Skip to main content

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የሰጧቸውን ምክር ሁሌም እንደሚያስታውሱት ይናገራሉ። “ንጉሠ ነገሥቱ ተግታችሁ አጥኑ፣ ተማሩ ብለው ከመከሩን በኋላ ጠንክራችሁ መሥራት እና ሀገራችሁ ኢትዮጵያን የምትገነቡበትን ዕውቀት ይዛችሁ ተመለሱ። ስትመለሱ አዕምሯችሁ ዝግጁ የሆነ እውቀታችሁም ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚችል ጥበብን ሸምቶ እንዲመለስ ነው እንጂ አውሮፓ ውስጥ እንዴት ያሉ ረዣዥም ፎቅ ቤቶች እንዳሉ ወይም መንገዶቻቸው የቱን ያህል ስፋት እንዳላቸው እንድትነግሩን አይደለም።” ነበር ያሏቸው። አፈወርቅ ተክሌ በእንግሊዝ አገር የአዳሪ ተማሪ ቤትን ኑሮ ሲያስታውሱ የባዕድ ባህላት፣ የአየር ለውጥ እና የተለመደው የተማሪ ቤት ዝንጠላ እንዳስቸገራቸው ያወሳሉ። ቢሆንም ትምሕርታቸውን በትጋት ሲከታተሉ ቆዩ። በተለይም በሒሣብ፣ በፖካርሲን (chemistry) እና በታሪክ ትምሕርቶች ጥሩ ውጤት በማምጣት ሰለጠኑ። ነገር ግን አስተማሪዎቻቸው የተፈጥሮ ስጦታቸው ኪነ ጥበብ እንደሆነ ለመገንዘብ ብዙ ጊዜም አልወሰደባቸውም። በነሱም አበረታችነት በእዚህ ስጦታቸው ላይ የበለጠ ለማተኮር ወስነው በሎንዶን የኪነ ጥበብ ማእከላዊ ትምሕርት ቤት (Central school of Arts & Crafts) ተመዝግበው ገቡ:: እዚህ ትምህርት ቤት ጥምሕርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለከፍተኛ ጥናት በስመ ጥሩው የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ የስሌድ ኪነ ጥበብ ማዕከል (Faculty of Fie Arts at Slade) የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ተማሪ (ከተከተሏቸው አፍሪቃውያን አንዱ የሱዳን ተወላጁ ኢብራሂም ኤል ሳላሂ ናቸው) በመሆን ገቡ። እዚህ በስዕል፣ ቅርጽ እና በስየቃ (architecture) ጥናቶች ላይ አተኩረው ተመረቁ። ትምሕርታቸውን አጠናቀው ወደኢትዮጵያ ሲመለሱ፣ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በየጥቅላይ ግዛቶቹ እየተዘዋወሩ፣ በየቦታው እስከ ሦስት ወራት በመቀመጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እና የብሔረሰቦቿን ባህልና ወግ ሲያጠኑ ቆዩ። “ምኞቴ በዓለም የታወቀ ኢትዮጵያዊ የኪነ ጥበብ ምሑር መሆን ስለነበር፣ የአገሬን ወግና ባሕል ጠንቅቄ ማወቅና ማጥናት እንዳለብኝ አውቄያለሁ። ሥራዬ የዓለም ንብረት ይሆናል ነገር ግን በአፍሪቃዊነት ቅመም የጣፈጠ ሥራ ነው የሚሆነው።” ይሉ ነበር። ከሁሉም በላይ ግን የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ፤ የላቀው ድካማቸውና የምናየውም ውጤት፣ የኪነ ጥበብ ሥራቸው የአገራቸውን ታሪክ የሚያንጸባርቅ ሕብረተ ሰብአዊ መሣሪያ እንዲሆን ነው። በውጭ የተማሩ ቢሆኑም፣ እሳቸው ‘ዋጋ ቢስ’ የሚሉትን፣ እንደሌሎች (ምዕራባውያንም ሆኑ ሌሎች) የሚጠቀሙበትን ‘ኩረጃ’ ላለመከተል በትጋት ተፋልመዋል። ወደ ውጭ ሊሄዱ ሲነሱ የሰሙትን የንጉሠ ነገሥቱን ቃላት ‘….ኢትዮጵያን ለመገንባት አዕምሯችሁ ዝግጁ ይሁን፣ ለዚህም የሚጠቅም ጥበብን ሸምቱ…” ያሏቸው ቃላት አሁንም በውስጠ ጆሯቸው እያስተጋቡ፤ ከውጭ ሲመለሱ የተመደበላቸውን ሚኒስቴራዊ ሥራ ትተው የኪነ ጥበብ ሥራቸው ላይ በማተኮር ስዕሎቻቸውን በአገር ውስጥም በውጭ አገርም እያሳዩ ለማገልገል ቆረጡ። በሀያ ሁለት ዓመታቸውም በ፲፱፻፵፮ ዓ/ም ሥራቸውን የሚያሳይ የመጀመሪያውን የኪነ ጥበብ ትርዒት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት አቀረቡ። ወዲያውም ከዚህ ትርዒት ባገኙት ገቢ ተመልሰው ወደአውሮፓ በመሄድ ለሁለት ዓመት በኢጣልያ፣ ፈረንሳይ፣ እስፓኝ፣ ፖርቱጋል፣ ብሪታንያ እና ግሪክ አገሮች የጠለቀ የኪነ ጥበብ ጥናት አከናወኑ። በተለይም በነኚህ አገሮች ውስጥ በስደት የሚገኙትን የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ የብራና መጻሕፍት በጥልቅ አጠኑ። እንዲሁም የመስታወት ስዕል (stained glass art) እና የ’ሞዜይክ’ አሠራርን ጥበብ ተምረው ወደአገራቸው ተመለሱ። በዚህ በሁለተኛ መልሳቸው ንጉሠ ነገሥቱ የመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን በሃይማኖታዊ የግድግዳና ጣሪያ ስዕሎች፣ የ’ሞዜይክ’ ሥራዎች፣ መስኮቶቹንም በመስታወት ስዕሎች እንዲያሳምሩት ቀጥረዋቸው አሁን የምናያቸውን እንደ “የዳግማዊ ምጽአት ፍርድ”፣ የእመቤታችንን ንግሠት የሚያሳየው “ኪዳነ ምሕረት”፣ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የዘውድ ስርዓት የሚያሳዩ ሥራዎቻቸው ይገኙበታል። አከታትለውም አሁን በሐረር ከተማ የሚገኘውን የልዑል ራስ መኮንንን ሀውልት ሠሩ። የስዕል እና ሌላ የኪን ሥራዎቻቸው ወዲያው በ’ቴምብሮች’፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የኪነ ጥበብ ትርዒት ላይ እጅግ በጣም እየታወቁና እየገነኑ መጡ። የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ ማክሰኞ፣ ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በተወለዱ በ፸፱ ዓመታቸው፤ በቅርብ ባደረባቸው ጽኑ ሕመም በሕክምና እየተረዱ ሳለ በካዲስኮ ሆስፒታል አርፈዋል። ከታዋቂ ሥራዎቻቸው በከፊል • አዲስ አበባ በአፍሪቃ አዳራሽ መግቢያ የሚታየው በመቶ ሃምሳ ካሬ ሜትር ላይ የተሳለው ትላቅ የመስታወት ስዕል፤ አንዱ የአፍሪቃን የቀድሞ ዕሮሮ፤ ሁለተኛው የአኅጉሯን የወቅቱን ትግል እና በሦስተኛው ደግሞ የዚችን ትላቅ አኅጉር የወደፊት ተስፋ የሚያሳዩ ናቸው • አዲስ አበባ በ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ስዕሎች፣ ‘ሞዜይኮች’ • አዲስ አበባ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚገኘው የመጀመሪያው የ’ዳግመኛ ምጽዓት ፍርድ ስዕል • በሐረር የልዑል ራስ መኮንን ሐውልት • በአዲግራት የ’ዳግመኛ ምጽዓት ፍርድ ስዕል • በሎንዶን ‘ታወር ኦፍ ለንደን’ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ቤት ከብር እና ከእንጨት የተሠራ የመንበር መስቀል • በሩሲያ፣ አሜሪካ እና በሴኔጋል ትርዒቶች የታዬው ‘የመስቀል አበባ’ • “እናት ኢትዮጵያ’ • የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምስል • ‘ደመራ’ ሲገኙበት፣ በ፲፱፻፶፰ ዓ/ም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሽልማት ድርጅት ተሸላሚም ናቸው። “የእኔን ሥራ የሚያዩ ሁሉ ተስፋ እንዲያገኙ፣ ስለኢትዮጵያ እና ስለ አፍሪቃ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው፣ በፀሐይ ጮራ እንዲሞቁ፣ ከሁሉም በላይ ግን “ይቻላል” የሚል እምነት እንዲኖራቸው ፍላጎቴ ነው።” የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ፤ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ፣ አዲስ አበባ ራሳቸው በነደፉትና ባሠሩት ባለ ሃያ ሁለት መኝታ ቤቱ ‘ቪላ አልፋ’ ይኖሩና ይሠሩ ነበር።
ቁጥር (አንድ) የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጆችዋ ታሪክ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የሰጧቸውን ምክር ሁሌም እንደሚያስታውሱት ይናገራሉ። “ንጉሠ ነገሥቱ ተግታችሁ አጥኑ፣ ተማሩ ብለው ከመከሩን በኋላ ጠንክራችሁ መሥራት እና ሀገራችሁ ኢትዮጵያን የምትገነቡበትን ዕውቀት ይዛችሁ ተመለሱ። ስትመለሱ አዕምሯችሁ ዝግጁ የሆነ እውቀታችሁም ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚችል ጥበብን ሸምቶ እንዲመለስ ነው እንጂ አውሮፓ ውስጥ እንዴት ያሉ ረዣዥም ፎቅ ቤቶች እንዳሉ ወይም መንገዶቻቸው የቱን ያህል ስፋት እንዳላቸው እንድትነግሩን አይደለም።” ነበር ያሏቸው። አፈወርቅ ተክሌ በእንግሊዝ አገር የአዳሪ ተማሪ ቤትን ኑሮ ሲያስታውሱ የባዕድ ባህላት፣ የአየር ለውጥ እና የተለመደው የተማሪ ቤት ዝንጠላ እንዳስቸገራቸው ያወሳሉ። ቢሆንም ትምሕርታቸውን በትጋት ሲከታተሉ ቆዩ። በተለይም በሒሣብ፣ በፖካርሲን (chemistry) እና በታሪክ ትምሕርቶች ጥሩ ውጤት በማምጣት ሰለጠኑ። ነገር ግን አስተማሪዎቻቸው የተፈጥሮ ስጦታቸው ኪነ ጥበብ እንደሆነ ለመገንዘብ ብዙ ጊዜም አልወሰደባቸውም። በነሱም አበረታችነት በእዚህ ስጦታቸው ላይ የበለጠ ለማተኮር ወስነው በሎንዶን የኪነ ጥበብ ማእከላዊ ትምሕርት ቤት (Central school of Arts & Crafts) ተመዝግበው ገቡ:: እዚህ ትምህርት ቤት ጥምሕርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለከፍተኛ ጥናት በስመ ጥሩው የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ የስሌድ ኪነ ጥበብ ማዕከል (Faculty of Fie Arts at Slade) የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ተማሪ (ከተከተሏቸው አፍሪቃውያን አንዱ የሱዳን ተወላጁ ኢብራሂም ኤል ሳላሂ ናቸው) በመሆን ገቡ። እዚህ በስዕል፣ ቅርጽ እና በስየቃ (architecture) ጥናቶች ላይ አተኩረው ተመረቁ። ትምሕርታቸውን አጠናቀው ወደኢትዮጵያ ሲመለሱ፣ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በየጥቅላይ ግዛቶቹ እየተዘዋወሩ፣ በየቦታው እስከ ሦስት ወራት በመቀመጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እና የብሔረሰቦቿን ባህልና ወግ ሲያጠኑ ቆዩ። “ምኞቴ በዓለም የታወቀ ኢትዮጵያዊ የኪነ ጥበብ ምሑር መሆን ስለነበር፣ የአገሬን ወግና ባሕል ጠንቅቄ ማወቅና ማጥናት እንዳለብኝ አውቄያለሁ። ሥራዬ የዓለም ንብረት ይሆናል ነገር ግን በአፍሪቃዊነት ቅመም የጣፈጠ ሥራ ነው የሚሆነው።” ይሉ ነበር። ከሁሉም በላይ ግን የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ፤ የላቀው ድካማቸውና የምናየውም ውጤት፣ የኪነ ጥበብ ሥራቸው የአገራቸውን ታሪክ የሚያንጸባርቅ ሕብረተ ሰብአዊ መሣሪያ እንዲሆን ነው። በውጭ የተማሩ ቢሆኑም፣ እሳቸው ‘ዋጋ ቢስ’ የሚሉትን፣ እንደሌሎች (ምዕራባውያንም ሆኑ ሌሎች) የሚጠቀሙበትን ‘ኩረጃ’ ላለመከተል በትጋት ተፋልመዋል። ወደ ውጭ ሊሄዱ ሲነሱ የሰሙትን የንጉሠ ነገሥቱን ቃላት ‘….ኢትዮጵያን ለመገንባት አዕምሯችሁ ዝግጁ ይሁን፣ ለዚህም የሚጠቅም ጥበብን ሸምቱ…” ያሏቸው ቃላት አሁንም በውስጠ ጆሯቸው እያስተጋቡ፤ ከውጭ ሲመለሱ የተመደበላቸውን ሚኒስቴራዊ ሥራ ትተው የኪነ ጥበብ ሥራቸው ላይ በማተኮር ስዕሎቻቸውን በአገር ውስጥም በውጭ አገርም እያሳዩ ለማገልገል ቆረጡ። በሀያ ሁለት ዓመታቸውም በ፲፱፻፵፮ ዓ/ም ሥራቸውን የሚያሳይ የመጀመሪያውን የኪነ ጥበብ ትርዒት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት አቀረቡ። ወዲያውም ከዚህ ትርዒት ባገኙት ገቢ ተመልሰው ወደአውሮፓ በመሄድ ለሁለት ዓመት በኢጣልያ፣ ፈረንሳይ፣ እስፓኝ፣ ፖርቱጋል፣ ብሪታንያ እና ግሪክ አገሮች የጠለቀ የኪነ ጥበብ ጥናት አከናወኑ። በተለይም በነኚህ አገሮች ውስጥ በስደት የሚገኙትን የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ የብራና መጻሕፍት በጥልቅ አጠኑ። እንዲሁም የመስታወት ስዕል (stained glass art) እና የ’ሞዜይክ’ አሠራርን ጥበብ ተምረው ወደአገራቸው ተመለሱ። በዚህ በሁለተኛ መልሳቸው ንጉሠ ነገሥቱ የመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን በሃይማኖታዊ የግድግዳና ጣሪያ ስዕሎች፣ የ’ሞዜይክ’ ሥራዎች፣ መስኮቶቹንም በመስታወት ስዕሎች እንዲያሳምሩት ቀጥረዋቸው አሁን የምናያቸውን እንደ “የዳግማዊ ምጽአት ፍርድ”፣ የእመቤታችንን ንግሠት የሚያሳየው “ኪዳነ ምሕረት”፣ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የዘውድ ስርዓት የሚያሳዩ ሥራዎቻቸው ይገኙበታል። አከታትለውም አሁን በሐረር ከተማ የሚገኘውን የልዑል ራስ መኮንንን ሀውልት ሠሩ። የስዕል እና ሌላ የኪን ሥራዎቻቸው ወዲያው በ’ቴምብሮች’፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የኪነ ጥበብ ትርዒት ላይ እጅግ በጣም እየታወቁና እየገነኑ መጡ። የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ ማክሰኞ፣ ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በተወለዱ በ፸፱ ዓመታቸው፤ በቅርብ ባደረባቸው ጽኑ ሕመም በሕክምና እየተረዱ ሳለ በካዲስኮ ሆስፒታል አርፈዋል። ከታዋቂ ሥራዎቻቸው በከፊል • አዲስ አበባ በአፍሪቃ አዳራሽ መግቢያ የሚታየው በመቶ ሃምሳ ካሬ ሜትር ላይ የተሳለው ትላቅ የመስታወት ስዕል፤ አንዱ የአፍሪቃን የቀድሞ ዕሮሮ፤ ሁለተኛው የአኅጉሯን የወቅቱን ትግል እና በሦስተኛው ደግሞ የዚችን ትላቅ አኅጉር የወደፊት ተስፋ የሚያሳዩ ናቸው • አዲስ አበባ በ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ስዕሎች፣ ‘ሞዜይኮች’ • አዲስ አበባ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚገኘው የመጀመሪያው የ’ዳግመኛ ምጽዓት ፍርድ ስዕል • በሐረር የልዑል ራስ መኮንን ሐውልት • በአዲግራት የ’ዳግመኛ ምጽዓት ፍርድ ስዕል • በሎንዶን ‘ታወር ኦፍ ለንደን’ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ቤት ከብር እና ከእንጨት የተሠራ የመንበር መስቀል • በሩሲያ፣ አሜሪካ እና በሴኔጋል ትርዒቶች የታዬው ‘የመስቀል አበባ’ • “እናት ኢትዮጵያ’ • የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምስል • ‘ደመራ’ ሲገኙበት፣ በ፲፱፻፶፰ ዓ/ም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሽልማት ድርጅት ተሸላሚም ናቸው። “የእኔን ሥራ የሚያዩ ሁሉ ተስፋ እንዲያገኙ፣ ስለኢትዮጵያ እና ስለ አፍሪቃ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው፣ በፀሐይ ጮራ እንዲሞቁ፣ ከሁሉም በላይ ግን “ይቻላል” የሚል እምነት እንዲኖራቸው ፍላጎቴ ነው።” የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ፤ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ፣ አዲስ አበባ ራሳቸው በነደፉትና ባሠሩት ባለ ሃያ ሁለት መኝታ ቤቱ ‘ቪላ አልፋ’ ይኖሩና ይሠሩ ነበር።

Source:  Ethio Love ኢትዮ ፍቅር's photo./ facebook.com

Comments

Popular posts from this blog

Voice of Africa; empowering self esteem

(This post had been originally found on my other blog since May 25, 2013. Please consider post date while reading.)              As dreamed to have achieved the greatness of Africa every nation shall take part an adhesive self development of thinking, working, saving and serving. No desperate movement of individual, small group and, or clan interest shall be recorded in the coming Africa. African shall learn to really stand together.  Since the beginning, all the world noted    how potentially resourceful Africa was. The strong power of the western interest scrambled the continent for years and had employed varies tying techniques to lame the nation so that the invaders keep on sipping raw materials and human resources. As far as most African countries are concerned, ethnicity and poor administration have been playing a vital role in the sluggish growth of the continent in contrary to the fast emerging new techno...

የወሲብ ግፍና ዘመን

(This post had been on my other blog since April 04,2013. Please consider the original post date while reading.) ዘመነ ወሲብ ዛሬ ዛሬ መቼም ትዳር የሚባለው ጎጆ የጋብቻ   ምሰጢር ያለበት አልመስል ብሏል፡፡ በአፀያፊ መልኩ ዎንዶችና ሴቶች ገና ጨቅላ በሚባል የጉልምስና (በዘመንኛው ቃል የፍንዳታ እድሜ ይሉታል፡፡) እድሜያቸው ወሲብ መጀመራቸውና በአስራዎቹ አጋማሽ ላይ ሲደርሱ ዓለም ሰየጠንሁ  ያለበትን የወሲብ ክህሎት ጣራ ነክተው ከዚያ ሲዳክሩ ይከረሙና በወላጅ ይሁን በኑሮ ግፊት ትዳር ይመሰርታሉ፡፡ የዚህ አዲስ አይነት ጎጆ አባላት ደግሞ በአብዛኛው የሚያስቁ ጥነዶች የሆናሉ፡፡ እነዲህ ያለው ትዳር የተመሰረተው ለገንዘብ ወይም ለውጭ ሀገር ዕድል ከሆነ፤ ተጋቢዎቹም ሆነ ገገባው ሩቅ ሳይሄድ ህጋዊ ፍች እንደሚፈፀምበት ገና የሰርጉ እለት ያውቁታል፡፡ በቤተሰብ ግፊትና በአብሮ አበዶች ሆይሆይታ የሚቀለስም ተመሳሳይ ጎጆ አለ፡፡ ብቻ ይህኛውም መቼ  እነደሚሆን አይታወቅም እንጂ ላይዘልቅ እንደሚችል ተጋቢዎቹም ሆኑ እኛ ስለጋብቻው አሁን የሰማን ሰዎች ከልምዳችን በመነሳት እርግጠኞች መሆን ንችላለን፡፡ የሆኖሆኖ የዛሬ ትዳር ምነም እክሎችን የያዘ እነደሆነ ላሰታውሳችሁ፡፡ ውሽምና ድጋፍ ባያገኝም አስከዚህኛው ትውልድ በመዝለቁ፤ ወደሽርሙጥና  እና  የዳማ በሚል ስያሜ በቡድን ለሚፈፀም ሰው ሰራሽ አረመኔያዊ ወሲብነት አድጓ፡፡ ጥነዶች በአንድ ጣራ ስር ሆነው እንኳ በተመሳሳይ ሰዓት ከተለያዩ ሰዎች ጋር በስልክ ወሲብ ራሳቸውን ያረካሉ፡፡ የነውሩ ዘመን   በአባቶቻችንና ከዚያ ቀደም ባለው ትውልድ ወሲብ በይፋ በየመንገዱ እንደልብ የሚወሳ ሳይሆን እንደነውር ...