Note: - posted date: June 01, 2018.
- I found this as a draft on my blog and regretted not posting it on time, it was written 4 years ago.
Now: re-posted here because I am cleaning my other blog.
ለመሆኑ በግንቦት 20 ነፃነት የታወጅው ለማን ነው? ለራስ ወዳድ እና ለዝራፊ ዘርኞችና ተከታዮቻቸው ይሆን? ለማንኛውም የጠብ መንጃ የእርስ በእርስ ጦርነት እነዲቆም የታወጀበት ቀን ተብሎ ቢሰኝ ኖሮ ያለጥርጥር ከአድዋ እኩል ክብር የሚያሰጥ ይሆን ነበር፡፡
ያለመታደል ሆኖ መሪዎቻችን ትናንትን ብቻ በማነፃፀር በጎ የሰሩ እነዲመስል የሚያደርጉት ጥረት ውጤቱ ሆዳቸውን ለማስፋት ነውና ለምስኪኑ ዜጋ እኔ በግሌ ምንም ማድረግ ያለመቻሌ ሁልጊዜም ያንገበግበኛል፡፡
ስንት ሆዳሞችን እያበረታቱ ሀገሪቱን ራቁቷን ለማስቀረት ከጣሩ ሆዳም መሪዎች መካከል አቶ መለስን ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር፣ በዘር እና በሃይማኖት ሽፋን ሀገራችን ኢትዮጲያን ከአንድነት ወደ መበታተን ለማድረግ ያደረጉት ጥረት ብቻ ነው፡፡
ደግነቱ የኢትዮጲያ ህዝብ ፎረሙላ እና ቀመር እንኳን ለ አምባገነን መሪዎቿ ይቅርና በፀሎት ተጋን ለሚሉትም ምስጢር ሆኖባቸው ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡
Comments
Post a Comment