Skip to main content

የ “ ‘ይድረስ’…” ይድረስ




 
“ይድረስ ለክቡር ወንድሜ ፣…………………………………
ከምንጨፈን እንደ እቡይ፣ከምንጫረስ እንደ እኩይ
የነገው ትውልድ በፍርድ ሳይመድበን ከዘር ድውይ
እባከህ ሳይጨልምብን አዲስ ራዕይ አብረን እንይ፡፡”
ብላቴን ጌታ (ሎሬት)
ፀጋዬ ገብረ መድህን ቀዌሳ
(1928  --1998ዓ/ም)
የትሁቱንና የቁጡውን ፣የምስኪኑንና የሐቀኛውን የዋሁንና የረቂቁን፣የተስፈኛውንና የጨለምተኛውን ፣የኢትዮጲያዊውንና የአፍሪካዊውን -ታላቂቱንም ታናሺቱንም ነፍሱን ጥቂት ደቂቃዎች ሰጥተን -የዝንተ-ዓለም ትዝብትና ሂሷን ፣ናፍቆትና-ፍቅሯን፣ለሰው ልጆች በተለይ ለኢትጲያውያን የሚቻልና የማይቻል ህልሟን በጥሞና እንቃኛት-በአራት ስንኞቹ ውስጥ፡፡
       በአንዳንድ የሰለጠኑና ጥንታውያን ሃገሮች ዘንድ በተለይም ለያዥ-ለገናዥ ያስቸገረ ሃገራዊ ጉዳይ ሲገጥም ከምንም በላይ የዕውቅ ባለቅኔዎቻቸውን ጥልቅ ዕታና ምኪር መዋስ የተለመደ ክቡር ተግባር ነው፡፡ግሪኮች የሆሜርን ቅኔ ዘሬ ድረስ መረምራሉ፤፡፡ እንግሊዞች በተለይ ለባለቅኔዎቻቸው ልዩ ክብር ሰጥተው “popular philosophers”-ስመ-ጥር ፈላስፎቻችን ሲሉ ያሞካሻቸዋል፡፡አሜሪካኖችም በቀውቲ ሰዓት የሚያማክሩት ዋልት ዊትማን የተባለ ገጣሚ ነበራቸው፡፡እኛስ…
       ይድረስ ለክቡር ወንድሜ …..የሚል ባለቅኔ አለን- አይዞን ፡፡ታላቁ ባለቅኔህ -አንተን ወገኑን በነፍሱ እሪታጭምር አክብሮ የንፈሲቱን ህመም ሲያማክርህ መኖሩን አትዘንጋ-ይድረስ ለክቡር ወንድሜ እያለ እያከበረ፡፡እኔም በእሱ ፈለግ እቀጥል ዘንድ ግድ ይለኛል፡፡
   ክቡር ወንድሜ፡-
   ኢትዮጲያ እናትህ ፣ሚሽትህ ፣ሴት ልጅህ ፣በታሪካዊ ጠላቶቹዋ ዱላ አቀባይነት፣በራስ ወዳድ ልጆቹዋ (ብሔሮችዋ) አላዋቂ ሳሚነት፣ሕልውናዋን ና ሉዓላዊ ክብሯን ሸራርፎ የመበታተን አደጋ -ከፊት ለፊትዋ ደቅነዋል፡፡እንግዲህ ይድረስ ለክቡር ወንድሜ የምልህ ሰቀቀኗን ብቻ አይደለም፡፡መላው በእጅህ መሆኑን  ታውቃለህና ፣ለዕለት ጉርስ ስትባክን ስትል ደፋ ቀና ፣ጊዜ ባትሰጣት ቢጣፋ ልቦና፣ብትዘናጋ ወይ ብትዘነጋት፣በባለቅኔው ነፋስ ውስጥ ዕረፍት የለችምና -እሱ የታየውን እኔም ቃኘሁና-እሱ ይድረስ እንዳለህ - እኔም አደራውን ላፀና -እሱ በግጥም እኔ በዝርው ያለውን እንዳለ--የጊዜን ዋቢነት እያጣቀስኩ ላመለክትህ - ልማጸንህ -ከደጅህ ቆሜያለሁ፡፡

     አዎ…ትላንት ባለቅኔው ፡-
ይድረስ ለክቡር ወንድሜ ፣ለምታውቀኝ ለማላውቅህ
…ሲል በዘመናዊነት ካባ ምክኛት፣ ሰው ከዘመዱ መራራቁን በጠቆመበት፣አሊፍ ስነ-ግጥሙ -ለዳር አገሩ ለባላገሩ፣ለገባሩ፣ለስም አይጠሩ ፣ለጭቁኑ ወገኑ፣እንድትቆምለት ተማፅኖሃል፡፡አንተም መላው ቢጠፋህ - ችግሩ ቢያንቅህ ፣ዘመናዊ ትምህርትህን ጥለህ ጫካ ገብተህ፤በከተማ ተዋቅተህ ፤በፍቅሩ ተነድፈህ አይሆኑ ሆነሃል፡፡ፀሃቱን ገፍተህም ከደጅ አድርሰሃል፡፡ለዚህ ገድልህ፣ ክብር ምስጋና ይገባሃል፡፡
   ግና …ዛሬም  ባለቅኔው 
አበቅቴ ውሉን አይስትምና፣
“ይድረስ ለክቡር ወንድሜ ፣ከምንጨፈን እንደ እቡይ…”       (1)ይልሃል፡፡
          ኸረ ለመሆኑ ዕውን እንደ ዕቡይ ፣ራስህን በራስህ ተጨፍነኃል›››;?!ምነው ወንድሜ -ምን ነክቶሃል../?!መታበይ ለማንስ ሲበጅ አይተሃል..;?!መመካት በብሔር ቢሉ በህብረ-ብሔር ፣የትና ከምን ሲያደርስ አይተሃል..?!ትምክህትስ በሐቅ -በእውነት-በአንድዬ እንጂ በማን ተሟልቶ አይተሃል..?!…፡፡በቃ!...የምን ዕቡይነት…?!
           እንግዲህ የዚህ ዘመን ችግርህ ከይህ ይመነጫል፡፡እወቀው፡፡ከትምክህተ-ብሔር፡፡ይህን ባለቅኔው በነፍስ እግር ፈረስ ኳትኖ አግኝቶልሃል፡፡ለዚህም ዘመነኛው ማጣቀሻህን አግኝተሃል፡፡ምን…?! ብሄርን ከሕብረ-ብሔር ባጫረሰው ጦርነት በደም ናአጥንት ላቁጦ በጥላቻ መሮ ተቀርፆ የጨው አምደ ሆኖ ኀውልቱ ባድመ ቆሞልሃል፡፡እንዴት ይዘነጋሃል…?!
          ያቺ ምስኪን እናት ፣ኢትዮጲያ - ድሮም “ወግ ነውና ሲዳሩ ማልቀስ”:- እያለች ታላቂቱን ልጇን -ስትለማመጥ እንዳልኖረች- ከሰላሳ ዓመታት የደም-ሸማ ማጫነት በኋላ፣ “በጄ” ባትል፣ምርጫ ብታጣ፤እኛ “ጎጆ ወጣች” ስንል -እሷ “ራሴን ቻልኩ-ነጻ ወጣሁ“ ብላ የእወቁልኝ  ካርድ አሳተመች፡፡አዋቂውና አላዋቂው እስኪያደናግር ዓለም ጉድ አላቸው፡፡መካሪ የለሽ ቤተሰሪዋም ታበየችና - ቤቷን ባሸዋ ላይ ሰራች፡፡ስለ ችሎታዋም አለም አደነቀላት፡፡ከማህፀን ከወጣችም በኋላ እንደፍየል የወጣችበትን ማህጸን መራገጧን ቀጠለች፡፡ለዚህም ነው ፣ ያ ጠባሳ !...ጉዳኒሳ!...ሐውልታችን ሆኖ የዛሬውን ትውልድ  በሞኞች ጦርነት (“fool’s war”…)-ሲያስጨንቅ-ሲያሰጠነቅቅ-ሲያጠይቀንና ሲያስንቀን ያለው፡፡
       ምን ነክቶን ይሆን ወንድሜ …?!..ለምንስ እውነቱን ማት ተሳነን ?!…ለምንስ ራሳችንን - በራሳችን ተጨፈነን.?!...ለምንስ. እኩይ ሆንን…?!
-ባለቅኔው እኮ -“የተጫረስነው  እኩይ ስለሆንን ነው”- ብሎ በየነብን….እሱማ መች ላለፈችዋ ባድመ ብቻ  …የሰዋሰው አቀማመጡ እንደሚያሳየን ፣ገና  ለወደፊቱ አይሆኑ እንዳንሆን ነው እንጂ ተማፅኖው!
                       “ከምንጨፈን እንደ ዕቡይ ፣ከምንጫረስ እንደ እኩይ”
         ሱ ራሱ ግን -ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ፣የሚታበይበት ፣አሊያም  የሚሞትለት ብሔር የለውም ይሆንና ነው ይሄ ሁሉ የፈሪ ዕሪታ;!...ወይስ ከብሔሩ አፈር -ከላሞቹ ወተት ያልተፈጠረ ባዕድ ሆኖ/…ወይስ የጣሊያን ገረድ ወሽሞ/.-ዘመነኛውሀገር ወዳድ ደራሲ በዓሉ ግርማ በአንድ ድርሰቱ እንደፃፈው፣-“አንዳንዴም ከጣሊያን ገረድ ይታደራል” ፣ይላልና፡፡
         እሱማ  የጀግኖቹ  ሃገር ከምትባለዋ አምቦ ፣ቦዳ-አቦ ከሙላዴ አፈሯ የተፈጠረው ህፃን ጸጋዬ እንደዛሬው በሃገር ከመኩራት አልፈን ፤ሃገር በመቆራረስ ፋሽን-ልክፍት ፣ሽውታውም በሌለበት ፣መሞላቀቁም ባልነበረበት ዘመን ፤ያኔ በባዕድ ቅኝ ገዢ ዘመን-የተወለደባት ሳር ጎጆ ሳትቀር፣ በፋሺስት ፈረሰኛ-ወታደሮች በእሳት እየጋየች ፣የሚያድግበት ታዛ ፍለጋ በየጢሻዋ ሲማቅቅ፣ከእቅፍና እዝል  ሳይወጣ ሲሳቀቅ ጨቅላ ጊዜውን ያሳለፈባት፣የሚቦርቅበት ገላጣ አውድማ ሳይጠፋ ባድማው በሶላቶ አረር በሞላባት ፤በሰቀቀን ያደገባትን ቀዬውንማ ፣ለወግ ማዕረግ የበቃባትን ኢትዮጲያንማ ፤በደንብ የራሱ ስጋያህል ተዋህዷት ኑሯል፡፡መላ ሃገሪቱን ተራሮቹዋን፣ወንዞቹዋን፣ጫካዎቹዋን፣የጦር አውድማዎቿን ፣በረሃዎቿንና ስረጓጉጧን ሳይቀር ከነፍሱ ጋር አዋህዶ ኖሯታል፡፡በብእሩም ዘላለማዊ አድርጓታል፡፡
      ያቺ ጎጆ ወጪዋን ም - በዋና ከተማዋ ማማር ፣ በኮምቢሽታቶዋ መሽቀርቀር፣ትዝታዋን በልቡ ፣በፍቅር አትሞ አስቀምጧታል፡፡እንዳትታለል ሲመክርና ሲያስመክራት ባትሰማውም፤ጎጆዋን ከሰራች በኋላ እንኳን፣በባለቅኔ ነፍሱ የስንኝ ደብዳቤ ፅፎላታል፡፡ተመቸሽ ወይ ኤርትራ ፣እያለ አንጎራጉሮላታል፡፡ፍቅሩን ትዝታውን ገልጾላታል፡፡የስልጣኔዋን ክፋትና የየዋህነት ምክሩን  በሳር በቄጠማው ተለማምኖላታል፡፡
             ሆኖም ለእሷም ሆነ ለሌላው ለመላው ያለውን መላ ፣ከመግለጽ ወደ ኋላ አላለም፡፡እትንፋሱ እስካለች ድረስ ለሃገሩና ለወገኑ ነፍስያውን፣ቀልቡንና ሩሁን አስገዝቷል፡፡ሃሳቡን ፣የደረሰበትን ቀመሩንና የወረሰውን ይትበሃሉን አስተላልፏል፡፡ በተለይም ባለቅኔው በሕይወቱ ማብቂያ ዋዜማ ከፃፋቸውና -ይድረስ- ካላችው ግጥሞቹ ስርወ-ማንነታችንን ከጥልቅ ጥናቱ እፍታ ዘክሯል፡፡ይህ ባንፃሩ፣ለዛሬው የዛር በሽታ ፍቱን መድሃኒት በሆነ ነበር፡፡ “ውሃ ጥሩ ነበርሽ ማን ቢጠጣሽ” -ሆነ እንጂ ነገሩ :: ህጻን እንደምታባብል እናት፣ታላላቁንና ታናናሹን ሳይለይ፣ሃገርን በሉአላዊነት ስለማቆየት ተማጽኗል- የኢትጲዊነትን ረቂቅነት እያስረዳም ፣ከክፉ መዓት እንድንርቅ መክሯል፡፡ሁላችንንም ነጻ ስለሚያወጣን እውነት ሰብኳል፡፡ዳግም የኢትዮጲያዊነት መለዮአችን በአፍሪካዊነት መድመቁን ና ባንጻሩ በጠባብ ብሔረተኝነት መውደቁን አሳውቋል፡፡ሃገርንከማፈራረስ፣ ወገንንከማጫረስ ፣ በጀግኖች አርበኞቹ አባቶቻችን ስም እና መንፈስ አስጠንቅቋል፡፡ይድረስ ለክቡር ወንድሜ እያለ››››
     በተለይ በተለይ ግን ለእኔ ፣ከላይ ካነሳኋተ አራት ስንኝ  በመጨረሻዎቹ  ሁለት ስንኞች-ከነመፍትሄው የሃሳብ ስንዘረታውን ፣ቋጭቶ -የባለቅኔነት ሃገራዊ ግዴታውን ተወጥቶ አሸልቧል ፡፡ያች ነፍሱ ግን ዛሬም ህያው ሆና በቃላቱ ህያውነት  ውስጥ በየልቦናችን ተግ እያለች ፍኖተ-ነፃነትን ታስቃኘናለች፡፡
የኔ ብጤ መንገድ የጠፋው ፣የዘመን ምች ያጠናገረው ገጣሚ ነኝ ባይ መደዴ፣ አዲስ በሚመስል ያረጀ ያፈጀ ፣ህዝብ አጫራሽ ፍልስፍና እንዳይወሰድ፤የባለቅኔው ፍኖት ያሻዋል፡፡በመሆኑም ከሚሊዮን ስንኞቹ ፣ከእድሜ ዘመን ሃቲቱ ፣ይህቺን አራት መስመር (ስንኝ)፣ማላመጥ ፣ማጣጣም ፣ቢልልኝ ዋጥ አድርጊያት መደርጀት የህይወቴ ፍፃሜ ቢሆን በማን ዕድሌ!...
“የነገው ትውልድ በፍርድ ፣ሣይመድበን ከዘር ድውይ
  እባክህ ሣይጨልምብን ፣ አዲስ ራዕይ አብረን እንይ፡፡”
     እባክህ -ይልሃል  ጎምቱው ባለቅኔ፡፡አዲስ ራዕይ እንይ-ይልሃል፡፡ሃገር ፈራርሳ ፣ዘር በዘር ላይ ተነስቶ ና ተጠፋፍቶ-ዘር ማንዘር እስኪያስጠላው -ትውልድ -በጦርነት ናስደት፣ተሰቃይቶ በመከራው ሣይፈርድብን፣ሣያሳቅለን፣እባክህ ፣እባክህ፣አዲስ ራእይ አብረን እንይ  ከማለት በላይ ከአንድ ባለቅኔ ምን ይጠበቃል!/….ዘመኑን የዋጀ ቃልን ያልገደፈ፣ኢትዮጲያዊ ህይወትን ፣ሣይሰለችና ሣይሸነፍ እስከህቅታው በክብር ያገለገለ፣ ዋርካውና ታላቁ ባለቅኔ ብላቴን ጌታ ፀጋዬ ገ/መድህን ባለራዕይ ኢትዮጲያዊ ነው፡፡ በዚህ ከተስማማን የይድረስ ይድረስም ቢሆን፣….እንዲህ እንደመድማለን፡፡
        ይድረስህ ደርሶናል፡ ወንድም እንበለው፡፡ጓዴ፣(ኮምሬድ)፣ታጋዩ ጓዴ-ማለትን ግን እንተወው፡፡ባይሆን ከስጋ ወንድምነት ይልቅ ወደ መንፈሳዊው በሚያደለው የማይሞተው መንፈሳችን ወንድማማችነት ፣እንጠራራ፡፡እሱንም የነፍሱን እሪታ እናዳምጥለት፣ምክሩን እንቀበል፡፡ለነገሩማ ለሐቀኛ ታጋዮች ወንድማማችነት ታላቁ መርህ አለነበር፡፡ዛሬ የሴራ ፖለቲካ ማሰተዋላችንን ሳይወርብን በፊት እኮ፣የሴራ ፖለቲካ ጠባሳንማ በደንብ ቀምሰነው የድል ፅዋችንን አሰነጥቀን ህዝብን ላለፈት ሰላሳ ዓመታት ፍዳ ዳርገነዋል፡፡ማ?..ሁላችንም፡፡ሌላው ባለቅኔ እነደሚለው “ማንም የለ ነፃ የሚወጣ”::
     ወንድማማችነት በሃይማኖት አይገድበንም፡፡በጎሳ አያጋጨንም፡፡በቀለም አይለያየንም፡፡በዘር አያቧድነንም፡፡ወንድማማችነት አንድ ሙሉ ሰው ካለው ስብዕና ሙላት ከፊል ገፅታው መሆኑን ማወቅ ይገባዋል፡፡አንጂ በእውቀቱ ሳይንሳዊነት ወይም በሃብቱ እርከን ማበጀት ሳቢያ ሌላውን የሚንቅበት የወዳጅ መለያው ሊሆን አይችልም፡፡ለሰው ልጆች ነፃነት እና አኩልነት የሚታገል ህሊና ሁሉ የሰው ልጆችን ወንድማማችነትን ይቀበላል፡፡እንጂ ልዩነታቸውን ውበት አሰመስሎ በማቅረብ ሽርደዳ፣ህዝብን ህዝቦች ብሎ በመጥራት እርኩስ መንፈስን አስርፆ ፤ወድማማችነትን  አያጠፋም፡፡
                                 ለነገሩ እኮ ጥንታያኑ አሳቢዎች ገና በጠዋቱ ሊበሪቴ፣ ኢኳሊቴ ፣ፍራተርኒቴ፣(liberty..equality,…fraternity=britherhood..)ነበር ፣ የሰብዓዊነት ጥያቄዎቻቸው ማጠንጠኛዎች፡፡በመካያውም ነበር ድንበር ተሸግረው ላልተወለዱበት ሉዓላዊ  ሀገር ህዝብ ነፃነት በመታገል መሞትን የወንድማማችነት መሰረት የጣሉት፡፡ሎረድ ባይረን የተባለ እንግሊዛዊ ባለቅኔ በሥነ ፅሁፉ ባለውለታው ለሆነው ለግሪክ ህዝብ ለመዋጋት ፈር የቀደደው፡፡ይህ የወንድማማችነት ረቂቅ ትርጓሜ እያደር ዓለምአቀፋዊ ቅርጽ ከመያዙ በፊት እነ ቼ ጉቭራን አፍርቷል፡፡ ዛሬማ የሰብዓዊነት ጠላቶች ፣በተባባረ የዓለም ህዝብ ጠላትነት ተፈረጀው ድባቅ ሲመቱ ማየት የቀንተቀን ወሬ ሆኗል፡፡ለዚህ ህብረ-ብሄራዊ ትብብር መሰረቱ ወንድማማችነት መሆኑን አንዘንጋ፡፡
        ይ ህ ሁሉ እየሆነ ሳለ ዛሬም በእኩያንና በሰናይት መካከል ያለው ጦርነት እንደቀጠለ ነው፡፡በየትኛውም ሀገር ይህ ጦርነት አለ፡፡በአህጉራችን የዚህ ጦርነት መልክ የሰብዓዊነት አያያዝ ደረጃችንን ከማሳበቅ አልፎ ለዓለም አቀፍ ወንጀልነት በመብቃቱ ዓለም አዲስ የተጠያቂነት መስፈርት አስቀምጣ በመልካምናአኩያን መካከል ጫፍ የደረሰውን ችሎት ማስተናገድ ቀትላለች፡፡ምስጋና ለባለብሩህ አእምሮ ባለቤቶቹ ይሁንና በዓለምዓቀፍ ወንደማማችነት የሚያመነው የሰው ልጅ ካተከላላነት ወደ “አጥቂነት”፣እየተሻገረ ይሔድ ዘንድ ግድ ያለው ሁሉ፣ ባለቅኔው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን፣እንዳለው፡- ከዕኩይነት ባፊት ያለውን ዕቡይነት ፣ከትውልዱ ህሊና እንዳይሰርፅ፣ወንድማዊ ትግሉን በመቀላቀል ለአዲስ ራዕይ የሚደረገውን ጉዞ ማፋጠን ይኖርበታል፡፡
    ኢትዮጵያ የሁላችንም እናት ናት፡፡እንውደዳት፡፡ፍቅራችንንም በስራ እንግለፅላት፡፡ታሪኳን እንጠብቅም እናርምም፡፡ከዕቡይነት ተላቀን ፣በልጅነት ስልጣን፣በጥበብና በዕውቀት እናሰልጥናት፡፡እንዳትበለጥብን እንቅናላት፡፡እንጂ በእሷ አንቅና፡፡ይልቅ የአዲስ ራዕይ ጉዟችንን  እናቅና፡፡….ይቅናን፡፡አሜን፡፡

                           ሁሌም  አብረን ነን፡፡(ተፈፀመ)2006-ኢትዮጵያ
By: Tesfaye Waktola 




  

Comments

Popular posts from this blog

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የ

I am an Oromo too! ስለምን ይዘበትብናል…?

እኛ በሰው አምሳል መፈጠራችንንና ከናንተው እኩል የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ስለመሆናችን እንዴት ተዘነጋችሁ! ቀደምት አባቶቻችን ስንቶቹን ደራሽ ያጡ የሀገራችንን ኢትዮጲያ ልጆች ጡት እያጠቡ ከአብራካቸው ከወጡ ልጆቻቸው እኩል እያስተማሩና ሀብት ንብረት እያወረሱ ለወግ ማዕረግ ያበቁ መሆናቸው ተረሳችሁ…? ኢትዮጲያዊነትን ከኦሮሞ ሕዝብ፤ የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጲያዊነት በመነጣጠል የምታገኙት ልዩ ጥቅም እነደሚኖር ሳይታለም የተፈታ መሆኑ በየጓዳው የሚወራው ለዚህም አይደል ብላችሁ እነዴት አልጠረጠራችሁም…? ሕዝቡ ሁሉ ተጠርጣሪ (ሊያውም በሽብርተኝነት) ተብሎ በይፋ እስር ቤት   እንዲገባ የሚቻላችሁ መስሏችሁ ይሆን…? እንኪያስ የትኛውን ሕዝብ ልትመሩት ነው…?(ይቅርታ በአይንህን ጨፍን ላሞኝህ ልትነግዱበት ነው…?- ለማለት ፈልጌ ነው፡፡) ለነገሩ ዞን 9ኞችን የመፍጠሩ ስትራቴጂ ሲነቃባችሁ ዞን 9 ነዋሪውን ትታችሁ ብሎገሮቹን ታስሩ ታንገላቱ ታሳድዱ ዘንድስ ማን አይዟችሁ እንዳላችሁ ምን ይታወቃል…? ይህች ፅሁፍ እንኳ ካቅሟ በመንግስታችሁ እውቅና አግኝታ ከመነበብና የፀሃፊውን መብት ከማስከበር ትታገድ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል…? ዓለም ሁሉ በንግድ /ቢዝነስ/ ፅንሰ ሃሳብ በተወጠረችበት በዚህ ዘመን የኋሊዮሽ የተንቋሸሸሽንበት ያህል እንዲሰማን የተደረግንባቸውን የሀገራችንን ታሪክ እየባዘታችሁ ስለምን የትውልዱን ተስፋ በቁንፅል ሃሳብ በመወጠር ትቀጩብናላችሁ…? እናንተ የምትገነቡትን ሕንፃ፣ ለሎችን በመጨቆን ስንጥቅ የምታተርፉበትን ንግድ፣ በሀሰት ህዝብን እየሸነገላችሁ የምትቸበችቡትን መሬት፣ የምታቀያይሯቸውን መኪኖች፣ ህዝብ የሚያውቃቸውና የማያውቃቸው በአጭር ጊዜ የምትበለፅጉባቻው መንገዶች ሁሉ ከዓይንና ከህሊናችን የተሰወሩ ይመስላችሁ ይሆን…?

Seeing the Arcs off , Nazareth main road

 Nazareth / Adama like all other cities and towns has very colorfully celebrated the Ethiopian Epiphany, `Timket` both religiously and culturally. Some funny  moments were on public by individuals and small group; including school children songs that used to be experienced in music periods or teaching help. Watch video here under.     See ...        more ...                 photo...