ትንፋሽ አሳጥቶ
በርሃብ ቀጥቶ
ጉልበቷ እስከሚዝል
በዝቶብኛል ሳትል
ተራራ ሜዳውን
ማንም የሚነዳት
አንዱ ሲጋልባት
ሌላው የሚጭናት
ሃገሬ አህያ ናት!
ክብሯ የትም ወድቆ
መብቷ ተንቆ
ጅራፍና ዱላው ሲፈራረቁባት
ነይ ወደዚህ ሲሏት
ሂጅ ወደዚያ ሲሏት
ሃገሬ የእኔ እናት
የመሪዎች ሸክም ወገቧን አጉብጧት
እንደማሽላ አራ ደግሞም እየሳቀች
በርሃብ ቀጥቶ
ጉልበቷ እስከሚዝል
በዝቶብኛል ሳትል
ተራራ ሜዳውን
ማንም የሚነዳት
አንዱ ሲጋልባት
ሌላው የሚጭናት
ሃገሬ አህያ ናት!
ክብሯ የትም ወድቆ
መብቷ ተንቆ
ጅራፍና ዱላው ሲፈራረቁባት
ነይ ወደዚህ ሲሏት
ሂጅ ወደዚያ ሲሏት
ሃገሬ የእኔ እናት
የመሪዎች ሸክም ወገቧን አጉብጧት
እንደማሽላ አራ ደግሞም እየሳቀች
በዘመን ፋርጎ ላይ ዛሬም ትጏዛለች!
Source (የግጥም ምሽት በፌስቡክ)
//በዘሐዲስ አየለ//
Comments
Post a Comment