Skip to main content

ፖለቲኳስ ቢሆን...!



                                                                                                                                      19/10/2006
ኳስ ክብ መሆኗ ብቻ ለአለም መነጋገሪያ አላደረጋትም፡፡ በእግር መለወሷም ከቶ አላስናቃትም፡፡ ብዙ ሚሊዮኖችን ታስፈነጥዛለች፤ ብዙ ሚሊዮኖችን ታስመነዝራለች፤ ለብዙ ሚሊዮኖች የስራ እድል ፈጥራ እንጀራ ታበላለች፡፡ ሊያውም “fair play” የሚል የሚዛንን አድልዎ የሚኮንን መፈክር አንግባ! ይልቁንም አለሙን ሁሉ በአንድ ቋንቋ ታዘምራለች፡፡
የግል ብቃትና ልዩ ክህሎት፣የቡድን ስራ እና ቁርጠኛ አመራር፣ የላቀ አፈፃፀም ያለውን ጠንካራ ቡድን ይመሰርታሉ፡፡ ምግብ፣ አልባስ፣ እና መጠለያ፤ የጤና ባለሙያ፣ የስነልቦና አማካሪ፣ ወኔ ወስቃሽ እና ሌሎች ሁሉ ስለ ቡድኑ ውጤት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እረገው በሚመዘገበው ድል ይረካሉ፣ ይቦርቃሉ፡፡ እንኳንና እነሱ ደጋፊዎች በሩቅ ሆነው እርሳቸውን እስኪስቱ  ይደሰታሉ፤ ስለ ድሉ ይዘምራሉ፤ በየቅፅበቱ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ሁሉ በጉጉት ይወራጫሉ፤ በቁጭት ይንገበገባሉ፡፡
ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን  ኳስ ገደብ ስላላት፣ እንዲሁም የተጫዋች ቅያሬ ልክ፤ የመለዮ ልብስ አግባብ፤ የግብ ሁኔታ፤ የመከላከልና የአፀፋ ምላሽ፤ ዝላይ፣ መንሸራተት፣ የእጅ ጣልቃ ገብነት፤ የማንቂያ ደውል(ፊሽካ፤) … ብቻ ሁሉም ገደብ አለው፡፡
እነዚህ ገደቦቸች ቢጣሱ የሚያስከትሉት ቅጣት አለ፡፡ ገደቦቹም ሆነ ቅጣቶቹ ለሕዝብ በማያሻማ መልኩ ይቀመጣሉ፡፡ በየደረጃውም በሰፈር ጨዋታዎች ሳይቀሩ ይተገበራሉየበላይ   ጠባቂም አላቸው፡፡ እነርሱም የሚየሻሙ ነጥቦችን ከዘመኑ ጋር እየዘመነ በሚሄደው ቴክኖሎጂ ሳይቀር እየታገዙ የጨዋታውን ተወዳጅነት በ“fair play” መፈክርነት ለማስቀጠል ይተጉለታል፡፡
የኳስ ሜዳ ነገር እንኳንስ እለት እለት ትኩረት ሰጥቶት ቤተሰብ ለሆነው ይቅርና እንደኛ ባጋጣሚ እግር ሲጥለው ለሚያየው እንኳ በፍቅር ትንፋሽን የሚያስውጥ ወደረኛ መስክ ነው፡፡ እነዲያውም ሀገርን የመነግዛት የፖለቲካ ጨዋታ በኳስ ሜዳ ህግ ቢመራ አያሰኝምና ነው?!
በተንኮል መሰንዘርና ማጥቃት ቢጫ/ቀይ እና የቅጣት ምት ቢያሰስከትሉ፤ ከሚገባው በላይ ሹም ሽረት ለማድረግ አሰልጣኙ ገደብ ቢኖርበት፤ ከመስመር ውጭ በወጣ ኳስ ራስን ለመከላከልም ሆነ ተቀናቃኝን ለማጥቃት እንዳይቻል የመስመር ዳኛው እንደሚጠባበቅ በስልጣን ላይ ያለው ፖለቲከኛ ሀይ ባይ ቢኖረው፤ እንደ “Goal-line” ቴክኖሎጂ የምርጫ ኮሮጆ ላይ እፍረት እንዳይኖር ውጤት መጠበቂያ ቢበጅለት፤ በጉጉት የማጥቃት ውጤት ላይ ላሉት ከጨዋታ ውጪ(off side) ምልክት ቢውለበለብ፤
ጉዳት የደረሰበት ወይም የተበደለ እጁን ከፍ አድርጎ ምልክት የሚሰጠውና አይቶ የሚቨይንለት ጤናማ ዳኛ ቢሰየም፤ በዕድ አካላትን ወይም ተደራቢ የመጫወቻ ኳስን አለያም ህገ-ተላላፊ አሰልጣኝን ከሜዳ የማስወጣት መብት ያለው ዳኛ ቢቆም፤ በትክክል ግብ ላገባው ወይም ለግቡ አስተዋጥዖ የሆነውን ሰው እና እንቅስቃሴ ተመልካች በማያሻማ መልኩ የሚያስችል ማሳያ(Re-play) ቢኖር፤
ቢጫና ቀይ ካርድ አይተው ከሜዳ የተወገዱ ተጫዋቾች ቅጣታቸውን ጨርሰው እነደሚመለሱት በፖለቲካ የቆሰሉና የታሰሩት በግልፅ ህግ ከሆነ ከቅጣት መልስ ቢሰለፉ፤ በጉዳት  ከሜዳ ውጭ ስለሆኑ ተጫዋቾች ሳይወሸከት  ለህዝብ ይፋ ቢሆን፤ … ወዘተ፡፡
አዎ! በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነት ያለው እግር ኳስ ዛሬም በብራዚል የአለም ዋንጫ ፉክክር የሚዮኖችን ልብ እንደሰቀለ ቀጥሏል፡፡ ኳስ ክብ ናትና ነገ ደግሞ በሌላ ስፍራ እንጠብቃታለን፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው በዘጠና ደቂቃ የጊዜ ገደብ የታጠረች በመሆኗ ነው፡፡ የባከነ ሰዓት በአግባብ ይካሳል፡፡ በአንዳች ያለገደብ መንዛዛት የለም፡፡ ይህ የዘጠና ደቂቃ ገደብ ባይኖር  ተጨዋቾች ይደክማሉ፣ ተቀናቃኛቸውን ሮጠው ኳስ ማስጣል ሰረለማይቻላቸው ትግል፣ ግፊያና ጠረባ ያበዛሉ፤ በሜዳ ተዝለፍልፈው የሚወድቁም፣ በዚያው ያሸለቡም አሉ፡፡ ስለዚህ የጊዜ ገደብ መኖሩ የግድ ጠቃሚ ይሆናል፡፡
የኛ ሀገር ስልጣን ግን ገና ብዙ ያልተቀመጡለትና የማይከበሩ ህጎችና ገደቦች አሉት፡፡ ስልጣን ስራ ሳይሆን ትዳር የሆነባቸው አቅም አጥተው ተዝለፍልፈው ስላልወደቁ ብቻ ሰማኒያ እንደመቅደድ አሳፍሯቸው የሙጥኝ ብለውት እየተዝለፈለፉ አንዳንዶችም ጭራሽ በስልጣን ሜዳ ወድቀው ሲሞቱ እያየን ነው፡፡
ዋይ! አለማዊም፤ አፍሪካዊም፤ ኢትዮጲያዊም ባልሆን ፖለቲኳስ እንደግርኳስ በ“fair play” ብትመራ ደስ ይለኝና በነገር ሁሉ መከፋቴ ይቀርልኝ አልነበረምና ነው?!

Comments

Popular posts from this blog

ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም.የግጥም መድብል ....

አስገራሚ ገጠመኞች የተስተዋሉበት የግጥም መድብል ምርቃት ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም. በልዩ ሁኔታ በኢትዮጲያ  ወመዘክር አዳራሽ ተፈፀመ፡፡

ቀልድ ስላለማወቃችን

12/11/2006EC አንድ ሰሞን ወደሁለት ተከፍላ ብዙም ሳትቆይ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው ሱዳን የገጠማትን ምስቅልቅል ሁኔታ ለመከታተል አለም ሁሉ ጆሮውን አቁሞ ነበረ፡፡ ቀድሞም ጠግቦ ያላደረው ደሃ ሕዝብ ነፍሱን ስለማቆየት ሲል ወደጎረቤት ሀገራት ተሰዷል፡፡ በዛ አስቸጋሪ ወቅት ግን አቶ ሳልቫኪየር ከየሀገራቸው እድገትና ስልጣኔ ያልተመጣጠነ ምቾት ስላሰከራቸው አቻዎቻቸው ጉዳይ እንጂ ስለ ሕዝባቸው ፈፅሞ ግድ የሌላቸው እንደሆነ መሰከሩልን፡፡ “የፀጥታውን ስምምነት የፈረምኩት የኢትዮጲያው ጠቅላይ ሚኒሰተር አስርሃለሁ ስላሉኝ ነው”-ብለው አስደመሙን፡፡  ጋዜጠኞቹም ለጉዳዩ መልስ ሲጠባበቁ ቆዩና ሰሞኑን አቶ ኃይለማሪያምን ማብራሪያ ይጠይቋቸዋል፡፡ እርሳቸውም ሳልቫኪየር ቀልዴን ነው ብለዋል ሲሉ መለሱ፡፡ እንዲያውም እነዚህ ጋዜጠኞች ቀልድ አያውቁም ብለው መናገራቸውን ሊያብራሩ ሞክረው አለፉ፡፡ ይህም የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ደረቅ ቀልድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኢቴቪ 1 ፣ 2 ፣ 3 ፣ 4 ተብሎ ይቀለዳል፤ ስለመብራት ስርጭት ብዙ ቁም ነገር የሚመስሉ ቀልዶች እንሰማለን፤ እናያለን፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት ላይ በተጠናከረ መልክ እየሰሩ መሆኑን ይነግሩናል__የቀልዳቸውን፡፡ መንግስት ጸረ - ሰላም ሀይሎች የህዝብን ጥቅም የሚነኩ ኢ - ሰብዐዊ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው ብሎ የቀልዱን ይነግረንና አሴሩ የተባሉትን አሳራቸውን ያበላቸዋል፤ግን የቀልዱን ነው፡፡የሃገሪቷን ሰላም ለማደፍረስ ስለመነሳታቸው መረጃ የለማ ! ቀላል የከተማ ባቡር መጓጓዣን ስራ ለማሰጀመር ሩጫው እየተፋጠነ መሆኑ በተደጋጋሚ በቴሌ...

ናዝሬትዬ መሪዎችሽ ለምን ይፈሩሻል?

Tesfaye Waktola https://www.facebook.com/twaktola Andinet Ada-nazreth ናዝሬትዬ መሪዎችሽ ለምን ይፈሩሻል? ድሮም ጃንሆይ ናዛሬት/አዳማ መምጣት አይወዱም ነበር፣ይባላል፡፡በዚህም የተነሳ ለገላውዴዎስ ት/ቤት መሰረትና ምርቃት ከመምጣታቸው ውጪ ሌላ ጊዜ መች እንደመጡ ሲነገርም አልሰማሁም፡፡መንጌም ሲመጣ በጣም ተደብቆና በድንገት ሲሆን ፣የማስታውሰው ለናዝሬት ቴክኒክ ኮሌጅ (የዛሬው አዳማ ዩኒቨርሲቲ) መሰረትና ምርቃት መምጣቱን ነው፡፡ከዚያ በተረፈ ሁለቱም መሪዎች ወደ ሶደሬ ሲያልፉ ረዥም እድሜ ተመኙ ተብሎ ሕፃናት ወጥተን ቪቫ (VIVA JANHOY! …viva mengistu!..)ብለን እንገባ ነበር፡፡ያኔም ድንገት ካየናቸው ደስታችን ወሰን የለውም ነበር፡፡የልጅ ነገር!ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እጫወት ነበር …ያለው ማነው? ታዲያ ፍርሃት የተጋባበት መሌም ናዝሬት መጣ ከተባለ ከተማው በፌደራል ይወረራል፡፡ከዚያ የት እንዳደረ ሳይታወቅ ወይ ምሽቱን ሄዷል ወይ …አድሯል፡፡ካደረ ጎብዟል፡፡ግን መሌ ሶደሬ ሄዶ ያውቃል?….ቢዚ ስለነበር ምስኪን፣…. ግን ግን-ሶስቱም መሪዎችሽ ለምንፈሩሽ- ---እውነት ግን አዳማ/ናዝሬትን ለምን ፈሯት…? እስቲ እኔ ልገምት፡፡ ጊዜው በጣም ሩቅ ነው ይባላል፡፡ዓጼ ገላውዴዎስ ከግራኝ ጋር ጦርነት ገጥመዋል፡፡ጦርነቱ ተፋፍሞ ዓጼው ብዙ ከገፉ በኋላ ግራኝ ጦሩን አስተባብሮ እየገፋ ይመጣል፡፡ይሄኔ ላለመማረክ ሲዋጉ የነበሩት ንጉስ በስተመጨረሻ ይቆስላሉ በኋላም አሁን ካለው ከዓጼ ገላውዴዎስ ከፍ ብሎ ካለው ከአለሌ ወንዝ ማዶ ባለ ቦታ ተገድለው ተገኙ፡፡በኋላም ግራኝ አንገታቸውን ቆርጦ ወደ ሃረር ወስዶ በግንቡ ላ ሰቀለው የሚል ዲስኩር በገላውዴዎስ ት/ቤት ግቢ ውስጥ በ 50ኛ ...