Skip to main content

Posts

Showing posts from February 4, 2014

የ “ ‘ይድረስ’…” ይድረስ

  “ይድረስ ለክቡር ወንድሜ ፣………………………………… ከምንጨፈን እንደ እቡይ፣ከምንጫረስ እንደ እኩይ የነገው ትውልድ በፍርድ ሳይመድበን ከዘር ድውይ እባከህ ሳይጨልምብን አዲስ ራ ዕይ አብረን እንይ፡፡” ብላቴን ጌታ (ሎሬት) ፀጋዬ ገብረ መድህን ቀዌሳ (1928   --1998ዓ/ም) የትሁቱንና የቁጡውን ፣የምስኪኑንና የሐቀኛውን የዋሁንና የረቂቁን፣የተስፈኛውንና የጨለምተኛውን ፣የኢትዮጲያዊውንና የአፍሪካዊውን - ታላቂቱንም ታናሺቱንም ነፍሱን ጥቂት ደቂቃዎች ሰጥተን - የዝንተ - ዓለም ትዝብትና ሂሷን ፣ናፍቆትና - ፍቅሯን፣ለሰው ልጆች በተለይ ለኢትጲያውያን የሚቻልና የማይቻል ህልሟን በጥሞና እንቃኛት - በአራት ስንኞቹ ውስጥ፡፡        በአንዳንድ የሰለጠኑና ጥንታውያን ሃገሮች ዘንድ በተለይም ለያዥ-ለገናዥ ያስቸገረ ሃገራዊ ጉዳይ ሲገጥም ከምንም በላይ የዕውቅ ባለቅኔዎቻቸውን ጥልቅ ዕታና ምኪር መዋስ የተለመደ ክቡር ተግባር ነው፡፡ግሪኮች የሆሜርን ቅኔ ዘሬ ድረስ መረምራሉ፤፡፡ እንግሊዞች በተለይ ለባለቅኔዎቻቸው ልዩ ክብር ሰጥተው “popular philosophers”-ስመ-ጥር ፈላስፎቻችን ሲሉ ያሞካሻቸዋል፡፡ አሜሪካኖችም በቀውቲ ሰዓት የሚያማክሩት ዋልት ዊትማን የተባለ ገጣሚ ነበራቸው፡፡እኛስ…        ይድረስ ለክቡር ወንድሜ …..የሚል ባለቅኔ አለን- አይዞን ፡፡ታላቁ ባለቅኔህ -አንተን ወገኑን በነፍሱ እሪታጭምር አክብሮ የንፈሲቱን ህመም ሲያማክርህ መኖሩን አትዘንጋ-ይድረስ ለክቡር ወንድሜ እያለ እያከበረ፡፡እኔም በእሱ ፈለግ እቀጥል ዘንድ ግድ ይለኛል፡፡    ክቡር ወንድሜ፡-    ኢትዮጲያ እናትህ ፣ሚሽትህ ፣ሴት ልጅህ ፣በታሪካዊ ጠላቶቹዋ ዱላ አቀባይነት፣በራ