Skip to main content

ልፋ ያለው በሬ ቆዳው ከበሮ ይወጠራል!

(This Post had been originally posted on my other blog on April 16, 2013. Please consider the post date while reading.)

ይህ ፅሁፍ በ October 29, 2011 ለአዲስ ጉዳይ መፅሄት ተልኮ የነበረ ሲሆን አንዳንድ እርማት ተደርጎለት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ወቅቱ በመፅሄቷ ላይ “ኩበት በሌለበት ጭስ ከየት ይመጣል?” በሚል ርዕስ የሀገራችንን የፊለም ንግድ (ይቅርታ የፊልም ጥበብ ለማለት ተሳቅቄ ነው፡፡) በመውቀስ ለዘርፉ ያለውን ወዳጅነት አሳይቶ ለሌሎች ታዳሚዎችም ጋብዞ ተሰናብቶ ነበር፡፡ እስቲ እኔም እኛ ተመልካቾች ስለማረራችን ትንሽ ልክተብ ብዬ ተነሳሁ፡፡


አሁን ዘመኑ አለማቀፋዊነት እየገነነ የመጣበትና በየሀገሩ ጫፍና ጫፍ እየጠፋ፣ ሁሉም ከተሜ እየሆነ፣ መረጃ ሙሉ በሙሉ እየተዳረሰ፣ በሰከንዶች ልዩነት ድምፅና ምስልን ያቀናበሩ ወሬዎች በየርዕሰ ጉዳዩ  ለጆሮና ለአይን  ሲበቁ ማስተዋል እነኳን ጥበብን ለሚናፍቁና ጠቢባን ነን ለሚሉ ቀርቶ ለእንደኔ ላለውም ተራ ግለሰብ አንዳች መንገድ ይጠቁማል ባይ ነኝ፡፡

ምንም እንኳ ትምህርቴ ያልገፋና በአንድም ዘርስ ተሳክቶልኝ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በጋዜጦችና በመፅሄቶች ለህዝብ እይታና  ጆሮ የቀረበረሁ ሰው ባልሆንም አልፎ አልፎም ቢሆን ስለጥበብ የተፃፉ ፅሁፎችን የማንበብንና ሲተረኩ የመስማት ዕድል ገጥሞኛል፡፡ ይህም ዕድል ለብዙዎች የተነፈገ ስላይደለ የምሰጠው አስተያየትም በተራው ታዳሚና ተመመልካች አናሳ እውቀት ላይ መሰረት ያደረገ ነው ማለት ነው፡፡

ጥበብን በርካታ ጠቢባን እያሞካሹና እያወደሱ ረቀቅ ያለ ትርጓሜ እንደ ሚሰጧት እኔ ብናገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብኛል፡፡ ጠቢባንን  ግን ወረፍ ማድረግ ለእውቅናቸውና እውቀታቸው ተጨማሪ ግብዓት ነውና መቀጠሌ ነው፡፡

ጥበብን መፈለግ
  እንኳን   ዛሬ አለም ልጆቿን እውቀት ለመመገብ የጓዳ ጎድጓዳዋን ክምችት በኮምፒውተራችንና በስልኮቻችን ጫፍ አገናኘታልን ቀርቶ የቀደሙ አባቶች ታሪክን፣ ቋንቋን፣ ባህልን፣ ሳይንስንና ሌሎችን ለመመርመር፣ ለማጤን፣ ለማስተዋልና ለትውልድ ለማውረስ፣ እንደየ ግለሰቦቹ የኋላ ታሪክና ባህል የተለያዩ መከራዎችን በመጋፈጥና ድል በማድረግ አልያም መስዋዕት በመሆን ጠቢብ ለመባል ሳይሆን ጠቢብ ለመሆን ጥረዋል፡፡

ምስጋና ይግባውና ለቴክኖሎጂ፣ ማወቅ ባሻዎ ርዕስ ላይ ጉግልና ሌሎች የፍለጋ መረቦች የጎለጉሉልዎታል፡፡ ስለፊልም ማወቅ ለሚፈልጉም የተለያዩ ድህረ-ገፆች ተኮልኩለዋል፡፡ ስክሪፕት ለመፃፍ፣ ለትወና፣ ለካሜራ ቀረፃ፣ ለሜካፕ፣ ለዳይሬክተር፣ ለአዘጋጅ፣… ወዘተ፡፡

በጥበብ ለመናገር
መቼም ጠቢቡ ከተራው ነዋሪ የሚለየው ነገርን ሁሉ በጥበብ ማቅረብ በመቻሉ ነው፡፡ የማስተዋል ጥበብ፣ የንግግር ጥበብ፣ የስነ-ስዕል ጥበብ፣ የስነፅሁፍ ጥበብ፣ የስነልቦና ጥበብ… ወዘተ፡፡

ታዲያ የፊልሙ ሙያ እነደሌሎች ጥበባት ሁሉ ነገርን በጥበብ የሚያቀርብ መድረክ ነው ማለት ነው፡፡ የፊልሙ ባለሙያም በጥበብ ለህዘቡ ሊገልፅ የፈለገውን ነጥብ ብቻ አድምቆ አስምሮበት ይናገራል፡፡ ሙያተኛው መንግስትን፣ ባለስልጣን ግለሰብን፣ ህዝብን፤ ከፖልቲካ ከማህበራዊ እና ከስነልቦና አንፃር እነዲህ ነህ ብሎ የሚያነቃበት፤ አመለካከትህ አካሄድና ተጋልጦህ ሁሉ ይህን ይመስላልና በርታ ቀጥል አልያም አሻሽል ብሎ የሚመክር፣ የሚገስፅና አንዳንዴም ለቅጣት የሚያጋልጥ መረጃ መሆን የሚችል ዶሴ የሚያዘጋጅበተ ጥበብ ነው፡፡

መቼም አያጋጥምም አይባልምና አፍንጫውን በአደባባይ በጣቱ የሚጎረጉር ነገር ግን “በምትበሉበት ጊዜ በሁለት ጉንጭ መብላት ነውር ነውና ተዉ፡፡” የሚል የስነምግባር መምህር ቢገጥምዎ ምን ይሰማዎታል? ንቀት እንደሚሰማዎ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ምክኒያቱም የጠንቋይ ለራሱ አለማወቅ ህዝቡን ይዞ ገደል እነደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ 

የፊለም ሙያም በብርሃንና ጨለማ መስተጋብር የሚጠበቡበት ድንቅ ሙያ ንደመሆኑ፣ ሊናገሩበት የሚገባቸው በትክክል የጥበቡን ውሃ የጠጡና (ሲጠጣ ያዩ አላልኩም፡፡) እየዘፈቁ የጥበቡን ባህር ሊዘፈቁ የሚዎዱ ብቻ መሆን አለባቸው፡፡ አለዚያ የጠንቋዩ ታሪክ ይደገማል፡፡

ሕዝቡ ምን በደለ?
ጊዜው የቆየ ቢሆንም አንድ የማስታውሰው የየኔ ቢጤ ታሪክ አለ፡፡ ይህ ቀጣፊ ለማኝ ቀን ቀን እግሩ ላይ ቀይ ግራሶ የጠገበ ፋሻ ጠቅልሎ በክራንች ተደግፎ ጭር ባሉ መንደሮች ሲቧግትና ሲሰልል ይውልና ማታ ማታ ከርሱ የሚበረቱትን ቀማኛ ጓደኞቹን ሰብስቦ የቻሉትን ያህል የዘርፋሉ፣ ለወሲብ ጥማታቸውም መለከመልካሚቱን ሴት እየመረጡ በግዳጅ ይገናኛሉ፡፡

ኋላ እንደልማዱ አንድ ቀን ከአንድ መንደር ገብቶ እየቧገተ ሳለ ድንገተኛ ፍንዳታ ይሰማና ክራንቹን ጥሎ ፈትለክ ማለት፡፡ በፍንዳታው ሳቢያ ተደናግጠው ስለነበረ ወዲያው ልብ ያላሉት የአካባቢው ጎረምሶች ፍንዳታው ተራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ዞር ሲሉ የባለክራነቹን ሰው ሁኔታ ይገነዘቡና በሌሊት አካባቢውን ሲያምስ የከረመውን ይህን ቀበኛ መከራውን አብልተውና ዳግም ወዲያ ሰፈር ዝር እንዳይል አስፈራርተው  እንደለቀቁት አስታውለሁ፡፡

አሁን አሁን እየተበራከቱ ያሉ ሲኒማ ቤቶች በየጊዜው የሚወጡትን የሲኒማ ፊለሞች ለህዝቡ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ ሃያ ብር፣ ሰላሳ ብር፣ የምረቃ ጊዜያት ደግሞ መቶ ብርና ከዚያ በላይ ያስከፍላሉ፡፡ ልፋ ያለው ተመልካችም አንዳች አገኝ ብሎ ገንዘቡን ይገፈግፋል፡፡ (ለነገሩ ይሄ ራሱ ልዩ ጥናት ካለልተደረገበት በቀር ተመለልካቹ ፊልም ለማየት  ናፍቆ ወደ ሲኒማ ቤቶች ይሄዳል ለለማለት እቸገራለሁ፡፡ ምክኒያቱም እዚህ ግባ የማይባሉ አያሌ ፊልሞች በተመልካች ባዛት የሀገርኛ የተወዳጅነት ሰንጠረዦች ላይ ይቆያሉና ናው፡፡ በተጨማሪም በርካታ  ወጣቶች ማሳጅ ቤቶችንና ሌሎችን ተጠቃሽ ቦታዎች በስውር ሌላ ልምምድ ለማድረግያ  እነደሚመረጧቸው እየተደረሰበት መጥቷልና ነው፡፡ ምናልባት ተመልካቹ ሲኒማ ቤት እያገኘ ያለው ሌላ ነገር እንደሆነስ?) 

የአአዲስ ጉዳዩ ፀሃፊ ስለዘውግ አንስተው ነበር፡፡ የሚያናድዱ ኮሜዲዎች፣ ጭብጥ የሌላቸው ድራማዎች፣ ሌላም ሌላም፡፡ እስኪ አኔ ደግሞ እርር የምልበትን የምስል ቀረፃ(shot) ትንሽ ልናገር፡፡ ተመልካችም ዐይደለሁ?

·         ከአናት በላይ እይታ(ሔድ ሩም/head room) - አንድ ትዕይንት ላይ ከሚታየው ገፀ-ባህሪ/ድርሰተ-ሰብ አናት አቅጣጫ ሌላ ጉዳይ(ድረሰተ-ሰብ፣ ቁስ፣ ወይም ሌላ ምስል)ከሌለ በቀር ከድርሰተ-ሰቡ አናት ሰፊ ክፍት ቦታን መተው የምስሉን(shots) ትርጉም ያበላሻል፡፡

·         ትይዩ እይታ(ሉኪነገ ሩም/looking room) - በምስሉ(shots)ላይ የምናየው ድርሰተ-ሰብ እያናገረ/እያየ ያለውን ሌላ ድርሰተ-ሰብ፣ ቁስ ወይም ሌላ ምስል በቀኝ በኩል ከሆነ በስተቀኝ፤  ቁሱ በግራ በኩል ከሆነ ደግሞ በስተግራ በኩል ክፍት ተደረጎ ይቀረፃል፡፡ ድርሰተ-ሰቡ አይኑን ተክሎ ፊትለፊት በሙሉ (screen ላይ) የሚታይ ከሆነ ግን ድርሰተ-ሰቡ  ጉዳዩን ከተመልካቹ ጋር እነንዳደረገው ይታወቃል፡፡

·         ከባህሪ ግንባታ ጀምሮ ያለው ድርሰተ-ሰቡን በትወና የመወከል ጉዳይ በአዘጋጁ ብቃት ላይ የተመሰረተና አዘጋጁ የለእውቀት ሊወጣው ስለማይችል በቂ የ ሲኒማ ቃላት እውቀትና ጥናት ይጠይቃል፡፡ሌሎችም ሌሎችም ቀላል የሚመስሉ መሰረታዊ እንከኖችን ማየት የታከቱ ባለሙያ ወዳጆቼ ከሲኒማ ቤቶች ለመራቅ እየተገደዱ ነው፡፡

መቼም የፅሁፌ አላማ እንዳለመሆኑ መጠን ከዚህ በላይ በርካታ ነጥቦችን ለማብራራት ባልሞክረ ጥሩ ነወ፡፡ ነገር ግን ብዙ የሀገርኛ ፊልሞቻችን መሰረታዊ የቀረፃ (shot to screen) ችግር እንዳለባቸው ገሃድ ነው፡፡

ስለየቀረፃው(shot) የምስል አቅጣጫና በስከሪን(screen) ላይ የሚታየው የብርሃን የሰው/ቁስ ምጣኔ እና ድምፅ ግብር በትንቃቄ እና አዘጋጁ(the director) በመረጠው አተረጓገጎም መንገድ  በፊልሙthe (movie) በኩል ለህዝብ የሚተላለፍ ሲሆን አዘጋጁ ምልክትና የአተያዩን አቅጣጫ የሚያሳይበት ስለመሆኑ በርካታ ፅሁፎችን ከመፀሃፍት፣ ከመፅሄቶችና ከተለያ ድህረገፆች መማር ይቻላል፡፡ 

ለመሆኑ አምሪካዊ መሰረት ያላቸው አንጋፋ የፊልም ባለሙያ አርቲስት ማያ ገሪማ “ጤዛ” የሚል ፊልማቸውን በምን ደረጃ ሰሩት? “ሒሩት አባቷ ማነው?” ከተሰራ ከስንት ዘመን በኋላ ሌሎች በዚህ ጥበብ ዙሪያ በመስራተቸው ገንዘብ እያካበቱ ያሉ  ግለሰቦች ለተመልካቹ ዛሬ የቅርና ለነገ ምን ሊሉት ይፈልጋሉ? 

የንግድ ቋንቋ
ዘመናዊ ንግድ በማስታወቂያ የጀርባ አጥንት እንደልቡ በግሩ ቆሞ እንደሚራመድ ይታወቃል፡፡ ማስታወቂያም ቢሆን በስነምግባርና ህግ ተላለፊነት ቀጣት ሸንቆጥ አየተደረገ  የሚገራ በህዝብ ላይም ተገቢ ያልሆነ ተፅእኖ ካሳደረ ካሰ የሚከፈልበት ሙያ ነው፡፡

 የኛ  ሀገሩ የማስታወቂያ ስራ ከእደሜው አንፃር ያን ያህል ፍርጃ ባይገባውም ቀጥ ወደማጣትና አጉራዘለሎችን፣ በተለይ በጥበብ ስም የሚዘርፉትን ወደማበረታት እንዳይሄድ ሀይ መባል አለበት፡፡
ለምሳሌ ማስታወቂያ በሚል ስያሜ ባይሆንም የህዝቡን ልብና ገንዘብ አስልተው ለመበዝበዝ እንዲመቻቸው እነዲህ ያሉ የወቀሳና ነቀፋ ፅሁፎችን በአደባባይ የሚያወግዙ ጠቢባን ነን ባዮች አሉ፡፡ “ተዉን እንስራበት” ሲሉም ይደመጣሉ፡፡ ለምን ፀሀፊውም እንዲፅፍ እነርሱም እርምት መውሰድን ሲለማመዱት ማሳየትን አናስተዋውቅም?

ትውልድን ማኮላሸት
የሙያ አፍቃሪ ነኝ ለሚል ሰው ይህ የተጠቀሰው ርዕስ ስድብሊሆንበት ይገባል ብዬ አላምንም፡፡
ነገ (ዛሬ እየመጡ ተስፋ ቆርጠው የሚመለሱትነን ወይም ጠማማ እድገት ለማደግ የተገደዱትነን ሳይጨምር) ብዙዎች ወደዚህ የሙያ ጥበብ በነፍስ ጥሪ ይጠራሉ፡፡ አንዳች ማፍራት፤ትውልዱ አላይ ያለውን ማሳየት፤ ጭለማውን ማብራት፤ ችንቀቱን ማስረሳት…ወዘተ፡፡ ታደያ እነዲህ የማድረግ ተነሳሽነት ከየት ይመጣል? በመሙያ ስልጠና አስፈላጊነት ሳያምንስ ምን ባለሙያ ያሰኘዋል? የማሳየት ፍላጎተ፣ በቂ እውቀትና አቅም ቢኖረውስ ለየትኛው ተመልካች ያሳየዋል? (ተመልካቹ አሁን ባሉት የፊልሞች ጠራት ማጣትና ህልመ ቢስነት ምክኒያት ወደ ድራፍትና ጭፈራ ቤት እግረ መንገድ በሚል ስበብ ጀምሮታልና በዚያው ይሰደዳል የሚል እምነት ስላለኝ ነው፡፡) አያድርስ! አያድርስ!

Comments

Popular posts from this blog

ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም.የግጥም መድብል ....

አስገራሚ ገጠመኞች የተስተዋሉበት የግጥም መድብል ምርቃት ትናንት 05/04/2006 ዓ.ም. በልዩ ሁኔታ በኢትዮጲያ  ወመዘክር አዳራሽ ተፈፀመ፡፡

ቀልድ ስላለማወቃችን

12/11/2006EC አንድ ሰሞን ወደሁለት ተከፍላ ብዙም ሳትቆይ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው ሱዳን የገጠማትን ምስቅልቅል ሁኔታ ለመከታተል አለም ሁሉ ጆሮውን አቁሞ ነበረ፡፡ ቀድሞም ጠግቦ ያላደረው ደሃ ሕዝብ ነፍሱን ስለማቆየት ሲል ወደጎረቤት ሀገራት ተሰዷል፡፡ በዛ አስቸጋሪ ወቅት ግን አቶ ሳልቫኪየር ከየሀገራቸው እድገትና ስልጣኔ ያልተመጣጠነ ምቾት ስላሰከራቸው አቻዎቻቸው ጉዳይ እንጂ ስለ ሕዝባቸው ፈፅሞ ግድ የሌላቸው እንደሆነ መሰከሩልን፡፡ “የፀጥታውን ስምምነት የፈረምኩት የኢትዮጲያው ጠቅላይ ሚኒሰተር አስርሃለሁ ስላሉኝ ነው”-ብለው አስደመሙን፡፡  ጋዜጠኞቹም ለጉዳዩ መልስ ሲጠባበቁ ቆዩና ሰሞኑን አቶ ኃይለማሪያምን ማብራሪያ ይጠይቋቸዋል፡፡ እርሳቸውም ሳልቫኪየር ቀልዴን ነው ብለዋል ሲሉ መለሱ፡፡ እንዲያውም እነዚህ ጋዜጠኞች ቀልድ አያውቁም ብለው መናገራቸውን ሊያብራሩ ሞክረው አለፉ፡፡ ይህም የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ደረቅ ቀልድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኢቴቪ 1 ፣ 2 ፣ 3 ፣ 4 ተብሎ ይቀለዳል፤ ስለመብራት ስርጭት ብዙ ቁም ነገር የሚመስሉ ቀልዶች እንሰማለን፤ እናያለን፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት ላይ በተጠናከረ መልክ እየሰሩ መሆኑን ይነግሩናል__የቀልዳቸውን፡፡ መንግስት ጸረ - ሰላም ሀይሎች የህዝብን ጥቅም የሚነኩ ኢ - ሰብዐዊ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው ብሎ የቀልዱን ይነግረንና አሴሩ የተባሉትን አሳራቸውን ያበላቸዋል፤ግን የቀልዱን ነው፡፡የሃገሪቷን ሰላም ለማደፍረስ ስለመነሳታቸው መረጃ የለማ ! ቀላል የከተማ ባቡር መጓጓዣን ስራ ለማሰጀመር ሩጫው እየተፋጠነ መሆኑ በተደጋጋሚ በቴሌ...

ናዝሬትዬ መሪዎችሽ ለምን ይፈሩሻል?

Tesfaye Waktola https://www.facebook.com/twaktola Andinet Ada-nazreth ናዝሬትዬ መሪዎችሽ ለምን ይፈሩሻል? ድሮም ጃንሆይ ናዛሬት/አዳማ መምጣት አይወዱም ነበር፣ይባላል፡፡በዚህም የተነሳ ለገላውዴዎስ ት/ቤት መሰረትና ምርቃት ከመምጣታቸው ውጪ ሌላ ጊዜ መች እንደመጡ ሲነገርም አልሰማሁም፡፡መንጌም ሲመጣ በጣም ተደብቆና በድንገት ሲሆን ፣የማስታውሰው ለናዝሬት ቴክኒክ ኮሌጅ (የዛሬው አዳማ ዩኒቨርሲቲ) መሰረትና ምርቃት መምጣቱን ነው፡፡ከዚያ በተረፈ ሁለቱም መሪዎች ወደ ሶደሬ ሲያልፉ ረዥም እድሜ ተመኙ ተብሎ ሕፃናት ወጥተን ቪቫ (VIVA JANHOY! …viva mengistu!..)ብለን እንገባ ነበር፡፡ያኔም ድንገት ካየናቸው ደስታችን ወሰን የለውም ነበር፡፡የልጅ ነገር!ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እጫወት ነበር …ያለው ማነው? ታዲያ ፍርሃት የተጋባበት መሌም ናዝሬት መጣ ከተባለ ከተማው በፌደራል ይወረራል፡፡ከዚያ የት እንዳደረ ሳይታወቅ ወይ ምሽቱን ሄዷል ወይ …አድሯል፡፡ካደረ ጎብዟል፡፡ግን መሌ ሶደሬ ሄዶ ያውቃል?….ቢዚ ስለነበር ምስኪን፣…. ግን ግን-ሶስቱም መሪዎችሽ ለምንፈሩሽ- ---እውነት ግን አዳማ/ናዝሬትን ለምን ፈሯት…? እስቲ እኔ ልገምት፡፡ ጊዜው በጣም ሩቅ ነው ይባላል፡፡ዓጼ ገላውዴዎስ ከግራኝ ጋር ጦርነት ገጥመዋል፡፡ጦርነቱ ተፋፍሞ ዓጼው ብዙ ከገፉ በኋላ ግራኝ ጦሩን አስተባብሮ እየገፋ ይመጣል፡፡ይሄኔ ላለመማረክ ሲዋጉ የነበሩት ንጉስ በስተመጨረሻ ይቆስላሉ በኋላም አሁን ካለው ከዓጼ ገላውዴዎስ ከፍ ብሎ ካለው ከአለሌ ወንዝ ማዶ ባለ ቦታ ተገድለው ተገኙ፡፡በኋላም ግራኝ አንገታቸውን ቆርጦ ወደ ሃረር ወስዶ በግንቡ ላ ሰቀለው የሚል ዲስኩር በገላውዴዎስ ት/ቤት ግቢ ውስጥ በ 50ኛ ...