12/11/2006EC አንድ ሰሞን ወደሁለት ተከፍላ ብዙም ሳትቆይ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው ሱዳን የገጠማትን ምስቅልቅል ሁኔታ ለመከታተል አለም ሁሉ ጆሮውን አቁሞ ነበረ፡፡ ቀድሞም ጠግቦ ያላደረው ደሃ ሕዝብ ነፍሱን ስለማቆየት ሲል ወደጎረቤት ሀገራት ተሰዷል፡፡ በዛ አስቸጋሪ ወቅት ግን አቶ ሳልቫኪየር ከየሀገራቸው እድገትና ስልጣኔ ያልተመጣጠነ ምቾት ስላሰከራቸው አቻዎቻቸው ጉዳይ እንጂ ስለ ሕዝባቸው ፈፅሞ ግድ የሌላቸው እንደሆነ መሰከሩልን፡፡ “የፀጥታውን ስምምነት የፈረምኩት የኢትዮጲያው ጠቅላይ ሚኒሰተር አስርሃለሁ ስላሉኝ ነው”-ብለው አስደመሙን፡፡ ጋዜጠኞቹም ለጉዳዩ መልስ ሲጠባበቁ ቆዩና ሰሞኑን አቶ ኃይለማሪያምን ማብራሪያ ይጠይቋቸዋል፡፡ እርሳቸውም ሳልቫኪየር ቀልዴን ነው ብለዋል ሲሉ መለሱ፡፡ እንዲያውም እነዚህ ጋዜጠኞች ቀልድ አያውቁም ብለው መናገራቸውን ሊያብራሩ ሞክረው አለፉ፡፡ ይህም የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ደረቅ ቀልድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኢቴቪ 1 ፣ 2 ፣ 3 ፣ 4 ተብሎ ይቀለዳል፤ ስለመብራት ስርጭት ብዙ ቁም ነገር የሚመስሉ ቀልዶች እንሰማለን፤ እናያለን፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት ላይ በተጠናከረ መልክ እየሰሩ መሆኑን ይነግሩናል__የቀልዳቸውን፡፡ መንግስት ጸረ - ሰላም ሀይሎች የህዝብን ጥቅም የሚነኩ ኢ - ሰብዐዊ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው ብሎ የቀልዱን ይነግረንና አሴሩ የተባሉትን አሳራቸውን ያበላቸዋል፤ግን የቀልዱን ነው፡፡የሃገሪቷን ሰላም ለማደፍረስ ስለመነሳታቸው መረጃ የለማ ! ቀላል የከተማ ባቡር መጓጓዣን ስራ ለማሰጀመር ሩጫው እየተፋጠነ መሆኑ በተደጋጋሚ በቴሌ...
Comments
Post a Comment