Skip to main content

አስተያየት ነውር ነውን? (Is a comment a taboo?)

(This post had been originally found on my other blog since April 14, 2013. Please consider the original date while reading.)

ስነ ሂስ ለለውጥ መርሃ ግብር መሰረታዊ አስተዋፅዖ ስለማድረጉ የጠቢባን እምነት ነው፡፡ ጠቢባንም የልፋታቸው ሚሰጥር ስለጥበብ ቋንቋና ምግባር እድገት ነው፡፡ በመሆኑም ጠቢባን ጥበበኛ የሚባሉት ባበረከቱት መሰረታዊና መደበኛ ያልሆኑ መልካም አስተዋፅዖዎች ነው፡፡
የፖለቲካ አመለካከት ቅኝት ከማጣቱ የተነሳ በእውቀት ማነስ ከሚወቃቀሱ፣ ከሚነካከሱ እና ከሚገዳደሉ የህዝብ አካላት ተፅዕኖ ምክኒትያት ሂስ መስጠትም ሆነ ግድፈትን ማውራት የተቃዋሚ ወይም ተፃራሪ ቦታን ስለሚያሰጥ ጤናማ የሚባል ወይም ለዕድገት የጋራ ሚና ያለው አስተያየት ማግኘት የለም፡፡ እሳት ወለደች አይነት ነው፡፡
ስለሆነነም ስለመፃህፍት፣ አስተምህሮ፣ የስልጠና ማዕከላት፣ የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት፣ ወዘተ ባነሳን ቁጥር ስለዕድገትና ብልፅግና እያሰቡ ጉድለቶችን አንስቶ መተቸት ወይም ስህተቶችን መወረፍ እጅግ ነውረኛነትና “ከመልካም አሳቢው” ባለመፅሃፍ፣ አስተማሪ፣ የስልጠና ባለሙያ አልያም የሆቴልና ቱሪዝም አገልጋይ ዘንድ ጠላት ሆነኖ የመፈረጅን እድል ያጋፍጣል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ በሃገራችን እንጭጭ ሊባል የሚችል እድሜና እምብዛም አልተመደበለትም ሊባል የሚያስችል የገንዘብ በጀት የተደረገበትን የፊልም ጥበብን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚቀርብበትን ትችት በመመርኮዝ ባለሙያዎችና ባለሃብቱ ጥለውት እየፈረጠጡ፤ መንግስትም በግብርና ተዛማጅ ማነቆ ጣጣዎች ከፍተኛ ጫና በማድረግ ስለጥበቡ መሻሻል ግድፈቶች እንዲሻሻሉ የጠቆሙ ሂሰኞችን ለማሳፈር በሚመስል አካሄድ ለዘርፉ ማደግ የራሳቸውን የእንቅፋትነት ድርሻ አየተወጡ ይገኛሉ፡፡
 ምንም እንኳ በኛ ሀገር የጥበብ፣ የገንዘብና የባለሙያ አቅም ማነስ የተነሳ ይሄ ነው ተብሎ የሚቆጠር ተውልድ ግብዐት ባይሆንም፤ ያለችውን ዘመን አከፋፍለው የሀገሪቱ ፊልም ከሙዚቃና ቴአትር ጥበብ እንደተወለደ ባሉዋቸው ውስን ማስረጃዎች ማጣቀሻነት ይከራከራሉ፡፡
የሆኖ ሆኖ የፊልምን መነሻ ሀሳብ ተረድቶ ከመተግበር አንፃር ገና ብዙ መሻሻል አለበት የሚሉ አስተያየቶች ከመበራከታቸውና የተለያዩ የፊልም ጥበብ ማሰልጠኛ ማዕከላት ብቅ ብቅ ከማለታቸው የሰሉ ብዕሮችም ገና ቦታ ቦታቸውን መያዝና እርምትን መጠቆም ከመጀመራቸው  በቋፍና በስግብግብነት በጥበቡ ዙሪያ እየተሳተፉ ያሉ ነጋዴዎችና አድር ባይ ጠቢባንን እንዲሁም ደንባራ የመንግስት አካላትን ወዳልተገባ እርምጃና እነቅስቃሴ ያስኳተናቸው ይዟል፡፡ 
ለመሆኑ አስተያየት መስጠት ነውር ነነው እንዴ? ከፊልም ጥበብ የሚገኙ ገንዘቦች መልሶ በይበቡ ዙሪያ ያሉ ሰዎችን ብቃት ለማሳደግና  ለፊልሙ ጥበብ የተሸለ ዋስትና እነዲኖር ማስቻልን የሚያበረታቱ አስተያየቶች ያልተጠበቀ የግብር ቁልል እንዲከተል፤ የፊልምና ቴእር መድረኮች በርከት ያሉ ያለስራ የሚቆዩበት ሰዓታት መኖራቸው በጥያቄ ምልክት መጠቆሙ በአስገዳጅ ሁኔታ የፖለቲካ ማራመጃ የውይይት መድረኮች እንዲሆኑ መገደድን ማስከተሉ ምን ያህል ትችትና አስተያየትዎ እዚህ ሀገር እርባና ቢስና እንደተፈለገ ተተርጉሞ ለራስ ውድቀት ጥቆማ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡
እኔ ስለማዳላለት የፊልም ሙያ ዘርፍ ጠቆምኩ እንጂ በሃገራችን ያሉ እንዲሻሻሉ አስተያየት የተሰጠባቸው በርካታ የስራና የንግድ ዘርፎች ሁሉ በመንግስትና በሌሎች “ተፅዕኖ መፍጠር” በሚችሉ ባለጊዜዎች ሚዛናዊ ያልሆነ ፍርድ እየተሰጠባቸውና እንደውግዝ እየተቆጠሩ የአገልግሎት ዘመናቸው እንዲያበቁ ተደርገው ተከታዩ ትውልድ እንዳይጠቀምባቸው ሆኗል፡፡ አሁንም ይህ ጉዳይ የፊልሙን ዘርፍ እያስፈራራው ይመስለኛልና ለሚመለከታቸው ሁሉ ይህን ጥያቄ አነሳለሁ፡፡ ለመሆኑ አስተያየት መስጠት ነውር ነው እንዴ?

Comments

Popular posts from this blog

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ (ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም- ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም)፤ ‘’ኪነ ጥበብ የሰው ልጅን መንፈስ ለማዳበር፣ ሀገራችንን ለማሳደግ፣ ለማሳወቅ እና ለሕይወታዊ ኑሮ ተስፋ ለመፍጠር የላቀ ሚና ይጫወታል’’ ይላሉ። ለጥቀውም ‘’ዛሬ የምንሠራው ሥራ የዛሬን ሕይወት እያንጸባረቀ ለነገው ትውልድ ፈር መቅደድ አለበት፡፡” በሚል ስሜት ኪን ማንኛውንም የሰው ኑሮ ረገድ የሚነካ እንደሆነ ያስረግጣሉ። በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርታቸውን የት እና መቼ እንዳጠናቀቁ የተጻፈ መረጃ ባናገኝም፤ ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። ተሰዳጅ ተማሪ ወጣቶቹ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሲሰናበቱ፣ አፈወርቅ ተክሌ ጃንሆይ የ...

Voice of Africa; empowering self esteem

(This post had been originally found on my other blog since May 25, 2013. Please consider post date while reading.)              As dreamed to have achieved the greatness of Africa every nation shall take part an adhesive self development of thinking, working, saving and serving. No desperate movement of individual, small group and, or clan interest shall be recorded in the coming Africa. African shall learn to really stand together.  Since the beginning, all the world noted    how potentially resourceful Africa was. The strong power of the western interest scrambled the continent for years and had employed varies tying techniques to lame the nation so that the invaders keep on sipping raw materials and human resources. As far as most African countries are concerned, ethnicity and poor administration have been playing a vital role in the sluggish growth of the continent in contrary to the fast emerging new techno...

የወሲብ ግፍና ዘመን

(This post had been on my other blog since April 04,2013. Please consider the original post date while reading.) ዘመነ ወሲብ ዛሬ ዛሬ መቼም ትዳር የሚባለው ጎጆ የጋብቻ   ምሰጢር ያለበት አልመስል ብሏል፡፡ በአፀያፊ መልኩ ዎንዶችና ሴቶች ገና ጨቅላ በሚባል የጉልምስና (በዘመንኛው ቃል የፍንዳታ እድሜ ይሉታል፡፡) እድሜያቸው ወሲብ መጀመራቸውና በአስራዎቹ አጋማሽ ላይ ሲደርሱ ዓለም ሰየጠንሁ  ያለበትን የወሲብ ክህሎት ጣራ ነክተው ከዚያ ሲዳክሩ ይከረሙና በወላጅ ይሁን በኑሮ ግፊት ትዳር ይመሰርታሉ፡፡ የዚህ አዲስ አይነት ጎጆ አባላት ደግሞ በአብዛኛው የሚያስቁ ጥነዶች የሆናሉ፡፡ እነዲህ ያለው ትዳር የተመሰረተው ለገንዘብ ወይም ለውጭ ሀገር ዕድል ከሆነ፤ ተጋቢዎቹም ሆነ ገገባው ሩቅ ሳይሄድ ህጋዊ ፍች እንደሚፈፀምበት ገና የሰርጉ እለት ያውቁታል፡፡ በቤተሰብ ግፊትና በአብሮ አበዶች ሆይሆይታ የሚቀለስም ተመሳሳይ ጎጆ አለ፡፡ ብቻ ይህኛውም መቼ  እነደሚሆን አይታወቅም እንጂ ላይዘልቅ እንደሚችል ተጋቢዎቹም ሆኑ እኛ ስለጋብቻው አሁን የሰማን ሰዎች ከልምዳችን በመነሳት እርግጠኞች መሆን ንችላለን፡፡ የሆኖሆኖ የዛሬ ትዳር ምነም እክሎችን የያዘ እነደሆነ ላሰታውሳችሁ፡፡ ውሽምና ድጋፍ ባያገኝም አስከዚህኛው ትውልድ በመዝለቁ፤ ወደሽርሙጥና  እና  የዳማ በሚል ስያሜ በቡድን ለሚፈፀም ሰው ሰራሽ አረመኔያዊ ወሲብነት አድጓ፡፡ ጥነዶች በአንድ ጣራ ስር ሆነው እንኳ በተመሳሳይ ሰዓት ከተለያዩ ሰዎች ጋር በስልክ ወሲብ ራሳቸውን ያረካሉ፡፡ የነውሩ ዘመን   በአባቶቻችንና ከዚያ ቀደም ባለው ትውልድ ወሲብ በይፋ በየመንገዱ እንደልብ የሚወሳ ሳይሆን እንደነውር ...