈር ጨዋታዎች ሳይቀሩ ይተገበራሉየበላይ    ጠባቂም አላቸው፡፡ እነርሱም የሚየሻሙ ነጥቦችን ከዘመኑ ጋር እየዘመነ በሚሄደው ቴክኖሎጂ ሳይቀር እየታገዙ