(This post had been originally found on my other blog since April 14, 2013. Please consider the original date while reading.)
ስነ ሂስ ለለውጥ መርሃ ግብር መሰረታዊ አስተዋፅዖ ስለማድረጉ የጠቢባን እምነት ነው፡፡ ጠቢባንም የልፋታቸው ሚሰጥር ስለጥበብ ቋንቋና ምግባር እድገት ነው፡፡ በመሆኑም ጠቢባን ጥበበኛ የሚባሉት ባበረከቱት መሰረታዊና መደበኛ ያልሆኑ መልካም አስተዋፅዖዎች ነው፡፡
የፖለቲካ አመለካከት ቅኝት ከማጣቱ የተነሳ በእውቀት ማነስ ከሚወቃቀሱ፣ ከሚነካከሱ እና ከሚገዳደሉ የህዝብ አካላት ተፅዕኖ ምክኒትያት ሂስ መስጠትም ሆነ ግድፈትን ማውራት የተቃዋሚ ወይም ተፃራሪ ቦታን ስለሚያሰጥ ጤናማ የሚባል ወይም ለዕድገት የጋራ ሚና ያለው አስተያየት ማግኘት የለም፡፡ እሳት ወለደች አይነት ነው፡፡
ስለሆነነም ስለመፃህፍት፣ አስተምህሮ፣ የስልጠና ማዕከላት፣ የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት፣ ወዘተ ባነሳን ቁጥር ስለዕድገትና ብልፅግና እያሰቡ ጉድለቶችን አንስቶ መተቸት ወይም ስህተቶችን መወረፍ እጅግ ነውረኛነትና “ከመልካም አሳቢው” ባለመፅሃፍ፣ አስተማሪ፣ የስልጠና ባለሙያ አልያም የሆቴልና ቱሪዝም አገልጋይ ዘንድ ጠላት ሆነኖ የመፈረጅን እድል ያጋፍጣል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ በሃገራችን እንጭጭ ሊባል የሚችል እድሜና እምብዛም አልተመደበለትም ሊባል የሚያስችል የገንዘብ በጀት የተደረገበትን የፊልም ጥበብን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚቀርብበትን ትችት በመመርኮዝ ባለሙያዎችና ባለሃብቱ ጥለውት እየፈረጠጡ፤ መንግስትም በግብርና ተዛማጅ ማነቆ ጣጣዎች ከፍተኛ ጫና በማድረግ ስለጥበቡ መሻሻል ግድፈቶች እንዲሻሻሉ የጠቆሙ ሂሰኞችን ለማሳፈር በሚመስል አካሄድ ለዘርፉ ማደግ የራሳቸውን የእንቅፋትነት ድርሻ አየተወጡ ይገኛሉ፡፡
ምንም እንኳ በኛ ሀገር የጥበብ፣ የገንዘብና የባለሙያ አቅም ማነስ የተነሳ ይሄ ነው ተብሎ የሚቆጠር ተውልድ ግብዐት ባይሆንም፤ ያለችውን ዘመን አከፋፍለው የሀገሪቱ ፊልም ከሙዚቃና ቴአትር ጥበብ እንደተወለደ ባሉዋቸው ውስን ማስረጃዎች ማጣቀሻነት ይከራከራሉ፡፡
የሆኖ ሆኖ የፊልምን መነሻ ሀሳብ ተረድቶ ከመተግበር አንፃር ገና ብዙ መሻሻል አለበት የሚሉ አስተያየቶች ከመበራከታቸውና የተለያዩ የፊልም ጥበብ ማሰልጠኛ ማዕከላት ብቅ ብቅ ከማለታቸው የሰሉ ብዕሮችም ገና ቦታ ቦታቸውን መያዝና እርምትን መጠቆም ከመጀመራቸው በቋፍና በስግብግብነት በጥበቡ ዙሪያ እየተሳተፉ ያሉ ነጋዴዎችና አድር ባይ ጠቢባንን እንዲሁም ደንባራ የመንግስት አካላትን ወዳልተገባ እርምጃና እነቅስቃሴ ያስኳተናቸው ይዟል፡፡
ለመሆኑ አስተያየት መስጠት ነውር ነነው እንዴ? ከፊልም ጥበብ የሚገኙ ገንዘቦች መልሶ በይበቡ ዙሪያ ያሉ ሰዎችን ብቃት ለማሳደግና ለፊልሙ ጥበብ የተሸለ ዋስትና እነዲኖር ማስቻልን የሚያበረታቱ አስተያየቶች ያልተጠበቀ የግብር ቁልል እንዲከተል፤ የፊልምና ቴእር መድረኮች በርከት ያሉ ያለስራ የሚቆዩበት ሰዓታት መኖራቸው በጥያቄ ምልክት መጠቆሙ በአስገዳጅ ሁኔታ የፖለቲካ ማራመጃ የውይይት መድረኮች እንዲሆኑ መገደድን ማስከተሉ ምን ያህል ትችትና አስተያየትዎ እዚህ ሀገር እርባና ቢስና እንደተፈለገ ተተርጉሞ ለራስ ውድቀት ጥቆማ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡
እኔ ስለማዳላለት የፊልም ሙያ ዘርፍ ጠቆምኩ እንጂ በሃገራችን ያሉ እንዲሻሻሉ አስተያየት የተሰጠባቸው በርካታ የስራና የንግድ ዘርፎች ሁሉ በመንግስትና በሌሎች “ተፅዕኖ መፍጠር” በሚችሉ ባለጊዜዎች ሚዛናዊ ያልሆነ ፍርድ እየተሰጠባቸውና እንደውግዝ እየተቆጠሩ የአገልግሎት ዘመናቸው እንዲያበቁ ተደርገው ተከታዩ ትውልድ እንዳይጠቀምባቸው ሆኗል፡፡ አሁንም ይህ ጉዳይ የፊልሙን ዘርፍ እያስፈራራው ይመስለኛልና ለሚመለከታቸው ሁሉ ይህን ጥያቄ አነሳለሁ፡፡ ለመሆኑ አስተያየት መስጠት ነውር ነው እንዴ?
Comments
Post a Comment