Skip to main content

እሳት ወይ አበባ (ጸጋዬ ገብረ መድኅን)


ወንድ ብቻዉን ነዉ እሚያለቅስ
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ ሰዉ ተደብቆ
መሽቶ የማታ ማታ ነዉ ሌት ነዉ የወንድ ልጅ እንባዉ
ብቻዉን ነዉ የሚፈታዉ፡፡ . . .
ብቻዉን ነዉ የሚረታዉ፡፡. . . .
ችሎ ዉጦ ተጨብጦ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደደመና ተቋጥሮ
እዉስጥ አንጀቱ ተቀብሮ . . . .
መሽቶ፣ ረፍዶ፣ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ፣ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ፣ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር. . . .
የኋላ ኋላ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለምርቆ ብቸኝነት ብቻ ሲቀርብ
ያኔ ነዉ ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ
የብቻ እንባ ወዙ እሚነጥብ፡፡

ብቻዉን ነዉ ብቻዉን ነዉ. . . .
የእንባ ጨለማ ለብሶ ነዉ
ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥበዉ፡፡

ዕጣዉን ብቻዉን ቆርሶ
ብቻዉን ሰቀቀን ጎርሶ
ብቻዉን ጭለማ ለብሶ
ገበናዉን ሳግ ሸፍኖ
ክብሩን በሰቆቃ አፍኖ
ሌሊት የማታ ማታ ነዉ
ሕቅ እንቁን እሚነጥበዉ
ኤሎሄዉን እሚረግፈዉ. . . .
ከዓይኑ ብሌን ጣር ተመጦ
ከአንጀቱ ሲቃ ተቆርጦ
ደም አልሞ ፍም አምጦ
ከአጽመ-ወዙ እቶን ተፈልጦ
እንደጠፈር-ብራቅ እምብርት
እንደእሳተ ገሞራ ግት
‘ርቅ ነዉ ወንድ ልጅ እንባዉ
ደም ነዉ ፍም ነዉ እሚያነነባዉ
ንጥረ ሕዋስ ነዉ ሰቆቃዉ
ረቂቅ ነዉ ምስጢር ነዉ ጣሩ . . .ብቻዉን ነዉ የሚፈታዉ
ብቻዉን ነዉ የሚረታዉ፡፡

ችሎ ዉጦ ተጨብጦ ሰቀቀኑን በሆዱ አጥሮ
በአንጀቱ ገበና ቀብሮ
ዉሎ ጭጭ እፍን ብሎ እንደደመና ተቋጥሮ
ጣሩን ዉጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተሰትሮ. . . .
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
ከቤተ-ሰዉ ተደብቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተከናንቦ ተሸማቆ ተሸማቆ. . . .
የብቻ ብቸኝነቱ የጭለማ ልብሱ እስኪደርስ
በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ
ቅስሙ በገበያ እንዳይፈስ
ተገልሎ በእኩለ-ሌት ወንድ ብቻዉን ነዉ እሚያለቅስ፡፡
Source:- የግጥም ምሽት በፌስቡክ https://www.facebook.com/groups/189373957880006/

Comments

Popular posts from this blog

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የ

I am an Oromo too! ስለምን ይዘበትብናል…?

እኛ በሰው አምሳል መፈጠራችንንና ከናንተው እኩል የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ስለመሆናችን እንዴት ተዘነጋችሁ! ቀደምት አባቶቻችን ስንቶቹን ደራሽ ያጡ የሀገራችንን ኢትዮጲያ ልጆች ጡት እያጠቡ ከአብራካቸው ከወጡ ልጆቻቸው እኩል እያስተማሩና ሀብት ንብረት እያወረሱ ለወግ ማዕረግ ያበቁ መሆናቸው ተረሳችሁ…? ኢትዮጲያዊነትን ከኦሮሞ ሕዝብ፤ የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጲያዊነት በመነጣጠል የምታገኙት ልዩ ጥቅም እነደሚኖር ሳይታለም የተፈታ መሆኑ በየጓዳው የሚወራው ለዚህም አይደል ብላችሁ እነዴት አልጠረጠራችሁም…? ሕዝቡ ሁሉ ተጠርጣሪ (ሊያውም በሽብርተኝነት) ተብሎ በይፋ እስር ቤት   እንዲገባ የሚቻላችሁ መስሏችሁ ይሆን…? እንኪያስ የትኛውን ሕዝብ ልትመሩት ነው…?(ይቅርታ በአይንህን ጨፍን ላሞኝህ ልትነግዱበት ነው…?- ለማለት ፈልጌ ነው፡፡) ለነገሩ ዞን 9ኞችን የመፍጠሩ ስትራቴጂ ሲነቃባችሁ ዞን 9 ነዋሪውን ትታችሁ ብሎገሮቹን ታስሩ ታንገላቱ ታሳድዱ ዘንድስ ማን አይዟችሁ እንዳላችሁ ምን ይታወቃል…? ይህች ፅሁፍ እንኳ ካቅሟ በመንግስታችሁ እውቅና አግኝታ ከመነበብና የፀሃፊውን መብት ከማስከበር ትታገድ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል…? ዓለም ሁሉ በንግድ /ቢዝነስ/ ፅንሰ ሃሳብ በተወጠረችበት በዚህ ዘመን የኋሊዮሽ የተንቋሸሸሽንበት ያህል እንዲሰማን የተደረግንባቸውን የሀገራችንን ታሪክ እየባዘታችሁ ስለምን የትውልዱን ተስፋ በቁንፅል ሃሳብ በመወጠር ትቀጩብናላችሁ…? እናንተ የምትገነቡትን ሕንፃ፣ ለሎችን በመጨቆን ስንጥቅ የምታተርፉበትን ንግድ፣ በሀሰት ህዝብን እየሸነገላችሁ የምትቸበችቡትን መሬት፣ የምታቀያይሯቸውን መኪኖች፣ ህዝብ የሚያውቃቸውና የማያውቃቸው በአጭር ጊዜ የምትበለፅጉባቻው መንገዶች ሁሉ ከዓይንና ከህሊናችን የተሰወሩ ይመስላችሁ ይሆን…?

Seeing the Arcs off , Nazareth main road

 Nazareth / Adama like all other cities and towns has very colorfully celebrated the Ethiopian Epiphany, `Timket` both religiously and culturally. Some funny  moments were on public by individuals and small group; including school children songs that used to be experienced in music periods or teaching help. Watch video here under.     See ...        more ...                 photo...