Sometimes ... June 29, 2023 Sometimes days come to tell how we really feel about ourselves or whether we are confused. But what we speak or write is meaningful to others too. Does any one of this mean something to you? Share Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Share Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም.የግጥም መድብል .... December 15, 2013 አስገራሚ ገጠመኞች የተስተዋሉበት የግጥም መድብል ምርቃት ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም. በልዩ ሁኔታ በኢትዮጲያ ወመዘክር አዳራሽ ተፈፀመ፡፡ Read more
ቀልድ ስላለማወቃችን July 21, 2014 12/11/2006EC አንድ ሰሞን ወደሁለት ተከፍላ ብዙም ሳትቆይ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው ሱዳን የገጠማትን ምስቅልቅል ሁኔታ ለመከታተል አለም ሁሉ ጆሮውን አቁሞ ነበረ፡፡ ቀድሞም ጠግቦ ያላደረው ደሃ ሕዝብ ነፍሱን ስለማቆየት ሲል ወደጎረቤት ሀገራት ተሰዷል፡፡ በዛ አስቸጋሪ ወቅት ግን አቶ ሳልቫኪየር ከየሀገራቸው እድገትና ስልጣኔ ያልተመጣጠነ ምቾት ስላሰከራቸው አቻዎቻቸው ጉዳይ እንጂ ስለ ሕዝባቸው ፈፅሞ ግድ የሌላቸው እንደሆነ መሰከሩልን፡፡ “የፀጥታውን ስምምነት የፈረምኩት የኢትዮጲያው ጠቅላይ ሚኒሰተር አስርሃለሁ ስላሉኝ ነው”-ብለው አስደመሙን፡፡ ጋዜጠኞቹም ለጉዳዩ መልስ ሲጠባበቁ ቆዩና ሰሞኑን አቶ ኃይለማሪያምን ማብራሪያ ይጠይቋቸዋል፡፡ እርሳቸውም ሳልቫኪየር ቀልዴን ነው ብለዋል ሲሉ መለሱ፡፡ እንዲያውም እነዚህ ጋዜጠኞች ቀልድ አያውቁም ብለው መናገራቸውን ሊያብራሩ ሞክረው አለፉ፡፡ ይህም የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ደረቅ ቀልድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኢቴቪ 1 ፣ 2 ፣ 3 ፣ 4 ተብሎ ይቀለዳል፤ ስለመብራት ስርጭት ብዙ ቁም ነገር የሚመስሉ ቀልዶች እንሰማለን፤ እናያለን፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት ላይ በተጠናከረ መልክ እየሰሩ መሆኑን ይነግሩናል__የቀልዳቸውን፡፡ መንግስት ጸረ - ሰላም ሀይሎች የህዝብን ጥቅም የሚነኩ ኢ - ሰብዐዊ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው ብሎ የቀልዱን ይነግረንና አሴሩ የተባሉትን አሳራቸውን ያበላቸዋል፤ግን የቀልዱን ነው፡፡የሃገሪቷን ሰላም ለማደፍረስ ስለመነሳታቸው መረጃ የለማ ! ቀላል የከተማ ባቡር መጓጓዣን ስራ ለማሰጀመር ሩጫው እየተፋጠነ መሆኑ በተደጋጋሚ በቴሌ... Read more
ናዝሬትዬ መሪዎችሽ ለምን ይፈሩሻል? February 28, 2014 Tesfaye Waktola https://www.facebook.com/twaktola Andinet Ada-nazreth ናዝሬትዬ መሪዎችሽ ለምን ይፈሩሻል? ድሮም ጃንሆይ ናዛሬት/አዳማ መምጣት አይወዱም ነበር፣ይባላል፡፡በዚህም የተነሳ ለገላውዴዎስ ት/ቤት መሰረትና ምርቃት ከመምጣታቸው ውጪ ሌላ ጊዜ መች እንደመጡ ሲነገርም አልሰማሁም፡፡መንጌም ሲመጣ በጣም ተደብቆና በድንገት ሲሆን ፣የማስታውሰው ለናዝሬት ቴክኒክ ኮሌጅ (የዛሬው አዳማ ዩኒቨርሲቲ) መሰረትና ምርቃት መምጣቱን ነው፡፡ከዚያ በተረፈ ሁለቱም መሪዎች ወደ ሶደሬ ሲያልፉ ረዥም እድሜ ተመኙ ተብሎ ሕፃናት ወጥተን ቪቫ (VIVA JANHOY! …viva mengistu!..)ብለን እንገባ ነበር፡፡ያኔም ድንገት ካየናቸው ደስታችን ወሰን የለውም ነበር፡፡የልጅ ነገር!ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እጫወት ነበር …ያለው ማነው? ታዲያ ፍርሃት የተጋባበት መሌም ናዝሬት መጣ ከተባለ ከተማው በፌደራል ይወረራል፡፡ከዚያ የት እንዳደረ ሳይታወቅ ወይ ምሽቱን ሄዷል ወይ …አድሯል፡፡ካደረ ጎብዟል፡፡ግን መሌ ሶደሬ ሄዶ ያውቃል?….ቢዚ ስለነበር ምስኪን፣…. ግን ግን-ሶስቱም መሪዎችሽ ለምንፈሩሽ- ---እውነት ግን አዳማ/ናዝሬትን ለምን ፈሯት…? እስቲ እኔ ልገምት፡፡ ጊዜው በጣም ሩቅ ነው ይባላል፡፡ዓጼ ገላውዴዎስ ከግራኝ ጋር ጦርነት ገጥመዋል፡፡ጦርነቱ ተፋፍሞ ዓጼው ብዙ ከገፉ በኋላ ግራኝ ጦሩን አስተባብሮ እየገፋ ይመጣል፡፡ይሄኔ ላለመማረክ ሲዋጉ የነበሩት ንጉስ በስተመጨረሻ ይቆስላሉ በኋላም አሁን ካለው ከዓጼ ገላውዴዎስ ከፍ ብሎ ካለው ከአለሌ ወንዝ ማዶ ባለ ቦታ ተገድለው ተገኙ፡፡በኋላም ግራኝ አንገታቸውን ቆርጦ ወደ ሃረር ወስዶ በግንቡ ላ ሰቀለው የሚል ዲስኩር በገላውዴዎስ ት/ቤት ግቢ ውስጥ በ 50ኛ ... Read more
Comments
Post a Comment