Skip to main content

ቀልድ ስላለማወቃችን

12/11/2006EC

አንድ ሰሞን ወደሁለት ተከፍላ ብዙም ሳትቆይ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው ሱዳን የገጠማትን ምስቅልቅል ሁኔታ ለመከታተል አለም ሁሉ ጆሮውን አቁሞ ነበረ፡፡ ቀድሞም ጠግቦ ያላደረው ደሃ ሕዝብ ነፍሱን ስለማቆየት ሲል ወደጎረቤት ሀገራት ተሰዷል፡፡ በዛ አስቸጋሪ ወቅት ግን አቶ ሳልቫኪየር ከየሀገራቸው እድገትና ስልጣኔ ያልተመጣጠነ ምቾት ስላሰከራቸው አቻዎቻቸው ጉዳይ እንጂ ስለ ሕዝባቸው ፈፅሞ ግድ የሌላቸው እንደሆነ መሰከሩልን፡፡ “የፀጥታውን ስምምነት የፈረምኩት የኢትዮጲያው ጠቅላይ ሚኒሰተር አስርሃለሁ ስላሉኝ ነው”-ብለው አስደመሙን፡፡ 


ጋዜጠኞቹም ለጉዳዩ መልስ ሲጠባበቁ ቆዩና ሰሞኑን አቶ ኃይለማሪያምን ማብራሪያ ይጠይቋቸዋል፡፡ እርሳቸውም ሳልቫኪየር ቀልዴን ነው ብለዋል ሲሉ መለሱ፡፡ እንዲያውም እነዚህ ጋዜጠኞች ቀልድ አያውቁም ብለው መናገራቸውን ሊያብራሩ ሞክረው አለፉ፡፡ ይህም የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ደረቅ ቀልድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡


ኢቴቪ 1234 ተብሎ ይቀለዳል፤ ስለመብራት ስርጭት ብዙ ቁም ነገር የሚመስሉ ቀልዶች እንሰማለን፤ እናያለን፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት ላይ በተጠናከረ መልክ እየሰሩ መሆኑን ይነግሩናል__የቀልዳቸውን፡፡ መንግስት ጸረ-ሰላም ሀይሎች የህዝብን ጥቅም የሚነኩ -ሰብዐዊ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው ብሎ የቀልዱን ይነግረንና አሴሩ የተባሉትን አሳራቸውን ያበላቸዋል፤ግን የቀልዱን ነው፡፡የሃገሪቷን ሰላም ለማደፍረስ ስለመነሳታቸው መረጃ የለማ!


ቀላል የከተማ ባቡር መጓጓዣን ስራ ለማሰጀመር ሩጫው እየተፋጠነ መሆኑ በተደጋጋሚ በቴሌቪዥን የተገለጸው__ ቀልድ፤ እንዲያውም በቀልዱ መዘዝ ተነጠፈ የተባለው ሀዲድ ተመልሶ ሲፈታ በአይናችን በብረቱ አይተናል፡፡


 ስለደሞዝ ጭማሪ በርካታ ጊዜ ፓርላማ ለሚሰበሰቡ ተወካዮች እናቴሌቪዥን እና ሬድዮ ለሚከታተሉ ዜጎች እንደማሽላ እያሳረሩ የሚያስቁ ንግግሮችን የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስተር አቶ መለስ ያደርጉ ነበር፡፡ ቀልደኛ ነበሩ፡፡ የእርሳቸውን ሞት ተከትሎም በፓርላማ መቀመጫ 2 ቁጥር የተጻፈባትን ጠረጴዛ እያሳዩ ማንም በፓርላማው ላይ ሊቀልድ እንደማይችል__ ይህም ለሃዘኑ መባባስ መግለጫ ቁም ነገር ሆኖ በተደጋጋሚ ሲቀለድ ነበር፡፡


በሰሞንኛው የቴሌቪዥን ዲስኩር ደግሞ የመንግስት ሰራተኞችን ደምወዝ ጭማሪ መነገር አስመልክቶ የዋጋ ማስተካከያ ላደረጉ ወይም ለሚያደርጉ ነጋዴዎች ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ__ ቀልድ እየተነገረ ነው፡፡ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል የሚባል ቀልድ፣ ዋና ዋና አስመጪዎች፣ ዋና ዋና አጓጓዦች፣ ዋና ዋና ደላሎች፣ ዋና ዋና ተቆጣጣሪዎች፤___ ግን አይቀልዱም፡፡ለምን መንግስት እንደሚቀልድ በደንብ ያውቃሉ፡፡ በደንብ ይመሳጠራሉ፡፡ የመጨረሻ ተጠቃሚ ደግሞ እየማቀቀና እየተቀለደበት ይሞታል፡፡


መንግስታችን ቀልድ ስለሚወድ ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠረው የቀልዱን ተገቢ ጥናት እንዳደረገ እየነገረን በዘፈቀደ እና በድንገት በሚወስደው እርምጃ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ የዛሬ ሶስት አመት አካባቢ የዶላር ምንዛሬ ዋጋ በአንድ ጊዜ 13 ብር ወደ 16 ብር ከፍ አለ፡፡ ከማግስቱ ጀምሮ ቀስ ቀስ እያለ እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በቁሳቁሱ ሁሉ ላይ ታየ፡፡ በዚህም ዶላርን በአይኑ አይቶ የማያውቅ  የኔ ቢጤ ደሃ ህዝብ እጅግ የተሻሻለ ድህነትን ይለማመድ ዘንድ ተፈረደበት፡፡ እርሱንም በጸጥታ ያጣጥማል፡፡ 


አሁንም የመንግስት ሰራተኛው ደሞዝ ድንገት በ100% ወይም በ150% ሊያድግ እንደሚችል እየተሰማ ነው፡፡ ይህ ቀልድ አይደለም__ ይከፈላል፡፡ ነገር ግን ቀልዱ አግባብነቱ ላይ ነው፡፡ የታሸገ ውሃ፣ ስኳር፣ ዘይት፣ አልባሳት፣ የምግብ ቤቶች ዋጋ ሁሉ በአንድ ጊዜ 100% እና 150% እንዳልጨመረ ግልጽ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ጭማሪውን ተከትሎ የሚኖር የሸቀጥ ዋጋ ልዩነት ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ተደረገ አልተደረገ ለውጥ የለውም፡፡ 


በንግድ ዘርፉ ውስጥ በተለያየ ደረጃ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖች እንደመንግስታችን ስለማይቀልዱ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸን አደጋ ላይ አይጥሉም፡፡ ቀስ ቀስ እያሉ በየሳምንቱ እና በየወሩ ሁኔታዎችን እያመቻቹ ዛሬ በመካከለኛ ምግብ ቤቶች ከ45 ብር እስከ 90 ብር የሚሸጠውን ጥብስ ከአንድ እና ሁለት አመት በኋላ ከ120ብር እስከ 180 ብር ሊያደርሱት አይችሉም ይባላል?___በፍፁም!___እነርሱ እንደመንግስታችን አይቀልዱማ፡፡


ሳሙና ከ3 ብር 14 ብር የገባው በአንድ ጊዜ አልነበረም፡፡ ዳቦ ከ20 ሳነቲም ወደ 1 ብር ከ40 ሳንቲም፤ ቢራ ከ2 ብር ከ70 ሳንቲም ወደ 13 ብር፤ ወተት ከ2 ብር ወደ 12 ብር የሻቀቡት በአንድ ጊዜ ባይሆንም አስር ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የእያንድንዳቸው ዋጋ ከ200% እስከ 600% ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኛ ደሞዝ ግን የዚህን የሩብ ሩብ አልጨመረም ነበር፡፡__አያችሁ ቀልድ?! የሰሞኑ ጭማሪ እሙን ቢሆን እንኳ እጅግ የዘገየ የቀልድ ጭማሪ ነው፡፡


የት/ቤቶች ክፍያ፣ የትራንስፖርት፣ የመዝናኛ ቦታዎች ዋጋ እንኳ በፍፁም ከእነዚህ ሊወዳደር አይችልም፡፡ ድሮ ከኢዲስ አበባ ናዝሬት ስትሄዱ ከለገሀር ተነስታችሁ የአዳማ ከተማ መነሀሪያ በአማካይ ከ 1፡30 አስከ 2፡00 ያህል ጊዜ ይወስድባችኋል፤ 6 ብር ለትራንስፖርት ይከፍላሉ፡፡ ዘንድሮ ግን በጉዞዎ ከ 3፡00 እስከ 4፡00 ያባክናሉ/ይባክንብዎታል፤ ለዚህም እስከ 42 ብር ለትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡


ናዝሬት መጥተው ደግሞ ሶደሬ ጎራ ማለትዎ አይቀርምና ቀድሞ 3 ብር የነበረው የትራንሰፖርት ክፍያ ወደ 15 ብር ከፍ ብሎ ይጠብቅዎታል፡፡ የመግቢያ ክፍያው ደግሞ ጥቂት ጭማሪ ብቻ ተደርጎበት ከ5 ብር ወደ 41 ብር ከፍ ብሏል፡፡አይስክሬም ከ 3 ብር ወደ 18 ብር፣ የታሸገ ውሃ ደግሞ ከ 15 ብር እስከ 25 ብር በሆነ ዋጋ ያገኛሉ፤ ሌላውን በአካል ሄዶ መታዘብ የእርስዎ ድርሻ ነው፡፡


“ቀልዱን ተይ” የሚለው የማን ዘፈን ነበረ? ሀገር ግን እንዴት በቀልድ ልትመራ ትችላለች? ለምን የቀልድ ጥናቶች፣ የቀልድ እሰሮች፣ የቀል ሞቶች፣ የቀልድ ሀውልቶች፣ የቀልድ ትምህርቶች፣ የቀልድ የሲቪል ማህበራት፣…ወዘተ፣ ይበዛሉ? ቀልድ ስላለማወቃችን መነገር የለበትም ታዲያ?...የቀልድም ቢሆን! የሆነ ትምህርት ስለቀልድ መማር አይኖርብንም? ሳናውቀው ህዝብ ላይ ስንቀልድ እነዳንገኝ ይጠቅመን እነደሆነ?...!!!

Comments

Popular posts from this blog

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የ

I am an Oromo too! ስለምን ይዘበትብናል…?

እኛ በሰው አምሳል መፈጠራችንንና ከናንተው እኩል የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ስለመሆናችን እንዴት ተዘነጋችሁ! ቀደምት አባቶቻችን ስንቶቹን ደራሽ ያጡ የሀገራችንን ኢትዮጲያ ልጆች ጡት እያጠቡ ከአብራካቸው ከወጡ ልጆቻቸው እኩል እያስተማሩና ሀብት ንብረት እያወረሱ ለወግ ማዕረግ ያበቁ መሆናቸው ተረሳችሁ…? ኢትዮጲያዊነትን ከኦሮሞ ሕዝብ፤ የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጲያዊነት በመነጣጠል የምታገኙት ልዩ ጥቅም እነደሚኖር ሳይታለም የተፈታ መሆኑ በየጓዳው የሚወራው ለዚህም አይደል ብላችሁ እነዴት አልጠረጠራችሁም…? ሕዝቡ ሁሉ ተጠርጣሪ (ሊያውም በሽብርተኝነት) ተብሎ በይፋ እስር ቤት   እንዲገባ የሚቻላችሁ መስሏችሁ ይሆን…? እንኪያስ የትኛውን ሕዝብ ልትመሩት ነው…?(ይቅርታ በአይንህን ጨፍን ላሞኝህ ልትነግዱበት ነው…?- ለማለት ፈልጌ ነው፡፡) ለነገሩ ዞን 9ኞችን የመፍጠሩ ስትራቴጂ ሲነቃባችሁ ዞን 9 ነዋሪውን ትታችሁ ብሎገሮቹን ታስሩ ታንገላቱ ታሳድዱ ዘንድስ ማን አይዟችሁ እንዳላችሁ ምን ይታወቃል…? ይህች ፅሁፍ እንኳ ካቅሟ በመንግስታችሁ እውቅና አግኝታ ከመነበብና የፀሃፊውን መብት ከማስከበር ትታገድ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል…? ዓለም ሁሉ በንግድ /ቢዝነስ/ ፅንሰ ሃሳብ በተወጠረችበት በዚህ ዘመን የኋሊዮሽ የተንቋሸሸሽንበት ያህል እንዲሰማን የተደረግንባቸውን የሀገራችንን ታሪክ እየባዘታችሁ ስለምን የትውልዱን ተስፋ በቁንፅል ሃሳብ በመወጠር ትቀጩብናላችሁ…? እናንተ የምትገነቡትን ሕንፃ፣ ለሎችን በመጨቆን ስንጥቅ የምታተርፉበትን ንግድ፣ በሀሰት ህዝብን እየሸነገላችሁ የምትቸበችቡትን መሬት፣ የምታቀያይሯቸውን መኪኖች፣ ህዝብ የሚያውቃቸውና የማያውቃቸው በአጭር ጊዜ የምትበለፅጉባቻው መንገዶች ሁሉ ከዓይንና ከህሊናችን የተሰወሩ ይመስላችሁ ይሆን…?

Seeing the Arcs off , Nazareth main road

 Nazareth / Adama like all other cities and towns has very colorfully celebrated the Ethiopian Epiphany, `Timket` both religiously and culturally. Some funny  moments were on public by individuals and small group; including school children songs that used to be experienced in music periods or teaching help. Watch video here under.     See ...        more ...                 photo...