Skip to main content

Posts

ሰላም

ያቺ ጀግና እናቴ ስምንት ወንዶች ወልዳ፤ የሚጦራት አጣች፣ ረሃብ አንገላታት፣ ቁሩ ቀጭቶ አድምቶ፣ ማቅ አልባሷን ዘልቆ፣ እንዳልሆነ ሆነች፡፡   ያቺ ጀግና እናቴ ስምንት ወንዶች ወልዳ፤ ሁሉን ለጦር ማግዳ፤ በጉያዋ እሳት፣ እራሷን አንድዳ፣ በንዋየ ፍቅር፣ በስካረ ምንዳ፡፡   አይ እምይ እናቴ፤ ትረፊ ለሕይወቴ፤ ምንሽም መድሀኒት ነው፣ ይሽተተኝ በሞቴ፡፡   እንዳላገጡብን፣ እንደተላገዱ፤ እነርሱው ቆምረው፣ እነርሱው ሲሰጉ፤ ከጉጭን ወጥተው፣ ጎናችን ሲወጉ፤ ቀጠናውን አልፈው፣ አለምን ሲያሰጉ፤ ስንቀለብሰው፣ ጦርነቱን ባንዴ፤ መደቆሳቸውን፣ አምነው ዋጡት እንዴ ?   አይ እምይ እናቴ፤ በእኛ እና በእነሱ፤ በአበረ እና አበሩ፤ ሽምቅና ክተት፤ መፍረስና አንድነት፤ በአንድነት ልዩነት፤ በሕበረብሔር ዜማ፤ ምናምን እያልን፤ ስምንቱም ልጆችሽ እየተዋደድን፤ እየተቋሰልን፤ እየተዋደቅን፤ ስርዝ ድልዝ ታሪክ፣ ቅርስ እንገነባለን፡፡ ተረኛ እስኪያፈርሰው፣ ዛሬም እንሰራለን፡፡   አንቺ ጀግና እናቴ፣ ስምንት ጊዜ ያማጥሽው፤ ታምር ሚስጥራቱን በማህፀን አዝለሽ፣ በእንግዴ ልጅ ስበብ፣ ቀብረሽ የሸሸግሽው፤ እስኪ አፍሽን ክፈች፣ ተናገሪው ይውጣ፤ እህህ እና እዬዬሽ፣ በንግግር ይንቃ፤ በውይይት ይድቃ፤ ነጠላ መዘቅዘቅ፣ ፊት መንጨትሽ ይብቃ፡፡   እምዬ እናት አለም ማህፀነ ለምለም፤ ከአረንጓዴው በቀር፣ ትዝ የሚለን የለም፤ ብለን እናውጋቸው ለልጅ ልጅ ልጆችሽ፤ ከእርግማኑ ያምልጡ ተባርከው በእጆሽ፡፡   አንቺ ጀግና እናቴ፣ ስምንት የወለድሽው፤ ስምን...

አሁንም መጠየቅና መጠየቅ አለብን!!!

የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዳይሻሻል እንሻለን?!   እኔ ሀገር እየኖራችሁ ስለትራንስፖርት ችግር ሳትሰሙ እና ሳታወሩ መዋል እና ማደር ከቶ እንደማይቻል የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ በሁለቱም ገዢዎቻችን   (በሙሰኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና በህጋዊ ማእቀፍ በህገወጥነት ከሚበለፅጉት ነጋዴዎች) ዘንድ የመፍትሄ ሀሳብ ሊቀርብበት የተደፈረ ጉዳይ እንኳ አልመስል ብሏል፡፡ የመኪና መንገዶች አብዛኛው አስፋልት መንገድ ከፈሰሰበት የሀብት መጠን አንጻር በበርካታ ምክኒያቶች ተገቢውን አገልግሎት ሳይሰጥ እንደሚቀር ከሁሉ አይን የተሰወረ ባይሆንም፣ መልካም አስተዳደር ጉድለት ግን ችግሩን አባብሶታል፡፡ እኔ ተዘዋውሬ በማውቅባቸው ቦታዎች ሁሉ ያስተዋልኩት አንዱ ነገር የመኪና ማቆም (ፓርኪንግ) ነው፡፡ የቀለበት መንገዶችን ጨምሮ (ለብዙ የሙዚቃ ቪዲዮ ክሊፖች እንዳልተመረጡ …. ጊዜ ጥሏቸው…) በርካታ የአስፋልት መንገዶች በህጋዊና በህገ-ወጥ መንገድ የፓርኪነግ አገልግሎት ለመስጠት ብቻ የተሰሩ ይመስላሉ፡፡ በርካታ ጎሚስታዎችና ጋራዦችም ስራቸውን በተቀላጠፈ መንገድ የሚያከናውኑት በእነዚህ በከፍተኛ ወጪ በተገነቡ   አስፋልት መንገዶች ላይ ነው፡፡ አንዳንዱ መንገድ ላይማ በግራም በቀኝም መኪኖች ተኮልኩለው ቆመው ታክሲዎችም ሆኑ የአደጋ ጊዜ አምቡላንሶች በስቃይ ጩኸት እየታገሉ የእንፉቅቅ ርጀም ጊዜ ፈጅቶባቸው እንደሚያልፉ አላየንም ብሎ ሊክድ የሚችል ነዋሪ አይገኝም፡፡ እነዚህን ቁጭቶች በገንዘብ ስሌት ቀይረን ብናያቸው ነገሩን የተሸለግልፅ የሚያደርገው ይመስለኛል፡፡ ….... ለምሳሌ አንዲት ኮብል ንጣፍ መንገድ ዳር የሚቆምን አነስተኛ ርዝማኔ ያለው ተሸከርካሪ ምን ያህል ገንዘብ ላይ ቆሞ እንደሚውል እናስላ፡፡ ...

ቀልድ ስላለማወቃችን

12/11/2006EC አንድ ሰሞን ወደሁለት ተከፍላ ብዙም ሳትቆይ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው ሱዳን የገጠማትን ምስቅልቅል ሁኔታ ለመከታተል አለም ሁሉ ጆሮውን አቁሞ ነበረ፡፡ ቀድሞም ጠግቦ ያላደረው ደሃ ሕዝብ ነፍሱን ስለማቆየት ሲል ወደጎረቤት ሀገራት ተሰዷል፡፡ በዛ አስቸጋሪ ወቅት ግን አቶ ሳልቫኪየር ከየሀገራቸው እድገትና ስልጣኔ ያልተመጣጠነ ምቾት ስላሰከራቸው አቻዎቻቸው ጉዳይ እንጂ ስለ ሕዝባቸው ፈፅሞ ግድ የሌላቸው እንደሆነ መሰከሩልን፡፡ “የፀጥታውን ስምምነት የፈረምኩት የኢትዮጲያው ጠቅላይ ሚኒሰተር አስርሃለሁ ስላሉኝ ነው”-ብለው አስደመሙን፡፡  ጋዜጠኞቹም ለጉዳዩ መልስ ሲጠባበቁ ቆዩና ሰሞኑን አቶ ኃይለማሪያምን ማብራሪያ ይጠይቋቸዋል፡፡ እርሳቸውም ሳልቫኪየር ቀልዴን ነው ብለዋል ሲሉ መለሱ፡፡ እንዲያውም እነዚህ ጋዜጠኞች ቀልድ አያውቁም ብለው መናገራቸውን ሊያብራሩ ሞክረው አለፉ፡፡ ይህም የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ደረቅ ቀልድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኢቴቪ 1 ፣ 2 ፣ 3 ፣ 4 ተብሎ ይቀለዳል፤ ስለመብራት ስርጭት ብዙ ቁም ነገር የሚመስሉ ቀልዶች እንሰማለን፤ እናያለን፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት ላይ በተጠናከረ መልክ እየሰሩ መሆኑን ይነግሩናል__የቀልዳቸውን፡፡ መንግስት ጸረ - ሰላም ሀይሎች የህዝብን ጥቅም የሚነኩ ኢ - ሰብዐዊ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው ብሎ የቀልዱን ይነግረንና አሴሩ የተባሉትን አሳራቸውን ያበላቸዋል፤ግን የቀልዱን ነው፡፡የሃገሪቷን ሰላም ለማደፍረስ ስለመነሳታቸው መረጃ የለማ ! ቀላል የከተማ ባቡር መጓጓዣን ስራ ለማሰጀመር ሩጫው እየተፋጠነ መሆኑ በተደጋጋሚ በቴሌ...

ፖለቲኳስ ቢሆን...!

                                                                                                                                      19/10/2006 ኳስ ክብ መሆኗ ብቻ ለአለም መነጋገሪያ አላደረጋትም፡፡ በእግር መለወሷም ከቶ አላስናቃትም፡፡ ብዙ ሚሊዮኖችን ታስፈነጥዛለች፤ ብዙ ሚሊዮኖችን ታስመነዝራለች፤ ለብዙ ሚሊዮኖች የስራ እድል ፈጥራ እንጀራ ታበላለች፡፡ ሊያውም “fair play” የሚል የሚዛንን አድልዎ የሚኮንን መፈክር አንግባ! ...

I am an Oromo too! ስለምን ይዘበትብናል…?

እኛ በሰው አምሳል መፈጠራችንንና ከናንተው እኩል የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ስለመሆናችን እንዴት ተዘነጋችሁ! ቀደምት አባቶቻችን ስንቶቹን ደራሽ ያጡ የሀገራችንን ኢትዮጲያ ልጆች ጡት እያጠቡ ከአብራካቸው ከወጡ ልጆቻቸው እኩል እያስተማሩና ሀብት ንብረት እያወረሱ ለወግ ማዕረግ ያበቁ መሆናቸው ተረሳችሁ…? ኢትዮጲያዊነትን ከኦሮሞ ሕዝብ፤ የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮጲያዊነት በመነጣጠል የምታገኙት ልዩ ጥቅም እነደሚኖር ሳይታለም የተፈታ መሆኑ በየጓዳው የሚወራው ለዚህም አይደል ብላችሁ እነዴት አልጠረጠራችሁም…? ሕዝቡ ሁሉ ተጠርጣሪ (ሊያውም በሽብርተኝነት) ተብሎ በይፋ እስር ቤት   እንዲገባ የሚቻላችሁ መስሏችሁ ይሆን…? እንኪያስ የትኛውን ሕዝብ ልትመሩት ነው…?(ይቅርታ በአይንህን ጨፍን ላሞኝህ ልትነግዱበት ነው…?- ለማለት ፈልጌ ነው፡፡) ለነገሩ ዞን 9ኞችን የመፍጠሩ ስትራቴጂ ሲነቃባችሁ ዞን 9 ነዋሪውን ትታችሁ ብሎገሮቹን ታስሩ ታንገላቱ ታሳድዱ ዘንድስ ማን አይዟችሁ እንዳላችሁ ምን ይታወቃል…? ይህች ፅሁፍ እንኳ ካቅሟ በመንግስታችሁ እውቅና አግኝታ ከመነበብና የፀሃፊውን መብት ከማስከበር ትታገድ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል…? ዓለም ሁሉ በንግድ /ቢዝነስ/ ፅንሰ ሃሳብ በተወጠረችበት በዚህ ዘመን የኋሊዮሽ የተንቋሸሸሽንበት ያህል እንዲሰማን የተደረግንባቸውን የሀገራችንን ታሪክ እየባዘታችሁ ስለምን የትውልዱን ተስፋ በቁንፅል ሃሳብ በመወጠር ትቀጩብናላችሁ…? እናንተ የምትገነቡትን ሕንፃ፣ ለሎችን በመጨቆን ስንጥቅ የምታተርፉበትን ንግድ፣ በሀሰት ህዝብን እየሸነገላችሁ የምትቸበችቡትን መሬት፣ የምታቀያይሯቸውን መኪኖች፣ ህዝብ የሚያውቃቸውና የማያውቃቸው በአጭር ጊዜ የምትበለፅጉባቻው መንገዶች ሁሉ ከዓይንና ከህሊናችን የተሰወሩ ይመስላችሁ ይሆን…...