Skip to main content

የመለስ ፋውነዴሽን (Meles Foundation)

(This post had been originally posted on April 03,2013 on my other blog please consider the original date)

በርካታ ባህላዊና ዘመናዊ መንግስታትን ያለ ግልፅ ቅኝ ተገዢነት ያስተናገደችው ሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የመልካም አስተዳደር እጦትና የሰበዓዊ መብት ረገጣ እየተባባሰ በመምጣቱ ሳቢያ ሕዝቡ የዜግነት መብቱን በመንግስት ስልጣን ላይ ባሉ ግለሰቦች ወይንም ቡድኖች ፈቃድ ብቻ ሊሰጠው ወይም ሊነፈገው የሚችል መሆኑን እያመነ መጥቷል፡፡

ይባስ ብሎ መንግስት ለሕዝቡ ጥቅም በሚል በሚዘረጋቸው በማንኛውም የልማት መርሀ ግብሮች የመንግስትንና የግል ሌቦችን በሚያበረታታ መልኩ በዘፈቀደ አሰራር እየተሰራ ነገር ግን ለይስሙላ ያህል የሒሳብና የሚዲያ ሪፖርቶች እንደሚደረጉ ያደባባይ ሚስጥር ከሆነ እየሰነበተ ነው፡፡

የሆኖ ሆኖ ለሃያ አመታት፤ ሊያውም በዚህ በዘመነ ግሎባላይዜሽን ሀገራችንን በስልጣን ሲያስተዳድር የቆየው ኢሕአዴግ ከስልጣን ጊዜው ቀድሞ የክፉውን ጨለማ ሳይቀር አሸንፎ የመጣለትን ጠንካራ (በእኔ አተያይ አስሊ እና ከዱረዬ ባልተናነሰ በፈንግጪው ውጤት ተኮር) የሆነ መሪውን ካጣ ይኸው መንፈቅ ሞላው፡፡ ያለአንድ አምባገነን ምልክትነት ሕዝቡን ሰቅዞ ይዞ መምራት ያለመደበት የኢትዮጲያ መንግስት አገዛዝ ቀጣዩን መሪ አይነኬ አድርጎ በህዝቡ ላይ ለመሳል ተስኖት እየተውተተረተረ ይገኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እነዳለም የመለስን ፋውነዴሽን ለማቋቋም ጥረቱ ቀጠሎ በመጪው ቅዳሜ በይፋ ፀድቆ ስራ ይጀምራል፡፡

የቅርቡን ቢልከሊነተንን ጨምሮ በርካታ የዓለም ሀገራት መሪዎች፤ ታዋቂ አረቲሰቶችና በየተለያዩ ስራቸው እውቅናና ሀብትን ያተረፉ የየዘርፉ ባለሙያዎች ራሳቸው እነደ አምባሳደር በመሆነን በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን የሚሰሩ ድርጅቶችን አቋቁመው በአካባቢ ማህበራዊ እና ስነ-ምህዳራዊ ፋይዳዎችን ለማሻሻል ሲተጉ ይስተዋላል፡፡

ምንም እንኳ እኔ በግሌ የአቶ መለስ አድነናቂ ባልሆንም በረካታ የአፍሪካ፤የአውሮፓ፤ የእስያና የአሜሪካ ባለስልጣናትና ባለሀብት ወዳጆች እንደሚኖራቸው ግልፅ ነው፡፡ እንኳን ሙስና በተስፋፋበትና ሀገሪቱ በአንፃሩ የሰላም ችግር የሌለባት ጊዜ ለሃያ አንድ ዓመታት የመሩተ እሳቸው ይቅርና በፋሽስት ዘመን ወረራ የደረሰባቸው አፄ ኃ/ስላሴ እና በኢትዮጲያ የእርስ በእርስ ጦርነት ዘመን አምባገነን መሪ የሚል ስም የተለጠፈላቸው ጓድ መንግስቱ ኃ/ማሪያምም ቢሆኑ በመከራቸው ጊዜ ለሊሸሽጋቸው የሚችሉ ወዳጆችን በሹመት ዘመናቸው አፍርተው ነበር፡፡

ስለሆነም በአቶ መለስ ስም ለሚቋቋመው ፋውነዴሽን በረካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ዜጎችና ድርጅቶች ገንዘባቸውን ሊሰጡና ፖለቲካዊ፤ ሐይማኖታዊ ወይም ሌላ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚችሉበትን መንገድ የበጁ እንደሆነ ጥረት ያደርጋሉ ብዬ አስባለሁ፡፡
ግና የዚህ ፋውንዴሽን ዓላማ የግለሰቡ መልካምነት መወደሻ መሆኑ ቀርቶ ለኢሕአዴግ መደነሻ፤ የልማት ሰራዎች አጋር መሆኑ ቀርቶ የተቀናቃኝ ፓረቲዎች መግረፊያ አሳር ከሆነ ፋውንዴሽንነቱ ይቀርና ይፈነደሳል፡፡

ነገር ግን የህ ፋውንዴሽን  አቶ መለስ ነበራቸው ተብሎ የሚታመንበትን ከፍተኛ የንባብ ልምድ ለተተኪው ትውልድ የሚያስተላልፍበትን ሰፊ ፐሮጀክተ የቀረፀና የሚሰራ ከሆነ፤ ሀይለቃልን ሳይቀር በበሰለ ቋንቋ እየተጠቀመ ተቀናቃኙን በትህትና መርታት የሚችል አንደበተ ርቱዕ ተናጋሪ ማፍራት የሚችልን መድረክ ካዘጋጀ፤ እንደቆሎ በተለቀመ እጅፅሁፍ አካሄዶችንና መመሪያዎችን መንደፍ ማዋቀርና ማብራራት የሚችሉ ፀሃፍትን የሚመለምልበት መንገድ ከቄሰ፤ እውነትም የሰውውን ስም ለዘመናት ማወደስ የሚችል ማዕከል የሆንና በሕይወት ዘመናቸው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወይም አቅም በማጣት ያከናወኗቸውን የግፍ ተግባራት ያሰተሰርይላቸዋል፡፡ 
ልናይ ኋላ ዶሮ “ለጄ ጭራም አትበላ፤” ብላለች አሉ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የ

I am an Oromo too! ስለምን ይዘበትብናል…?

እኛ በሰው አምሳል መፈጠራችንንና ከናንተው እኩል የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ስለመሆናችን እንዴት ተዘነጋችሁ! ቀደምት አባቶቻችን ስንቶቹን ደራሽ ያጡ የሀገራችንን ኢትዮጲያ ልጆች ጡት እያጠቡ ከአብራካቸው ከወጡ ልጆቻቸው እኩል እያስተማሩና ሀብት ንብረት እያወረሱ ለወግ ማዕረግ ያበቁ መሆናቸው ተረሳችሁ…? ኢትዮጲያዊነትን ከኦሮሞ ሕዝብ፤ የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጲያዊነት በመነጣጠል የምታገኙት ልዩ ጥቅም እነደሚኖር ሳይታለም የተፈታ መሆኑ በየጓዳው የሚወራው ለዚህም አይደል ብላችሁ እነዴት አልጠረጠራችሁም…? ሕዝቡ ሁሉ ተጠርጣሪ (ሊያውም በሽብርተኝነት) ተብሎ በይፋ እስር ቤት   እንዲገባ የሚቻላችሁ መስሏችሁ ይሆን…? እንኪያስ የትኛውን ሕዝብ ልትመሩት ነው…?(ይቅርታ በአይንህን ጨፍን ላሞኝህ ልትነግዱበት ነው…?- ለማለት ፈልጌ ነው፡፡) ለነገሩ ዞን 9ኞችን የመፍጠሩ ስትራቴጂ ሲነቃባችሁ ዞን 9 ነዋሪውን ትታችሁ ብሎገሮቹን ታስሩ ታንገላቱ ታሳድዱ ዘንድስ ማን አይዟችሁ እንዳላችሁ ምን ይታወቃል…? ይህች ፅሁፍ እንኳ ካቅሟ በመንግስታችሁ እውቅና አግኝታ ከመነበብና የፀሃፊውን መብት ከማስከበር ትታገድ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል…? ዓለም ሁሉ በንግድ /ቢዝነስ/ ፅንሰ ሃሳብ በተወጠረችበት በዚህ ዘመን የኋሊዮሽ የተንቋሸሸሽንበት ያህል እንዲሰማን የተደረግንባቸውን የሀገራችንን ታሪክ እየባዘታችሁ ስለምን የትውልዱን ተስፋ በቁንፅል ሃሳብ በመወጠር ትቀጩብናላችሁ…? እናንተ የምትገነቡትን ሕንፃ፣ ለሎችን በመጨቆን ስንጥቅ የምታተርፉበትን ንግድ፣ በሀሰት ህዝብን እየሸነገላችሁ የምትቸበችቡትን መሬት፣ የምታቀያይሯቸውን መኪኖች፣ ህዝብ የሚያውቃቸውና የማያውቃቸው በአጭር ጊዜ የምትበለፅጉባቻው መንገዶች ሁሉ ከዓይንና ከህሊናችን የተሰወሩ ይመስላችሁ ይሆን…?