Skip to main content

Posts

Showing posts from 2013

እሳት ወይ አበባ (ጸጋዬ ገብረ መድኅን)

ወንድ ብቻዉን ነዉ እሚያለቅስ ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ ተሸሽጎ ተገልሎ ተሸማቆ ተሸምቆ ከቤተ ሰዉ ተደብቆ መሽቶ የማታ ማታ ነዉ ሌት ነዉ የወንድ ልጅ እንባዉ ብቻዉን ነዉ የሚፈታዉ፡፡ . . . ብቻዉን ነዉ የሚረታዉ፡፡. . . . ችሎ ዉጦ ተጨብጦ ተማምጦ ተጣጥሮ በሲቃ ግት ተወጥሮ እንደደመና ተቋጥሮ እዉስጥ አንጀቱ ተቀብሮ . . . . መሽቶ፣ ረፍዶ፣ ጀምበር ጠልቆ የጨለማ ድባብ ወድቆ በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ፣ በዝምታ ሲዋጥ አገር ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ፣ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር. . . . የኋላ ኋላ ማታ ምድር አገሩ በእፎይታ ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ ሁሉ በእረፍት ዓለምርቆ ብቸኝነት ብቻ ሲቀርብ ያኔ ነዉ ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ የብቻ እንባ ወዙ እሚነጥብ፡፡ ብቻዉን ነዉ ብቻዉን ነዉ. . . . የእንባ ጨለማ ለብሶ ነዉ ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥበዉ፡፡ ዕጣዉን ብቻዉን ቆርሶ ብቻዉን ሰቀቀን ጎርሶ ብቻዉን ጭለማ ለብሶ ገበናዉን ሳግ ሸፍኖ ክብሩን በሰቆቃ አፍኖ ሌሊት የማታ ማታ ነዉ ሕቅ እንቁን እሚነጥበዉ ኤሎሄዉን እሚረግፈዉ. . . . ከዓይኑ ብሌን ጣር ተመጦ ከአንጀቱ ሲቃ ተቆርጦ ደም አልሞ ፍም አምጦ ከአጽመ-ወዙ እቶን ተፈልጦ እንደጠፈር-ብራቅ እምብርት እንደእሳተ ገሞራ ግት ‘ርቅ ነዉ ወንድ ልጅ እንባዉ ደም ነዉ ፍም ነዉ እሚያነነባዉ ንጥረ ሕዋስ ነዉ ሰቆቃዉ ረቂቅ ነዉ ምስጢር ነዉ ጣሩ . . .ብቻዉን ነዉ የሚፈታዉ ብቻዉን ነዉ የሚረታዉ፡፡ ችሎ ዉጦ ተጨብጦ ሰቀቀኑን በሆዱ አጥሮ በአንጀቱ ገበና ቀብሮ ዉሎ ጭጭ እፍን ብሎ እንደደመና ተቋጥሮ ጣሩን ዉጦ ተጣጥሮ በሲቃ ግት ተሰትሮ. . . . ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ ከቤተ-ሰዉ ተደብቆ አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ...

Hino da Etiópia (voz) Ethiopia National Anthem (vocal) (source: http://s.ytimg.com)

ሃገሬ አህያ ናት!

  ትንፋሽ አሳጥቶ በርሃብ ቀጥቶ ጉልበቷ እስከሚዝል በዝቶብኛል ሳትል ተራራ ሜዳውን ማንም የሚነዳት አንዱ ሲጋልባት ሌላው የሚጭናት ሃገሬ አህያ ናት! ክብሯ የትም ወድቆ መብቷ ተንቆ ጅራፍና ዱላው ሲፈራረቁባት ነይ ወደዚህ ሲሏት ሂጅ ወደዚያ ሲሏት ሃገሬ የእኔ እናት የመሪዎች ሸክም ወገቧን አጉብጧት እንደማሽላ አራ ደግሞም እየሳቀች   በዘመን ፋርጎ ላይ ዛሬም ትጏዛለች! Source (የግጥም ምሽት በፌስቡክ) //በዘሐዲስ አየለ//

ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም.የግጥም መድብል ....

አስገራሚ ገጠመኞች የተስተዋሉበት የግጥም መድብል ምርቃት ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም. በልዩ ሁኔታ በኢትዮጲያ  ወመዘክር አዳራሽ ተፈፀመ፡፡

ጥበብን፤ እውነትን፤ ፍቅርን፤ ኢትዮጲያን መታሰቢያ ያደረገ የግጥም...........

እንሆ ጥበብን፤ እውነትን፤ ፍቅርን፤ ኢትዮጲያን መታሰቢያ ያደረገ የግጥም መድብል ትናንት በአዲሰአበባ ቤተመዛግብትና ወመዘክር አዳራሽ በአስገራሚ ስነስርዓት ተመረቀ፡፡    

ሲሞት ያልገደለን…

ሲሞት ያልገደለን… ሞቱን የገደለ አንድ ሰው ተገኘ ጭቆናን ረግጦ በልዕልና የናኘ ሲታሰር ያስፈታ ሲለቀቅ የፈታ ሲሞት ያልገደለ ሲነሳ ይበረታ! ይልክልን ይሆን መንፈሱን መፅናኛ እምነቱን ፅናቱን ትዕግስቱን ስለእኛ አይጠረጠርም-ዛሬም ትላንትና መንፈሱ አብሮን አለ ሲያጀግን- ሲያፅናና የሮቢን ባህታዊ - እነሱ እነደሚሉን- የጥቁር ሰብዓዊ አካልን መንፈስን በአንድ አስተባብሮ ነፃነት ያወጀ በህገ-ተፈጥሮ ከኢየሱስ ቀጥሎ ሚስጥር የነገረን እውነትን በተግባር ቀምሶ ያስተማረን ማንዴላ ሕያው ነው በመኖሩ ያኖረን - ሲሞት ያልገደለን፡፡ - ተስፋዬ ዋቅቶላ - 27/03/2006 ዓ/ም - ናዝሬት-ኢትዮጵያ

When one loves nature and all its value, art takes the position to tell the story!

ፍቅር በአርጩሜ! ያኔ ትምህርት ቤት ቀለሙን ስንቀልም፣ ስሌት ስናሰላ ሰይንስ ስንጠበብ፣ አይናችን ሲገለጥ ሁሉን ስንካን፣ ፍቅርን ዝም አሉን የኛ መምህር፡፡ ትዝ ይለኛል ያኔ.... የክፍሌ ተማሪ ፍቅር ብታሲዘኝ፣ አይናፋርነጸቷ ዝምታዋ ቢያመኝ፣ ፍቅረሯ አያማለለ መማሩ ቢሳነኝ፣ ትዝ ይለኛል ያኔ.... ቃላት አውጣጥቼ ደብዳቤ መፃፌ፣ ባማሩ ቃላቶች ወደድኩሽ ማለቴ፤ ግና ምን ይሆናል.... ወድጃለሁ ብዬ ሃሳቤን በገለፅኩ፣ እሰልፉ መሃል ላይ ባርጩሜ ተገረፍኩ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... እንደወንጀለኛ ፍርድ እንዳጎደለ፣ ማፍቀሬ ተወራ ጉድ እየተባለ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... የአርጩሜው መዘዝ ስር አየሰደደ፣ ፍቅር በአርጩሜ ከኔ ተዋሀደ፡፡ ይመስገነው ዛሬ ሴትን አልጠይቅም፣ የማፍቀሩን ፀጋ ነፃነት አላውቅም፣ ሰጠየቅ እሺ እንጂ እኔ አልጠይቅም፡፡ እኔ!?.... ምን በወጣኝ! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... በስመአብ!! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... እማማ ትሙት - እኔ አልጠይቅም፡፡ 1981 ዓ.ም. — ናዝሬት በመስፍን ገብሬ ወንዳፍራሽ (ቅንጣት 2005 ዓ.ም.)

Obama, Mandela

  "We, too, must act on behalf of justice. We, too, must act on behalf of peace," said Obama, who like Mandela became the first black president of his country. Obama said that when he was a student, Mandela "woke me up to my responsibilities — to others, and to myself — and set me on an improbable journey that finds me here today."  source:    Tesfaye Waktola on face book

The man who taught Mandela to be a soldier

       The man who taught Mandela to be a soldier By Penny Dale BBC Africa, Addis Ababa In July 1962, Col Fekadu Wakene taught South African political activist Nelson Mandela the tricks of guerrilla warfare - including how to plant explosives before slipping quietly away into the night. Mr Mandela was in Ethiopia, learning how to be the commander-in-chief of Umkhonto we Sizwe - the armed wing of the African National Congress (ANC). The group had announced its arrival at the end of 1961 by blowing-up electricity pylons in various places in South Africa. Then on 11 January 1962, Mr Mandela had secretly, and illegally, slipped out of South Africa. His mission was to meet as many African political leaders as possible and garner assistance for the ANC, including money and training for its military wing. And to be moulded into a soldier himself. During this trip, he visited Ethiopia twice and left a deep impression on those who met ...

ይብላኝ…

ችግር ወላፈኑ ጠብሶሽ በላብሽ ፍሳሽ ልታብሽው እንደዋዛ ካገር ወተሽ ደፋ ብለሽ ለቀረሽው በደሌን አሁን አወኩት ምትክ በሌለው ብዕርሽ ሰቆቃሽ ገፍቶ በፃፍሽው በድንጋይ ላይ ትርክትሽ በሞትሽ ቃል ገለፅሽው እህቴ ልናዘዝ ስሚኝ በባዕድ ሀገር ወርውሬ የገደልኩሽ እኔነኝ ስሚኝ… የጅብ ከሄደ ጩኸቴን የምፀት ቃል ምሬቴን የፍርሀት ጠርዝ መልክቴን የምላስ ተርፍ በረከቴን ይብላኝ… ያያትሽን ግብር ሳልፈፅም በሞቴ ሂወት ሳልሰጥሽ ከጠላትሽ ጋር አብሬ እኔው በጅ አዙር ገደልኩሽ ይብላኝ… የሞትሽ ፀፀት ሳይበቃኝ እንደገና ልገልሽ በሰልፍ ወደሞት ስቴጂ ዝም ብዬ ለማይሽ ይብላኝ… የሰው ትርፍ አርጌ እንደ አይረባ ለጣልኩት ውርደትሽን ክብር አርጌ በደምሽ ወዝ ለራስኩት የናቴ ልጅ… እኔን ይድፋኝ ልበልሽ ልደፋ ይድረሰኝ ፅዋሽ ነፃ ማውጣቱ ቢያቅተኝ ሞትሽን ባፌ ልጋራሽ /ፀደቀ ድጋፌ/

ሲሞት ያልገደለን…

     ሞቱን የገደለ አንድ ሰው ተገኘ ጭቆናን ረግጦ በልዕልና የናኘ     ሲታሰር   ያስፈታ ሲለቀቅ የፈታ     ሲሞት ያልገደለ ሲነሳ ይበረታ! ይልክልን ይሆን መንፈሱን መፅናኛ እምነቱን ፅናቱን ትዕግስቱን ስለእኛ አይጠረጠርም-ዛሬም ትላንትና መንፈሱ አብሮን አለ ሲያጀግን- ሲያፅናና የሮቢን ባህታዊ - እነሱ እነደሚሉን- የጥቁር ሰብዓዊ አካልን መንፈስን በአንድ አስተባብሮ ነፃነት ያወጀ በህገ-ተፈጥሮ ከኢየሱስ ቀጥሎ ሚስጥር የነገረን እውነትን በተግባር ቀምሶ ያስተማረን ማንዴላ ሕያው ነው በመኖሩ ያኖረን ሲሞት ያልገደለን፡፡ ተስፋዬ ዋቅቶላ 27/03/2006 ዓ/ም ናዝሬት-ኢትዮጵያ

የሷ ሱስ

የወደዷትን ልጅ እያወዳደሱ እያሞጋገሱ እንዲህ እያስደነሱ፤ ልፍታ ልተው ቢሏት እንኳንስ ፍቅሯና አይለቅህም ሱሱ! tsenawoo

ፍቅር በአርጩሜ!

ያኔ ትምህርት ቤት ቀለሙን ስንቀልም፣ ስሌት ስናሰላ ሰይንስ ስንጠበብ፣ አይናችን ሲገለጥ ሁሉን ስንካን፣ ፍቅርን ዝም አሉን የኛ መምህር፡፡ ትዝ ይለኛል ያኔ.... የክፍሌ ተማሪ ፍቅር ብታሲዘኝ፣ አይናፋርነጸቷ ዝምታዋ ቢያመኝ፣ ፍቅረሯ አያማለለ መማሩ ቢሳነኝ፣ ትዝ ይለኛል ያኔ.... ቃላት አውጣጥቼ ደብዳቤ መፃፌ፣ ባማሩ ቃላቶች ወደድኩሽ ማለቴ፤ ግና ምን ይሆናል.... ወድጃለሁ ብዬ ሃሳቤን በገለፅኩ፣ እሰልፉ መሃል ላይ ባርጩሜ ተገረፍኩ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... እንደወንጀለኛ ፍርድ እንዳጎደለ፣ ማፍቀሬ ተወራ ጉድ እየተባለ፡፡ መቼ በዚህ ብቻ.... የአርጩሜው መዘዝ ስር አየሰደደ፣ ፍቅር በአርጩሜ ከኔ ተዋሀደ፡፡ ይመስገነው ዛሬ ሴትን አልጠይቅም፣ የማፍቀሩን ፀጋ ነፃነት አላውቅም፣ ሰጠየቅ እሺ እንጂ እኔ አልጠይቅም፡፡ እኔ!?.... ምን በወጣኝ! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... በስመአብ!! - እኔ አልጠይቅም፣ እኔ!?.... እማማ ትሙት - እኔ አልጠይቅም፡፡ 1981 ዓ.ም. — ናዝሬት በመስፍን ገብሬ ወንዳፍራሽ (ቅንጣት 2005 ዓ.ም.)