Skip to main content

የወሲብ ግፍና ዘመን

(This post had been on my other blog since April 04,2013. Please consider the original post date while reading.)

ዘመነ ወሲብ
ዛሬ ዛሬ መቼም ትዳር የሚባለው ጎጆ የጋብቻ   ምሰጢር ያለበት አልመስል ብሏል፡፡ በአፀያፊ መልኩ ዎንዶችና ሴቶች ገና ጨቅላ በሚባል የጉልምስና (በዘመንኛው ቃል የፍንዳታ እድሜ ይሉታል፡፡) እድሜያቸው ወሲብ መጀመራቸውና በአስራዎቹ አጋማሽ ላይ ሲደርሱ ዓለም ሰየጠንሁ  ያለበትን የወሲብ ክህሎት ጣራ ነክተው ከዚያ ሲዳክሩ ይከረሙና በወላጅ ይሁን በኑሮ ግፊት ትዳር ይመሰርታሉ፡፡

የዚህ አዲስ አይነት ጎጆ አባላት ደግሞ በአብዛኛው የሚያስቁ ጥነዶች የሆናሉ፡፡ እነዲህ ያለው ትዳር የተመሰረተው ለገንዘብ ወይም ለውጭ ሀገር ዕድል ከሆነ፤ ተጋቢዎቹም ሆነ ገገባው ሩቅ ሳይሄድ ህጋዊ ፍች እንደሚፈፀምበት ገና የሰርጉ እለት ያውቁታል፡፡

በቤተሰብ ግፊትና በአብሮ አበዶች ሆይሆይታ የሚቀለስም ተመሳሳይ ጎጆ አለ፡፡ ብቻ ይህኛውም መቼ  እነደሚሆን አይታወቅም እንጂ ላይዘልቅ እንደሚችል ተጋቢዎቹም ሆኑ እኛ ስለጋብቻው አሁን የሰማን ሰዎች ከልምዳችን በመነሳት እርግጠኞች መሆን ንችላለን፡፡

የሆኖሆኖ የዛሬ ትዳር ምነም እክሎችን የያዘ እነደሆነ ላሰታውሳችሁ፡፡ ውሽምና ድጋፍ ባያገኝም አስከዚህኛው ትውልድ በመዝለቁ፤ ወደሽርሙጥና  እና  የዳማ በሚል ስያሜ በቡድን ለሚፈፀም ሰው ሰራሽ አረመኔያዊ ወሲብነት አድጓ፡፡ ጥነዶች በአንድ ጣራ ስር ሆነው እንኳ በተመሳሳይ ሰዓት ከተለያዩ ሰዎች ጋር በስልክ ወሲብ ራሳቸውን ያረካሉ፡፡

የነውሩ ዘመን  
በአባቶቻችንና ከዚያ ቀደም ባለው ትውልድ ወሲብ በይፋ በየመንገዱ እንደልብ የሚወሳ ሳይሆን እንደነውር ተሸሽጎ የተያዘ ቢመስልም ዛሬ እውነቱን ለማስተዋል እንገደዳለን፡፡ እርግጥ በየዘመናቱ የሰው ልጅ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ህይወቱ ከገድልና ከጦርነት ጋር የተሳሰረ እንደነበር እሙን ነው፡፡ ይህም ስለ ጥንቱ ዘመን ጀብደኝነት ብቻ እነዲወሳ በማድረግ የወሲብ ህይወቱ ተሸፋፍኖ እንድናልፈው አድረጎናል፡፡ እርግጥነው በዚህ ብዙም ባል  ው ያለፈው ዘመን የወሲብ ህይወት ዙሪያ በርካታ መፀሃፍትና ፊልሞች ለህዝብ ቀርበዋል፡፡

ከሀይማኖት ድርሳናት ይልቅም የፅድቀ ድርሳን የለምና እነርሱን ብቻ በማስተዋል ስለ ወሲብ ተፈጥሯዊነትና የሰውን ልጅ ከጥንቱ ዘመን እስካሁኑ እስካለው ትውልድ ያስቀጠለ ብቸኛ መንገድ ስለመሆኑ መረዳት ይቻላል፡፡ በእነዚህ ቅዱስ መፀሃፍት ታዲያ አንዳንድ ሰዎች ወሲብን ባህላዊ ወይም ዘመናዊ ለማድረግ ሲጥሩ እነደሚስቱ  ዋናውን የህይወት ቁልፍም እንደሚጥሉ ተጠቁሟል፡፡

ለማንኛውም ግን በየትውልድ ከሚፈፀሙት የወሲብ ግፎች የያለፈው ትወልደ እንዲህ ይታወሳል፡፡ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ሰስለማይሰጥ ተሳፍሮባት ይወርዳል፡፡ ሁለትም ሶስትም ሚስት ካለችው እያማረጠ አንሶላ ይጋፈፋል፡፡ በተገቢው ፍቅር የተጋቡ እንኳ ቢሆን ለጥቂት ጊዜ ካልሆነ በቀር  ጥም የሚቆረጥን ወሲብ እስከመጨረሻው ሲለማምዱ አይቆም ነበር፡፡

የሀብት ደረጃቸው የወደዷትን ሊድርላቸው ያልቻሉ ደግሞ በበሏ አርካታ ያጣችውን ሴት በቋሚነት ወይም ጊዜው እስከፈቀደ ጣፋጭ ማር የሚቆረጡላት ውሽሞቿ የሆኑላታል፡፡ የሚገርመው ግን በዚህ መሀል ልጅ እንኳ ቢፈጠር የህግ ባል የኔ ብሎ ያሳድገዋል፤ ጉዱን መች በቶሎ ያውቅና! ሌላው አስገራሚው ነገር እነኚህ በውሽምነት የሚያገለግሉ ወንዶች የራሳቸው አነስተኛ ትዳርና በርካታ ልጆች ይኖራቸዋል፡፡

መኖሪያቤቶች
ከጥንቱ ዘመን ጀምሮ የተንጣለሉ ባይባሉም ልዩ ልዩ ክፍሎች ያሏቸው ጎጆዎች መቀለስ የተለመደ ነው፡፡ ሳሎን፤ ትልቁ መኝታ ክፍል፤ የልጆች ክፍል፤ እቃ ቤት፤ እንግዳ ክፍል፤ ማእድ ቤት… ወዘተ፡፡ የቤቱ አቅምና ጥራት ደረጃ ምንም ያህል ቢሰፋና ቢጠብ እነኚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ይሸጋሸጋሉ እነጂ መቅረት አይችሉም፡፡ ለምሳሌ አነኚህ ሁሉ በአነዲት ባልተከፋፈለች ጠባብ ክፍል ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ፡፡
እንግዲህ ታዲያ ልጆች የበዙባቸው ትዳሮች ከላይ የጠቀስነውን አይነት የወሲብ ህይወት ይዘው በኣባውራው አቅም የተሰራው የቤት ሥፋትና ክፍልፋይ በቂነትና አናሳነት ምክኒያት ሊባል የሚችል ነገር አለ፡፡

ከዘመናዊ የወሲብ አመለካከት ጋር ተያይዞ ቤቶች እየዘመኑ የቤት ይዞታ ባለቤትነትም እየተወደደ፤ እየናረ፤ጣራ እየነካ ስለመጣ ባለአንድ በለሁለትና ባለሶስት ክፍል የኪራይ ዋጋቸው አይነኬ ቤቶች እየተስፋፉ መጡ፡፡ የኪራይ ቤትን ተከትሎም የኪራይ ኑሮ ተጀመረ፡፡

ሰፋ የለቤት ሲከራዩ ሰፋ ያለ የጓደኛ አቅርቦት፤ ትደር የሚመስሉ ሰፋ ያሉ እንቅስቃሴዎች መብዛት፤ አንድ ክፍል ሲይዙም እነደመጠኑ አነዲት ጓደኛ፤ አነዲት ውሽማ፤ እነርሱ ንቀው ከሄዱ ደግሞ ሌላ አነስ ያለች ሴት፤  ካልሆነም በቀን አዳር የለባቸው ፔንሲዮኖች  ጋር ጎራ ማለት፤ እያሉ፤ እያሉ በዋጋቢስነት መኖር፡፡

የግፉ አዝመራ ፍሬ
ዘር ተዘርቶ ሲበቅል አጥፉን ያፈራል፡፡ ሰላሳም፤ ስልሳም፤ መቶም ፍሬ፡፡ ባባቶቻችንም ዘንድ ሆነ በዚህ ዘመን ያለውን ፍሬ ልብ ልንል ይገባል፡፡

በቀደመው ዘመን በአፍላነት የጋብቻ ዘመናቸው የሰሩትን ፍቅር አድሚያቸው ገፋ ሲል ልጆች በቤታቸው በዝተውባቸው  የስሜታቸውን እንኳ ለማብረድ ተሳቀውና ተጨንቀው አካባቢው ጭር ሲል ጠብቀው አድብተውና አድፍጠው በተፈጥሮ በነፃ የተሰጣቸውን ንፁህ የጋብቻ መኝታ በዱር በገደል ተሟግተው ተዳምተው እንደሚያገኙት ድል በመከራ ይጠጡታል፡፡

ንፁሁን መኝታ ከምትጋራቸው ሚስታቸው ከስር ከስር እየተማከሩ ለኑሮም ሆነ ፍቅር ለመስራት የሚያመችን ጎጆ መቀለስ የሚያስችል አቅም እያላቸው በነውር ተጀቡነው ነውር ነው አያሉ ነውረኛውን ነገር ሳይቀር በስውር አየፈፀሙ ልጆቻቸውን አሳደጉ፡፡ ይህም የግፋቸው ደመወዝ ሆነ፡፡

ይሄኛው ትውልድ ደግሞ ድንገት ያገኘውን የተቀዳ የወሲብ ሙዚቃ እየደለቀ ሀገሩን ሁሉ እያስጮኸው ነው፡፡ ከታላላቅ የሀገረ ጉዳይ ስብሰባዎች እስከ ትንንሽ የመጠጥ ንግድ ቤቶች የወሲብ ማሻሻጫ መድረኮች ሆነዋል፡፡ ከመድረኩ ጀርባ አንድም ንፁህ ሰው አይገኝ የተባለ ይመስል ሁሉም በዚህ ጉዳይ ሀጥዕ ሆኗል፡፡

እንሆም ለሰራተኛ ደሞዙን አይነፍጉምና ትውልዱ የዘራውን ዘር ማጨዱን ጀምሯል፡፡ በጥንዶች ግጭት በሚጠፉ ነፍሳት ሳቢያ የወላጅ አልባ ህፃናት ቁጥር የትዬለሌ ሲደርስ በተጧሪ አያት እጅ የእንፉቅቅ የሚያድጉትን ደግሞ ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ በዚህ ኑሮ ሶስትና አራት ሰርጎችን ለደገስ መገደድም ሌላኛው የመጥፎው ዘር ፍሬ ነው፡፡
የሆነ ጊዜ ሲቀብጡ ፀያፍ አይነት ወሲብ የፈፀሙባት ሴት የልጀዎ አስተማሪ ወይም የታናሽ ወንድምዎ ሚስት ሆና ያገኟታል፡፡ የሆነ ጊዜ ለጥቅም ብለሽ ያወጣሽው ወንድ የባለቤትሽ ለቃ ሆኖ በእንግድነት ቤትሽን ይጎበኘዋል፡፡


ታዲያ ወሲብ ግፍ የለውም ይባላል?         

Comments

Popular posts from this blog

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የ

I am an Oromo too! ስለምን ይዘበትብናል…?

እኛ በሰው አምሳል መፈጠራችንንና ከናንተው እኩል የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ስለመሆናችን እንዴት ተዘነጋችሁ! ቀደምት አባቶቻችን ስንቶቹን ደራሽ ያጡ የሀገራችንን ኢትዮጲያ ልጆች ጡት እያጠቡ ከአብራካቸው ከወጡ ልጆቻቸው እኩል እያስተማሩና ሀብት ንብረት እያወረሱ ለወግ ማዕረግ ያበቁ መሆናቸው ተረሳችሁ…? ኢትዮጲያዊነትን ከኦሮሞ ሕዝብ፤ የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጲያዊነት በመነጣጠል የምታገኙት ልዩ ጥቅም እነደሚኖር ሳይታለም የተፈታ መሆኑ በየጓዳው የሚወራው ለዚህም አይደል ብላችሁ እነዴት አልጠረጠራችሁም…? ሕዝቡ ሁሉ ተጠርጣሪ (ሊያውም በሽብርተኝነት) ተብሎ በይፋ እስር ቤት   እንዲገባ የሚቻላችሁ መስሏችሁ ይሆን…? እንኪያስ የትኛውን ሕዝብ ልትመሩት ነው…?(ይቅርታ በአይንህን ጨፍን ላሞኝህ ልትነግዱበት ነው…?- ለማለት ፈልጌ ነው፡፡) ለነገሩ ዞን 9ኞችን የመፍጠሩ ስትራቴጂ ሲነቃባችሁ ዞን 9 ነዋሪውን ትታችሁ ብሎገሮቹን ታስሩ ታንገላቱ ታሳድዱ ዘንድስ ማን አይዟችሁ እንዳላችሁ ምን ይታወቃል…? ይህች ፅሁፍ እንኳ ካቅሟ በመንግስታችሁ እውቅና አግኝታ ከመነበብና የፀሃፊውን መብት ከማስከበር ትታገድ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል…? ዓለም ሁሉ በንግድ /ቢዝነስ/ ፅንሰ ሃሳብ በተወጠረችበት በዚህ ዘመን የኋሊዮሽ የተንቋሸሸሽንበት ያህል እንዲሰማን የተደረግንባቸውን የሀገራችንን ታሪክ እየባዘታችሁ ስለምን የትውልዱን ተስፋ በቁንፅል ሃሳብ በመወጠር ትቀጩብናላችሁ…? እናንተ የምትገነቡትን ሕንፃ፣ ለሎችን በመጨቆን ስንጥቅ የምታተርፉበትን ንግድ፣ በሀሰት ህዝብን እየሸነገላችሁ የምትቸበችቡትን መሬት፣ የምታቀያይሯቸውን መኪኖች፣ ህዝብ የሚያውቃቸውና የማያውቃቸው በአጭር ጊዜ የምትበለፅጉባቻው መንገዶች ሁሉ ከዓይንና ከህሊናችን የተሰወሩ ይመስላችሁ ይሆን…?